Netsanet: የወያኔ ግፍ በኡስታዝ አቡበከር አንደበት ሲጋለጥ! ክፍል 4

Montag, 7. April 2014

የወያኔ ግፍ በኡስታዝ አቡበከር አንደበት ሲጋለጥ! ክፍል 4

April 7/2014
ሰኞ፤ መጋቢት 29/2006፤ ፈሰቢር፡-
በማዕከላዊ ከወያኔ በኩል የደረሰባቸው ሰቆቃ!
ሰሞኑን ስናቀርብ እንደነበረው ሁሉ፣ ኡስታዝ አቡበከር ማክሰኞ መጋቢት 23/2006 ለኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፌደራል ከፍተኛ ፍርድቤት ልደታ (ልዩ) ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት ባቀረበው የክስ መከላከያ ላይ ከመጋረጃው በስተጀርባ ወያኔ ልክ የሌለውን እና በሰው ልጆች ላይ ሊፈጸም የማይችል ግፍ በመፈጸም የተጠመደ ደመኛ ገዢ መሆኑን አመላክቷል፡፡
ውዱ የኮሚቴዎቻችን ሰብሳቢ ኡስታዝ አቡበከር በማዕከላዊ ማሰቃያ ቤት በእሱ ላይና በሌሎቹ ባልደረቦቹ በሆኑት የሰላም አምባሳደሮች ላይ የዓለም አቀፍ እና የሀገርኛ ህጎችን ሙሉ በሙሉ በናደ መልኩ በወያኔ የተፈጸመባቸውን ሰቆቃና ግፍን አሁንም በዚህ መልኩ ይገልጽልናል፡-
“በድብደባ ስቃይ ብዛት የከፊል ተከሳሾችን ጥርስ ሰብረዋል፣ አካላቸው ከሰውነት ተራ እንዲወጣ አድርገው አጎሳቁለዋል። ከምርመራ ጊቢው ውጭ በመውሰድ ሽጉጥ ደግኖ ከማስፈራራታቸውም በላይ ቤተሰቦቻቸውን እንደሚያጠፏቸው በመዛት ከላይ ከተዘረዘሩት ግዙፍ ተጽዕኖዎችና ግዳጆች ጋር ተዳምሮ ባልተጻፈበት ነጭ ወረቀት ላይ የእምነት ቃላቸው እንደሆነ አድርገው እንዲፈርሙ አድርገዋል፤ ምስክሮች ባሉበት በድጋሚ እንዲናዘዙ በማድረግ ያለፈቃዳቸውና ያለ ተጨባጭ ምክንያት በፎቶግራፍና በተንቀሳቃሽ ምስል ካሜራ ቀርጸዋል።
ተከሳሾች የደረሰባቸውን ስቃይ የጊዜ ቀጠሮ መዝገቡን ለያዘው ፍርድ ቤት፣ ለጠበቆችና ለሶስተኛ ወገን ከተናገሩ፤ ከችሎት መልስ የበለጠ ስቃይ እንደሚጠብቃቸው በመዛት ያስፈሯሯቸው ሲሆን በፍ/ቤቱ ተስፋ ጥለው ለማጋለጥ የደፈሩትን ከፊል ተከሳሾች ደግሞ ከፍ/ቤት መልስ ለብቻቸው አስረው እንዲሰቃዩ አድርገዋል።”
የእምነት መብታችንን የማስከበሩ ሂደት በድብደባ አይገታም!
እስከመጨረሻው ለኢስላም እንታገላለን!
አላሁ አክበር!

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen