Netsanet: Mai 2014

Samstag, 31. Mai 2014

የጎዳና ተዳዳሪዎቹ ፍቅረኛሞች Meet Ethiopian homeless couples

May 31/2014ለሶደሬ ብቻ 
ቁም ነገር ቅጽ 13 ቁጥር 179 ግንቦት - ሰኔ 2006 ቁም ነገር በየ15 ቀኑ የሚወጣ
በ አዜብ ታምሩ 
ወጣቶች ናቸው፡፡ ዓለምፀሀይ ዘላለምና አበራ ተካ ይባላሉ፡፡ ኑሮን በጎዳና የሚገፉ፤ ተቃቅፈው ውለው ተቃቅፈው የሚያድሩ፤ ማንንም ለመስማት ጊዜ የሌላቸው፤ ከጥቂት ቡቱቶዎቻቸውና ከትንሿ ውሻቸው ውጪ ምሳ ካገኙ ስለራት የማያስቡ ከፍቅር ሌላ ምንም የሌላቸው ወጣቶች ናቸው፡፡ እነዚህ ወጣቶች በአዲስ አበባ ከተማ መሀል አውቶቡስ ተራ አዲስ ከተማ መሰናዶ ት/ት ቤት ጀርባ ከሚገኘው መንደር የኢትዮጵያ ህፃናት መርጃ ድርጅትን አጥር ተገን አድርገው የሚኖሩ ፍቅረኛሞች ናቸው፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎች ነጋ ጠባ የሚገረሙባቸው፤ ቤት ውስጥ ያጡት አንዱ ላንዱ መስዋዕትነት የሚከፍልለት ፍቅር እዚህ መገኘቱ አጀብ የሚያሰኛቸው፡፡
በነዚህ ወጣቶች ፍቅር ከሚገረሙት ሰዎች መካከል አንዱ አቶ በላይ ይባላሉ፡፡ የኢትዮጵያ ህፃናት መርጃ ድርጅት የቴአትር ክፍል ሀላፊ የሆኑት እኒህ ሰው ናቸው ስለወጣቶቹ የነገሩኝ፡፡ ከእለት ጉርሳቸው ውጪ ሌላ የሌላቸውና ከማንም ምንም እንደማይፈልጉ የሚናገሩት ወጣቶቹ በቀላሉ ያዋሩኛል ብዬ አልጠበኩም፡፡ እንዳሰብኩት ግን አልሆኑም፡፡ ከኔ ጋር ለማውራት ፍቃዳቸውን አልከለከሉኝም፡፡ ጥግ ይዘን ማውራት ጀመርን፡፡ እየሆነ ያለውን የሰሙ የአካባቢው ወጣቶች ተሰበሰቡ፡፡ ግርግሩን ፈራሁ፡፡ ወደ ድርጅቱ ግቢ ተያይዘን ገባን፡፡ የአካባቢው ልጆች ግን ‹‹ስለነሱ እኛን ጠይቂን፤ ነጋ ጠባ የምናያቸው የሚያስፈልጋቸውን የምናውቅ እኛ ነን›› አሉኝ፡፡ ያለ ምክንያት አይደለም እንዲህ ማለታቸው፤ እንደኔ ለአካባቢው እንግዳ የሆነ ሰው በመጣ ቁጥር ፍርሀታቸውን ያውቁታልና ሁሌም እንዲያ ይላሉ፡፡
“ፈራን መለያየት ፈራን” ይላል የሁለቱ ወጣቶች ልብ፡፡ የከበቡዋቸው የዚያ ሰፈር ልጆችም ‹‹እናንተን የሚለየው ሞት ብቻ ነው፡፡›› ይሏቸዋል፤ ግን ከዕለት ያለፈ ነገር ሊያደርጉላቸው አልቻሉም፡፡ እሱ ለሷ፤ እሷ ለሱ በሚሆኑት ነገር ተደንቀው የቀን ትዕይንት ካደረጓቸው ግን ከራረሙ፡፡
ዓለምፀሀይ ዘላለም ‹‹እድሜዬ 27 ነው›› አለችኝ፡፡ በደንብ ተመለከትኳት፤ ከዚህ አታልፍም፤ ጥቂት እውነት ብዙ መዘባረቅ የተቀላቀለበት ንግግሯ ከሚደጋገሙት መሀል እውነቶቹን እንድመርጥ አስገድዶኛል፡፡ በንግግሯ መሀል የእንግሊዝኛው ቃላት መደጋገም ሌላ ጥያቄ ያጭራል፡፡ አለምፀሀይ ጎበዝ ተማሪ ነበረች፤ ደብረ ማርቆስ ከተማ በሚገኘው ዋሸራ ብሮድቪው ኮሌጅ የሁለተኛ ዓመት የሴክሬተርያል ሳይንስ ተማሪ ሳለች የአእምሮ ህመም ስለገጠማት ትምህርቷን አቋርጣለች፡፡ (እሷ“ነቅዬ” ነው ትለኛለች ደጋግማ) አክስቶቿ ለማስታመም በሚል ወደ አዲስ አበባ ካመጧት በኋላ ረስተዋታል፡፡ ሄድ መለስ እያለች ነገሮች እየተደበላለቁባት ስትነግረኝ አዲስ አበባ ከመጣች ሦስት ዓመት አልፏታል፡፡
ዝም ብለው ሲመለከቷት ከንግግር ቅልጥፍናዋና ጥንቅቅ ከማለቷ የአእምሮ ችግሯን ታስረሳለች፡፡ በቀላል ህክምና ለውጤት የምትበቃ ትመስላለች፡፡ ነገሩን የሚያውቅላት ይኑር አይኑር እንጃ እንጂ ብዙ ያነበበችም ለመሆኗ በንግግሯ የምታነሳሳቸው የዓለማችን ፀሀፍትና ፈላስፋዎች ምስክር ናቸው፡፡ እነሶቅራጥስ፣ አርስቶትልና ሌሎችም በአንደበቷ ሲጠቃቀሱ ይቺ ልጅ የሆነ ከአቅሟ በላይ የሆነባት፤ ሰው አልረዳ ያላት ነገር ቢኖርስ ብዬ ገመትኩ፡፡ ደግሞም ጠየኳት “በልጅነትሽ ምን መሆን ትፈልጊ ነበር?” ስል፡፡ ‹‹ሳይንቲስት መሆን፣ የፊዚክስ ሊቅ መሆን ፣ጠፈር ላይ መውጣት…” ለምጠይቃት የምትሰጠኝ መልስ መጨረሻው ብቻ ነው ፈሩን የሚለቀው፡፡ በአብዛኛው በትክክል እየነገረችኝ ቆይታችን ቀጠለ፡፡
በወጣትነት እድሜ በተለይ በሃያዎቹ መጀመሪያ አካባቢ የውስጥ ፍላጎቶቻችን የሚጋጩ ይመስለኛል፡፡ የሚያደምጥ የሚረዳ ሲጠፋ የሚፈልጉት ሳይገኝ ሲቀር ደግሞም የሚናገሩት ከማህበረሰቡ ለየት ሲል ‹‹ለየላት›› መባል ከዚያም ቤተሰብ መፍትሄ የሚለውን ሲያደርግ የአእምሮ ውጥረት ሲባባስ ጭንቀት ሲበረታ የባጥ የቆጡን መቀባጠሩ ቢያይል አይገርምም፡፡ በአለም ፀሀይ ህይወት ውስጥ ተመሳሳይ ነገር እንደተከሰተ ለመገመት አይከብድም፡፡ እሷንና ተወልጄ አድጌበታለሁ ያለችኝን ደብረ ማርቆስ ከተማ ቀበሌ ሰባት ሸዋ በር ተብሎ የሚጠራው ሰፈር ከፖሊስ ጣቢያው ወረድ ብሎ ያለውን መንደር አስተያየኋቸው፡፡ የእሷ ፍላጎት ከማህበረሰቡ አመለካከት ጋር ሲጋጭና የምታነሳቸው የተለዩ ሃሳቦች ‹አበደች. እያስባላት በድግግሞሹ ተገፍታ ለአዕምሮ ህመም እንደተዳረገች ያስታውቃል፡፡
አበራ አጠገባችን ተቀምጧል፡፡ የምናወራውን እየሰማ ነው፡፡ አንዳንዴ በወሬያችን መሃል ሳቅ ይላል፡፡ ቀይ ረዥም ቆንጆ ወጣት ነው፡፡
“አበራ ተካ እባላለሁ፡፡ ተወልጄ ያደኩት አዲስ አበባ መነን አካባቢ ነው፡፡ እድሜዬ አስርን ሳይዘል ከቤተሰቦቼ ጋር ጥሩ ኑሮ ስንኖር ከሌሎች ዘመዶቻችን ጋር ተቀላቅለን መኖር ጀመርን፤ ያኔ ወላጆቼ ለዘመዶቻችን ጥለውኝ ሲሄዱ እኔም ከቤት ወጣሁ፤ የጎዳና ተዳዳሪ ሆንኩ፡፡ ዛሬ እድሜዬ ሰላሳዎቹ መጀመሪያ ላይ ይገኛል፡፡ አብዛኛውን እድሜዬን ያሳለፍኩት ጎዳና ላይ ነው፡፡” እያለ ስለራሱ አጫወተኝ፡፡
በአዲስ አበባ የተለያዩ ሰፈሮች፣ በባህርዳር፣ ምዕራብ ሸዋ ጎዳናዎች ብዙ ክረምትና በጋዎች ዝናብና ፀሀዩ ተፈራርቆበታል፡፡ የሌት ቁሩ የቀን ወበቁ ገርፎታል፡፡ እናም ዛሬ ከተላመደው የጎዳና ህይወት ከመውጣት ሞት የሚሻል የሚመስለው
አበራ ቀለል አድርጎ ‹‹ቀን ያገኘሁትን እሰራለሁ፤ ማታ ማታ እዚህ አድራለሁ›› በማለት የየዕለት ኑሮውን በአጭር ዓረፍተነገር ገለጸልኝ፡፡ በነአበራ ህይወት ውስጥ ማንም አብሮ ከሚኖረው የተለየ ብዙዎች ያጡትን የማፍቀርና የመፈቀር ህይወት በፍቅር ውስጥ ቢታመሙ አስታማሚ፣ ቢራቡም ቢጠግቡም የሚያወሩት የማያልቅ፣ ደስታ የማይለየው ለሌሎች ቦታ የሌለው መሆን ብዙዎች ያልታደሉት እንዲህ ባዶቤት እንዳንለው ጎዳናላይ ሲገኝ ለየት ያለ ስሜት መፍጠሩ አይቀርም፡፡
ሁለቱ ወጣቶች ስለተገናኙበት አጋጣሚ አበራ ያስታውሳል፡፡ “ አውቶቡስ ተራ ጀርባ ሰላም ጂም አካባቢ ቁጭ ብዬ መጣችና አጠገቤ ቁጭ አለች፡፡ ከዚያ ካንተ ጋ መሆን እፈልጋለሁ፤ አለችኝ ተግባባን፤ አብረን መኖር ጀመርን” ይላል፡፡ እሷም “በቃ ስለወደድኩት አብረን መኖር ጀመርን” ትላለች፡፡ የዚያ መንደር ወጣቶችም “እዚህ አካባቢ የመጡ ሰሞን ማንም ትኩረት አይሰጣቸውም ነበር፤ እየቆየ ግን እንደሌሎቹ የጎዳና ልጆች አለመሆናቸውን ስናይ በነሱ ተሳብን” ይላሉ፡፡
እሱ ማንም እንዳይነካት ጠባቂዋ ነው፡፡ የመንፈስ ጭንቀቷ አይሎ መረበሽ ስትጀምር ወደ ደረቱ አስጠግቶ ወደ ራሷ ይመልሳታል፤ አብረው ያገኙትን ተቃምሰው ተቃቅፈው ውለው ያድራሉ፡፡ ‹አንድም ቀን ከዚህ የተለየ ነገር አላየንባቸውም› ሲሉ ይናገራሉ ነጋ ጠባ የሚያዩዋቸው፡፡ እሱም “ ታሳዝነኛለች፤ ታውቂያለሽ ይቺ ልጅ ትረበሻለች፡፡ እኔ ሳባብላት ነው ዝም የምትለው፡፡ ደግሞ እወዳታለሁ” ይላል፡፡ ይህንን የተመለከቱ እውነተኛ ፍቅር ማለት ይሄ ነው አሉኝ፡፡ ከነሱ ውጭ የሆኑ የትዳርና የፍቅር ሕይወቶችን እያነሳሱ፡፡
እንደ ምሳሌ ከጠቀሱልኝ መሀል የሰሞኑን ሰርጎች ከውጥን እስከመጨረሻቸው ለተመለከተ የትዳር መሰረት የሆነውን ፍቅራቸውንም ለመዘነ በየፍርድ ቤቱም ሳይጋቡ ተፋቱ አይነት የፍቺ ጥያቄዎችን መብዛት ላየ ደግሞም የፍቺ ጥያቄ የሚቀርብባቸው ምክንያቶች ግልፅ የማይሆኑና ስስ መሆናቸውን ለሰማ የጋብቻ ትርጉም ቢደናገረው አይገርምም፡፡ ሲዘፈን እንደምንሰማው ተፅፎም እንደምናነበው የትዳር መሰረቱ ፍቅር ነው፡፡ ፍቅር ደግሞ ብዙውን ጊዜ ሳይታሰብ አንዳንዴም በመላመድ ይፈጠራል፡፡ የቱ ከልብ የሆነ የትኛው እውነተኛ ነው የሚለው በእያንዳንዱ ሰው ልብ የሚመዘን ነው፡፡
ፍቅር ሲታሰብ ምን አላት? ምን አለው? ከሚሉት ጀምሮ ከአቋም እስከ ዘሩ ከእውቀት እስከ አስተሳሰቡ ለክተው እስከሚጠብቁት ብዙዎችን አይተናል፡፡ ኑሮን ሀ ብለው ሲጀምሩም እንዲህ መሆኑን ባውቅ መች እገባበት ነበር? የሚሉት ብዙዎች ናችው፤ የሰው ባህሪ የጎደለውን መፈለግ ስለሆነ ሲይዙት ባዶ ቢመስል አይገርምም፡፡ ኑሮ ካሉት ሁለቱ ይስማሙ እንጂ የትም ቦታ በማንኛውም ሁኔታ ለመመስረቱ ብዙዎችን ስንሰማ ኖረናልና የእውነተኛ ፍቅር ምሳሌዎች ይኸው እነዚህ ተገኝተዋል፡፡ ለመገናኘትም አብሮ ለመኖርም ምክንያታቸው ፍቅራቸው ነውና ፡፡
“አንድ ቀን” አለኝ አብዲ የተባለ ወጣቶቹን የሚያውቅ የዚያ ሰፈር ወጣት፡፡ ‹‹ሀይለኛ ዝናብ እየዘነበ ወደቤት ለመግባት እየሮጥኩ ስመጣ እነሱ ግን ድንጋይ ላይ ተቃቅፈው ቁጭ ብለው ዝናቡ በላያቸው ላይ ይወርዳል፡፡ በጣም ደነገጥኩ፤ እነሱ ጋ የማይዘንብ ሁሉ መሰለኝ፡፡ ቀስ እያልኩ መራመድ ስጀምር ተመስጠው እያወሩ መሆናቸውን ልብ አልኩ፡፡ በፍቅራቸው እንደሁልጊዜው ቀናሁ፡፡ ፅናታቸውም አስገረመኝና ምነው በሞቁት ቤቶች መሀልም ይህን መሰሉ ፍቅር በሞላ አልኩ፡፡”
ሌላዋ ወይዘሮ ደግሞ በትዳር መሀል ሳይቀር የሚያጋጠሙትን እያነሳን ሁሌም እንገረምባቸዋለን አለች፡፡ ”ዛሬ ማነው የአእምሮ ህመምተኛ የሆነችኝ ሴት እንዲህ በትዕግስት ተንከባክቦ ከችግር፣ ከረሀብና ከጥማት ጋር ድንጋይ ላይ ቁጭ ብሎ እየኖረ የሚያስታምም? ከሞቀ ቤታቸው እንኳ ብዙዎች የጎደለባቸውን ፍለጋ ሲሄዱ ነው የምናየው፡፡ እነዚህ ወጣቶች ግን ሲያማት እዚሁ እያስታመመ አብረው እየኖሩ ነው፡፡ነገረ ስራቸው ሁሉ እውነት ነው፡፡ እሱም መስራት የሚችል ቆንጆ ወጣት ነው፡፡ እሷም የተማረች ቀልጣፋ ወጣት ናት፡፡ ትንሽ ህክምናና ምክር ድጋፍ ቢያገኙ ተቆርቋሪ ሀላፊነት የሚሰማው ሰው ቢያግዛቸው በቀላሉ ራሳቸውን ችለው የሚያስመሰግኑ ወጣቶች ይሆኑ ነበር” አሉኝ፡፡
እነዚህ ወጣቶች በተለይ እሷ አዲስ አበባ ጉለሌ አካባቢ አክሰቶች እንዳሏት ትናገራለች፡፡ በየጊዜው መንገድ ላይ እንደምታገኛቸው ስትነግረኝ በአካባቢው ያሉ ወጣቶች ደግሞ በአንድ ወቅት ዘመዶችዋ መጥተው የተፈጠረውን አወጉኝ ፡፡ “አንድ ቀን ሁለት አክስቶችዋ መጡ፡፡ ከዚያ ልጃችንን ይዘን መሄድ እንፈልጋለን አሉ፡፡ እና ምን እናድርግላችሁ ስንላቸው ከሱ ነጥሉልን አሉን፤ መጀመሪያ ደብቆ ያመጣት መስሎን ውሰዷት ብለን ነበር፡፡ በፍፁም እሱንና ውሻዬን ትቼ አልሄድም፡፡ ስትል የሆነ ብር ወርውረውላት ሄዱ፡፡ ከዚያ በኋላ ለበዓል እንኳን መጥተው አላዩዋትም፡፡ ስለዚህ ቢወስዷትም የሱን ያህል ስለማያስታምሟት እሱ ይሻላታል›› ይላሉ፡፡
በነበረን ጥቂት ቆይታ ስለጎዳና ህይወት አስከፊነት አበክሬ ለመናገር ብሞክርም ሀሳቤ መፍትሄ መፈለግ መሆኑ ያልገባቸው ሁለቱ ወጣቶች በጥላቻ የተመለከቱኝ መሰለኝ፡፡ እሱን ወደ ስራ እሷን ወደ ህክምና የሚወስዳቸው ቢገኝ የሚለውን የልቤን ሀሳብ ካወቁ ቢታዘቡኝ አይገርምም፡፡ እነሱ የዘወትር ፍርሀታቸው መለያየት ነውና፡፡ እናም የዛሬው ፀሀይ የመጪው ክረምት ዝናብና ጎርፍ ቢያሰጋቸውም ይኸው አሉ፡፡ ለኛ ብዙ ነገር የጎደላቸው ቢመስለንም ፍቅር ህይወታቸውን ሙሉ አድርጎላቸዋል፡፡

በእነ አቶ መላኩ ፈንታ የክስ መዝገቦች ላይ ብይን ተሰጠ

May 31/2014
የተከሳሾች መቃወሚያ ውድቅ ሆኗል


የፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት 15ኛ ወ/ችሎት የሙስና ክስ የቀረበባቸውን የቀድሞ ገቢዎችና ጉምሩክ ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታንና በሶስት መዝገቦች የተከሰሱ ሌሎች ተከሳሾችን የክስ መቃወሚያና የአቃቤ ህግን ምላሽ መርምሮ በትናንትናው እለት ብይን ሰጠ፡፡ ፍ/ቤቱ አብዛኛውን የተከሳሾችን መቃወሚያ ውድቅ አድርጓል፡፡
ፍ/ቤቱ ብይኑን ከመስጠቱ በፊት ተከሳሾቹ ያመለከቱትን የክስ መቃወሚያና የአቃቤ ህግን ምላሽ አስታውሷል፡፡
በመዝገቡ 1ኛ ተጠሪ የሆኑት አቶ መላኩ በዚህ መዝገብ በቀረቡባቸው ክሶች፤ የቀረቡብኝ ክሶች በስነ ስርአት ህጉ አንቀፆች መሰረት የተሟሉ አይደሉም፣ ከባለስልጣናት ጋር በመመሳጠር ክስ አንስተሃል ለተባልኩት ኃላፊነት የለብኝም” የሚሉና ሌሎች መቃወሚያዎችን ያስታወሰው ችሎቱ፤ አቶ ገ/ዋህድ በበኩላቸው፤ “በተነሱና በተቋረጡ ክሶች ልጠየቅ አይገባም፤ ክሶችን እንዳነሣ አዋጁም ይፈቅድልኛል፤ ከተፈቀደልኝ ወሰን በላይ ህግ አልጣስኩም” ማለታቸውን ጠቁሟል፡፡
ሌሎች በመዝገቡ የተካተቱ ተከሳሾች “የቀረበው ክስና ማስረጃ ግልፅ አይደለም፣ በተሻረ የህግ አንቀፅ ተከሰናል፣ ኮሚሽኑ በማይመለከተው ስልጣንና በሌለው ውክልና ነው የከሰሰን፣ ክሱ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ነው” የሚሉና ሌሎች በርካታ መቃወሚያዎች እንዳቀረቡም ችሎቱ አስታውሷል፡፡
ለተከሳሾቹ መቃወሚያ ከአቃቤ ህግ ከተሰጡ ምላሾች መካከልም፤ ከማስረጃና ከክስ ጭብጥ ጋር ተያይዞ የቀረቡት መቃወሚያዎች በብይን ሳይሆን በክርክር ሂደት ነው መታየት ያለባቸው የሚለው ይገኝበታል፡፡
እነ አቶ መላኩ በእርግጥም ክስ የማንሳት ስልጣን በአዋጅ እንደተሰጣቸው የጠቀሰው አቃቤ ህግ፤ ነገር ግን ተከሳሾቹ ከተፈቀደላቸው የህግ ወሰን በላይ የተሰጣቸውን መብት ተጠቅመዋል ሲል ምላሽ ሰጥቷል፡፡ ሁሉም ተከሳሾች ያቀረቡት የክስ መቃወሚያም ሙሉ ለሙሉ ውድቅ እንዲደረግለት አቃቤ ህግ የጠየቁ ሲሆን፡፡
የግራ ቀኙን መከራከሪያ ሲመረምር መቆየቱን ያስታወሰው ፍ/ቤቱም፤ በዚህ መዝገብ ላይ ክሱ መስፈርቱን አሟልቶ መቅረቡን እንዲሁም ገቢዎችና ጉምሩክ ለፀረ-ሙስና ኮሚሽን ውክልና መስጠት እንደሚችል በመግለፅ በመዝገቡ ከተጠቀሱት 93 ክሶች 90ዎቹ ባሉበት እንዲቀጥሉ ሶስቱ ተሻሽለው እንዲቀርቡ በይኗል፡፡
ፍ/ቤቱ ቀጣይ ሂደቱን ለማየት ሁሉንም መዝገቦች ለሰኔ 3 ቀን 2006 ዓ.ም ቀጥሯል፡፡

Freitag, 30. Mai 2014

ወ/ት ብርቱካን ሚዴቅሳ ተመረቀች

May 30/2014
ኢ.ኤም.ኤፍ) የቀድሞ የቅንጅት ፓርቲ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዘዳንት የነበረችው እና በኋላም በኢህ አዴግ ታስራ የተፈታችው ወ/ት ብርቱካን ሚዴቅሳ፤ ከሁለተኛው እስር ከተፈታች በኋላ፤ በ2011 ወደ አሜሪካ በመምጣት በሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ ትምህርቷን ስትከታተል ቆይታ በያዝነው ሳምንት ከሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ ተመርቃለች።
የሬገን ፋሴል ዲሞክራሲ ተቋም ወ/ት ብርቱካን ሚዴቅሳን ጨምሮ ለአቶ ስዬ አብርሃም የስኮላርሺፕ በመስጠት ትምህርታቸውን በላቀ ሁኔታ እንዲከታተሉ አድርጓል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ፕ/ር መረራ ጉዲናም የዚህ እድል ተጠቃሚ እንደሆኑ የኢ.ኤም.ኤፍ የቅርብ ምንጮች ገልጸውልናል። ወ/ት ብርቱካን ሚዴቅሳ ከተመረቀች በኋላ ወደ ፖለቲካ አለም በመግባት የመሪነት ሚናዋን እንደገና ትጫወታለች ተብሎ አይጠበቅም። አሁን ያላወቅነው ነገር ቢኖር፤ ‘ወ/ት ብርቱካን ኑሮዋን በአሜሪካ ትቀጥላለች ወይስ ወደ አገር ቤት ትመለሳለች’ የሚለው ነው። ለማንኛውም ኢ.ኤም.ኤፍ ለወ/ት ብርቱካን ሚዴቅሳ እና ለሌሎችም ተመራቂዎች እንኳን ደስ ያላቹህ በማለት ዘገባውን ያጠናቅቃል።

የቅድመ ምርጫ አፈናው በውይይት እንዲተካ እንጠይቃለን!! ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

May 30/2014

እንደሚታወቀው የግንቦት 2ዐን 23ኛ ዓመት ለማክበር ጉድ ጉድ እያለ የሚገኘው ገዥ ፓርቲ ወደ ጠቅላይ አምባገነን ፓርቲነት ከተለወጠ ብዙ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ በ1983 ዓ.ም ሀገሪቱን ከመቆጣጠራቸው በፊት በርካቶች ስለ ነፃነት፣ እኩልነት፣ ሰብአዊ መብት መከበርና ዴሞክራሲ ሥርዓት መስፈን ክቡር ህይወታቸውን እንዲገብሩ ተደርጎ በተገኘ የዜጎቻችን መስዋእትነት መንበረ ሥልጣኑን ቢጨብጡም በተግባር ዋጋ የተከፈለበትን ዓላማ ለማሳካት አልቻሉም፡፡ እንዲሁም የህዝቦችን ነፃነት በጉልበት በመቀማት፣ ሰብአዊ መብትን በመጋፋት ዴሞክራሲያዊ ሥርዓቱን ለማስመሰያነት በንድፈ ሃሳብ አስፍረው በተግባር በዜጎችዋ ግፍ በመፈፀም ነፃነውን ፕሬስ እንደጠላት በማየት፣ ተቀናቃኝ ኃይሎችንና የፖለቲካ መሪዎችን በማሰርና በማፈን፤ በነፃነት የመደራጀት መብትን በመጨፍለቅ በአጠቃላይ ፍፁም አምባገነን የሆነ ስርዓት በመዘርጋት ላይ ነው፡፡

UDJ/Andinet party logo
ሥርዓቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ የመሻሻልና የሁነቶች የመማሪያ ባህሪ ሊኖረው አልቻለም፡፡ ይልቁንም ከአብዮታዊ ዴሞክራሲ መስመር ውጭ የሆኑትን በጅምላ በመፈረጅና በተናጠል ግለሰቦችን ከፖለቲካው አውድ በማስወገድ የእድሜ ልክ ገዢ የመሆን ሕልም ውስጥ ወድቋል፡፡
ፓርቲያችን አንድነትም ለሀገራችን የሚጠቅመው ይህ ያለመቻቻልና የጥፋት ጎዳና ሳይሆን የመነጋገር፤ እንዲሁም አሸናፊ የሆነው ሃሳብ ተቀባይነት እንዲያኝና የዜጎች መብት ለስልጣን ሲባል ሳይሸራረፍ እንዲከበር በሠላማዊ ትግል አቅጣጫ መግፋት ተገቢ መሆኑን በጽናት ያምናል፡፡ የአመራር አባሎቻችንም ሳይገድሉ እየሞቱ፤ ሳይደበድቡ እየተደበደቡ፤ ሳያስሩ እያታሰሩ ለህዝቡ የሚገባው ነገር እንዲደረግ ያለመታከት እየሰሩ ይገኛሉ፡፡
አንድነት ህጋዊ መስመር በመከተልና በጠበበው የፖለቲካ ምህዳር ውስጥም ቢሆን ዓላማውንና ግቡን ፍፁም ሠላማዊና ህጋዊ በሆነ መንገድ ለህዝቡ ማድረስ የሚቻለውን ሁሉ እያደረገ እንዳለም ከማንም የተሰወረ አይደለም፡፡ በህዝቡ ዘንድ ያለው ተቀባይነትም እጅግ ጨምሯል፡፡ ነገር ግን ተቀባይነታችን በጨመረ ቁጥር በስጋት ባህር የሚዋኘው ገዢ ፓርቲ በአመራሮቻችንና አባሎቻችን ላይ እየፈፀመ ያለው ግልጽ በደልና በማናለብኝነት በጠራራ ፀሐይ ለመደብደብ የሞራል ችግር በሌለባቸው የደህንነት ሠራተኞችና ሆድ አደር ግለሰቦችን በማሰማራት እየተፈፀመ ያለው ግፍ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ቀጥሏል፡፡
ባለፉት ሁለት ሳምንታት ብቻ የፓርቲያችን ከፍተኛ አመራር የሆኑት የፖለቲካ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ሰለሞን ስዩም በጠራራ ፀሀይ ታፍነው እንቅስቃሴያቸውን የማያቆሙ ከሆነ እንደሚገደሉ የተነገራቸው ሲሆን፤ የአዲስ አበባ የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ አቶ ስንታየሁ ቸኮል በጠራራ ፀሐይ ወደቤታቸው ሲገቡ ከኋላቸው በድንጋይ ተመትተው ሲወድቁ ሞቱ ብለው ጥለዋቸው ሄደዋል፡፡ እንዲሁም የድርጅት ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ የመሀል ቀጠና አደራጅ አቶ ደረጀ ጣሰውን የማይታወቁ ግለሰቦች እንፈልግሀለን በማለት በመኪና አፍነው ለመውሰድ ትግል ሲያደርጉ ባሰሙት ጩኸት ህዝቡ ያስጣላቸው ቢሆንም አይናቸውን በቦክስ በመመታታቸው በከፍተኛ ህክምና ሊተርፉ ችለዋል፡፡ አንድነት ላይ እየተፈፀመ ያለው የአደባባይ አፈና በዚህ የሚያበቃ አይደለም፡፡ በቅርቡ አንድነትን የተቀላቀሉት አቶ አስራት አብረሃምም በኦሮሚያ ፖሊሲ ታፍነው እስካሁን ያሉበት አይታወቅም፡፡ ይህ በአዲስ አበባ አመራሮች የተፈፀመ ሲሆን ከአዲስ አበባ ውጭ ያሉ አባሎቻችን ላይ እየተፈፀመ ያለውን አፈናና እስራት ለመዘርዘር ከባድ ነው፡፡ ለአብነትም በወላይታ ሰዶ የፓርቲው ከፍተኛ አመራር በሆኑት የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ተፈራ እና ምክትል ኃላፊው አቶ ዳንኤል ሺበሺ እንዲሁም የዞኑ የምክር ቤት አባላት፣ በደሴ ከተማም በተመሳሳይ ሁኔታ በአቶ አዕምሮ አወቀ ላይ የተፈፀመው ውንብድና፣ ድብደባ እስራትና አፈና ጠቋሚ ማስረጃዎች ናቸው፡፡
በአመራሮችና አባላት ላይ ከሚፈፀመው አፈናና ክትትል በተጨማሪ የፓርቲውን ስም ለማጥፋትና ተቀባይነት ለማሳጣት አይጋ-ፎረምን የመሳሰሉ የሥርዓቱ ቀላጤ ሚዲያዎች ፀረ-ሠላም ከሚሏቸው ኃይሎችና አሸባሪ ብለው ከፈረጁአቸው አካላት ጋር ግንኙነት እንዳለን የሚያስመስል የልቦለድ ዘመቻ ከፍተዋል፡፡ ይሄ ሁሉ የሚያሳየው ፓርቲያችን ጠንክሮ መውጣቱን ሲሆን ከዚህ በኋላ በአፈና፣ በድብደባና በእስር እንዲሁም በፍረጃ አንድነትን ወደ ኋላ መመለስ እንደማይችል ለማረጋገጥም እንወዳለን፡፡
ይልቁንም ገዢው ፓርቲ ካለፈው ስህተቱ በመማር፣ ከስለላ፣ ከፍረጃና ከአፈና በመላቀቅ ወደ ውይይት እንዲምጣ አሁንም ጥሪ እናቀርባለን፡፡ ይህ ሳይሆን ቀርቶ በአፈናና በጉልበት አሁንም ቀጣዩን ምርጫ ለመቀልበስ መሯሯጥ ባለዕዳ የሚያደርገው ገዢውን አካል መሆኑን ለማስገንዘብም እንወዳለን፡፡
የ23ት አመቱ የግንቦት 2ዐ ፍሬ ተብሎ ሊጠቀስ የሚችል ቢኖር ይህ አስከፊ ስርዓት ያነበረው ጭቆናና በደል እስር እንግልትና በተጽእኖ ከሀገር መሰደድ ከሦስት ሺ ዓመታት በላይ የተገነባው አብሮነት አደጋ ላይ መውደቁ ተጠቃሽ ሊሆን ይችላል፡፡ የነፃነት ቀን ነው በሚሉት በግንቦት 2ዐ ዋዜማ እንኳ የዞን 9 ጦማሪዎች በማእከላዊ መከራ እየተቀበሉ ሲሆን የእስር እርምጃው ቀጥሎ ደራሲ አስራት አብርሃም ታፍኖ ከመሰወሩ ባሻገር የዕንቁ መጽሔት ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ በተጨማሪ ወደ እስር ተግዟል፡፡ ይህም የግንቦት 2ዐ ፍሬ መሆኑ ነው፡፡
ምን አልባትም ሥርዓቱ የምርጫ 97 ሽንፈትን ተከትሎ በግብታዊነት ወደ መሰረተ ልማት ማስፋፋት በማተኮር አንዳንድ ቁሳዊ ልማት ለማሳየት ቢጣደፍም ማህበራዊ ልማትን ቀብሮ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብትን እረግጦ፤ ልማት አስመዝግቤአለሁ እያሉ አገዛዝን በኃይል ለማስቀጠል መሞከር የከፋ አደጋ ሊያስከትል እንደሚችል መገንዘብ ይገባል፡፡
በመጨረሻም ፓርቲያችን ዛሬም የዚችን ሀገር ዘርፈ ብዙ ችግር በኃይል ለማዳፈን ከመሞከር ወደ ውይይት እና ብሔራዊ መግባባት ማዘንበል ጠቃሚ መሆኑን አበክሮ ይገልፃል፡፡
ድል የሕዝብ ነው!!
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
ግንቦት 19 ቀን 2ዐዐ6 ዓም
አዲስ አበባ

40 – 23 የኢህአዴግ የጎሳና የመጥበብ ሰረገላ ሐዲዱ ላይ ነውን?

May 30/2014

“ኢትዮጵያን በጎሳ ሳጥን ቆልፎ የሚጓዘው ህወሃትና ድግሱ”

40 - 23


ህወሃት በነጻ አውጪ ስም ታግሎ ኢትዮጵያን መግዛት የጀመረበትን 23ኛ ዓመት በዓሉን እያከበረ ነው። ወዳጆቹና መሪዎቹ ባስቀመጡት እቅድ መሰረት ኢትዮጵያን “በመተካካትና በተሃድሶ” ስም ራሱን እያገላበጠ ለመግዛት የቆረጠው ጊዜ በትንሹ 40 ዓመታት እንደሆነ ይታወቃል። አሁን ባለው የሰረገላው ጉዞ ኢህአዴግ ከ40 – 23 ከመቀነሱ ውጪ አሰበበት ስለመድረሱ መገመት የሚያስችል ምልክት የለም። እንደውም ስጋት እንጂ።
ሲጀመር “የገበሬ ተሟጋች” ነኝ በማለት ራሱን የአርሶ አደሩ ወኪል አድርጎ የተነሳው ህወሃት፣ ኢህአዴግ ሆኖ አገር መግዛት ሲጀምር ያስቀደመው የብሄር ብሄረሰቦችን የመብት ጥያቄ እንደ ውዳሴ ጸሎት በመደጋገም ነበር። በዚሁ በጎሳ ላይ ተመስርቶ በቋንቋ የተቆለፈው የአገዛዝ ስልት ሲጀመር ማስጠንቀቂያ የሰጡ፣ ለመታገል የሞከሩ፣ የታገሉ፣ ያስተባበሩ፣ ያደራጁ የህወሃት የ40 ዓመት ጉዞ ጸር ተደርገው ተወሰዱ። ስለ ኢትዮጵያ ጥቅምና ኢትዮጵያዊነት ያሳሰቡ ጠላት ተደርገው ተፈረጁ። በስውር በአፈና፣ በግልጽ ህግ እየተጠቀሰባቸው ከጫወታና ከመኖር ተገለሉ። ብዙዎች እንደሚሉት “የጉዳቱን መጠን ህወሃትና የተጎዱት ቤተሰቦች ይቁጠሩት”!
ግንቦት ሃያ “የህዝብ የድል ክቡር ቀን ነው” በሚሉና “የህዝብና የአገር ውድቀት የታወጀበት የክፉ ቀኖች ሁሉ ድምር” ሲሉ በሚሰይሙት መካከል ሰፊ መከራከሪያ አለ። የመንገድ ግንባታ፣ የህንጻ ግንባታ፣ የኮሌጅና የትምህርት ቤቶች ግንባታ፣ የግድቦች ግንባታና የአባይ ወንዝ ልማት ወዘተ ጉዳዮች የግንቦት 20 ጣፋጭ ፍሬዎች ስለመሆናቸው “የቀኑ ወዳጆች” ይከራከራሉ። የቀኑ “ባሮችም” ይህንኑ ውዳሴ በማቀንቀን ታማኝነታቸውን ይገልጻሉ። በጥቅም የተደለሉ ሎሌዎች ስለሆኑ ይህንን ድል ለማስጠበቅ በግልጽና በህቡዕ አድርጉ የተባሉትን ያደርጋሉ።
በተጠቀሱት የልማት ስራዎች ላይ ተቃውሞ የማያነሱ የቀኑ “ሰለባዎች” ሰላምና መረጋጋት እንዳለ የሚሰብክ አስተዳደር ልማትን ከመስራት ሌላ ተግባር እንደሌለው ይገልጻሉ። አያይዘውም ጣሊያንም በ5 ዓመት ጊዜ ውስጥ በርካታ መንገድና ድልድዮችን መገንባቱን ያጣቅሳሉ። ከሁሉም በላይ ግን ኢህአዴግ በሚገዛት አገርና ሕዝብ ስም የተበደረውን የገንዘብ መጠን “ከተዘረፈው ውጪ” በማለት ከፍተኛ እንደሆነ ይናገራሉ። በሌላ በኩል ደግሞ “መንገድ መስራትና ህንጻ ማቆም የመብት ጥያቄን በጥይት ለመመለስና በደም ለመጨማለቅ ዋስትና ሊሆን አይችልም” በማለት ስርዓቱን አጥብቀው ይኮንኑታል።
በሌላም ወገን የተሰሩትን ህንጻዎች፣ የንግድ ተቋማት፣ የገንዘብ ተቋማት፣ ከፍተኛ ኢንቨስትመንቶች በማንሳት “የግንቦት 20 ፍሬዎች” ሲሉ ይሰይሟቸዋል። ሲያብራሩም “የነዚህ ሁሉ ሃብቶች መነሻና ባለቤቶች ህወሃትና ህወሃት ዙሪያ የሚሽከረከሩ ባለሟሎች ናቸው። የህዝብ አይደሉም። ሕዝብም አያምንባቸውም” በማለት ጥርስ ይነክሱባቸዋል። በዝርፊያ ሃብት የሚያግበሰብሰውን ኤፈርት ኢትዮጵያን “ንብረቶችሽን ባደራ ላስቀምጥ” የሚል እስከሚመስል የንግድ ኢምፓየሩን ማስፋቱን አብዝተው ይኮንናሉ።
የግንቦት 20፣ የቀኑ ወዳጆች ኤፈርት ላይ የሚቀርበውን ጥያቄ አያስተባብሉትም። ይልቁኑም ድርጅቱ ጓዳና ካዝናው የተለጎመ መሆኑ ያብከነክናቸዋል። አለው የሚባለው ሃብት ሁሉ የትኛው ቋት እንደሚቀበር ስለማይረዱ “የተሸውደናል” ስሜት አላቸው። ለዚህም ይመስላል የህወሃት ወዳጆች “ኤፈርትን ያየህ ወዲህ በለኝ” ሲሉ የሚደመጡት። በግልጽ አነጋገር ኤፈርት ፊት ለፊት ከሚያሳየው ሃብቱ ይልቅ፣ የማይታው ጉዱ ስለሚያመዝን በህወሃት ወዳጆች ሳይቀር አልሞ ተኳሽ (ስናይፐር) የተደቀነበት ነው።
አፈናው፣ ግድያው፣ እስሩ፣ ዝርፊያው፣ ከላይ ከተገለጸው በተቃራኒ አርሶ አደሩ ላይ የሚፈጸመው የመሬት ቅሚያ ሌላው የግንቦት 20 የጨነገፈ ፍሬ ተደርጎ ይወሰዳል የሚሉ አሉ። በተለይም ራሱ ህወሃት ሁሉንም በራሱ ደረጃ ለማሳነስ ሲል ያዋቀረው የቋንቋና ጎሳን ተገን ያደረገ የአገዛዝ ስልት ዛሬ ግንቦት 20ን እድሜውን ወደ ማሳጠር እያደረሱት ነው ሲሉ ያክላሉ። በዚህ አስተሳሰብ ላይ የሚተቹ ሰሞኑን አጠንክረው እንደገለጸት “የግንቦት 20 ወዳጆች ኢትዮጵያዊነት ከውስጣቸው እንዲወልቅ ተደርጎ በተዘጋጀላቸው የትምህርት እቅድ፣ ሥርዓተ ትምህርት፣ … መሰረት ወደ ጎሳ እየጠበቡ የግንቦት 20 ድል ‘ሰረገላው’ መድረስ የፈለገበት ቦታ ሳደርስ ሃዲዱን ሊያወላልቀው ይችላል”፡፡
40 – 23 ዓመት ላይ ያለው ኢህአዴግ ህወሃትን እያጀበና እየሞሸረ ወደ “መንገሻው” ለማድረስ የተሰሩበት የጎሳ ኬሚስትሪ እንደሚከለክላቸው የሚናገሩ ክፍሎች “የግንቦት 20 ድል እየተከበረ 40 ዓመት መዝለቅ ምናልባትም ከተረትም የወረደ ሟርት ነው” ባይ ናቸው። ህወሃት ለጊዜው ብሎ የዘራው የበቀል ዘርና በጎሳ ሳጥን ውስጥ ከቶ ያሳደጋቸው ወዳጆቹና በጊዜ የታሰረ ቦንብ እንደሚሆኑበት ምልክቶቹ ከበቂ በላይ እንደሆኑም ይናገራሉ። እነዚህ ወገኖች እንደሚሉት “ህወሃትን የሚበሉት ራሱ ያመረታቸው ፈንጂዎቹ ናቸው” በመሆኑም የዘንድሮው ግንቦት 20 አንጸባራቂ ጥቅስ “ለመጥበብ ብሎ ህወሃት የወጠነው የጎሳ መዋቅርና አስተምህሮት የህወሃት ፉርጎ የሚሄድበትን ሃዲድ እያወላለቀው ነው” የሚለው ይሆናል – “ጉድጓድ የሚምስ ራሱ ይወቅድበታልና”፡፡

ዓባይ እንደዋዛ፤ ግድቡን ከጥላቻ አንጻር ማየት አደገኛ ነው (ዶ/ር አክሎግ ቢራራ፣ ክፍል አራት)

May 29, 2014

አክሎግ ቢራራ ዶ/ር (ክፍል አራት)

Click here for PDF

የዚህ ተከታታይ ፅሁፍ መሰረታዊ ሃሳብና ትንተና፤ ኢትዮጵያ ዓባይንና ሌሎች ወንዞቿን የራሷን ኢኪኖሚ ዘመናዊነት፤ ለሕዝቧ የምግብ ዋስትና ስኬታማነት፤ እያደገ ለሄደው ወጣት ትውልድ የስራ እድል የመፍጠር ወዘተ መብት ያላት መሆኑን የሚያጠናክር ነው። The Nile is African and Ethiopia is its hub በሚል አርእስት ለአለጀዚራ ያቀረብኩት ፅሁፍ ይኼን ይገባኛልነት በማስረጃ ተደግፎ ያሳያል። በአረብኛ የተተረጎመው ትንተና የብዙ አንባቢዎችን አስተሳሰብ እንደቀሰቀሰ ሰምቻለሁ፤ አሉታዊና ነቀፋ ያለበት ትችት አልደረሰኝም። የኢትዮጵያን ይገባኛልነት ሌሎች የጥቁር አፍሪካ ተፋሰስ አገሮች እንደሚደግፉም አሳይቻለሁ።
አከራካሪ ሆኖ ያየሁትና በተከታታይ ለመተንተን የሞከርኩት የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅምና ይገባኛልነት ከጥያቄ ውስጥ ለማስገባት አይደለም፤ ለማጠናከር ነው። ገዢውን ፓርቲ መቃወምና የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም መደገፍ የተለያዩ ነገሮች መሆናቸውን አሳይቻለሁ። የኢትዮጵያ ይገባኛልነት፤ ዘላቂ ጥቅምና ደህንነት ከጥያቄ ውስጥ መግባትና ለፖለቲካ መንደርደሪያና መጠቀሚያ ሊሆን አይገባውም እላለሁ። ኢትዮጵያ የባህር በሯን አጥታ ዓባይንም ማጣት ለተከታታይ ትውልድ በደል ነው። ለማስታወስ አፄ ኃይለሥላሴና ደርግ ለማልማት የሞከሩትን ዓባይ ዛሬ እድል ተገኝቶ የተሃድሶ ግድብ ስራ መጀመሩ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚፈልገው ሂደት የተገኘ ነው። ሕዝቡ በመንፈሱም፤ በጉልበቱም፤ በገንዘቡም እንደሚደግፈው እንሰማለን። ለኢንቬስትመንቱ የሚፈሰው ኃብት የህወሓት/ኢህአዴግ የግል ኃብት አይደለም። የኢትዮጵያ ሕዝብ ኃብት ነው። ጥቅሙም ለኢትዮጵያ ሕዝብ መሆን አለበት።Ethiopia's dam on Abbay/Nile river
የዚህ ትንተና መሰረት እንደ ተሃድሶ ግድብ ያለ የኢኮኖሚና የሃግር ጥንክርና ለማስገኘት የሚያስችል ፕሮጀክት ከፖለቲካው ፍትሃዊነትና ከሃብት ስርጭት ሚዛናዊነት ተለይቶ ሊታይ አይችልም የሚል ነው። ይክ ከሆነ የግድቡ ጥቅም ለገዢው ቡድን ብቻ መዋሉ አይቀርም። የህወሓት መስራቾችና መሪዎች ለጥቂቶች ጥቅም “ስልጣን ወይም ሞት” ብለው በኢትዮጵያና በኢትዮጵያውያን ላይ የጫኑት አደገኛ የከፋፍለህ ግዛው የአገዛዝ ስርዓት ዛሬ ወደ ከፍተኛ አደጋ እያመራ ነው። የተሃድሶ ግድብ ቢሰራም ባይሰራም አሁን ያለውን ቀውስ ሊፈታውና ሊገታው አይችልም። ከጅምሩ ስርዓቱ በማይታረቁ የብሄር፤ ብሄረሰብና ሕዝቦች ልዩነቶች፤ የተፈጥሮ ኃብትን ለተወሰነ ቡድን ባለቤትነት በማሸጋገር፤ ይኼን ስኬታማ ለማድረግ መብቶችን በማፈን ወዘተ ላይ የተመሰረተ ነው። ሕዝብ ከሕዝብ እየለያዩ፤ መሬትን ቆራርሶ ለጥቂቶች ጥቅም እያስተላለፉ፤ ህወሓት በዋና ጠላትነት የፈረጃቸውን ከመሬትና ከሃብታቸው እያስለቀቀና እያደኼየ፤ ሰላምና እርጋታ ለመፍጠር አይቻልም። የስርዓቱ አገልጋይነት ለጭቁኖች መብትና የኑሮ መሻሻል አለመሆኑ በይፋ ሲከሰት ቆይቷል። የኦሞ ሸለቆን፤ የጋምቤላን፤ የቤኒ ሻንጉል ጉሙዝን፤ የአፋርን፤ የኦጋዴንን “ጭቁን” ሕዝብ ከጢቂቶቹ አዲስ ባለኃብቶች ጋር ብናነጻጽር ህወሓትና ደጋፊዎቹ ለማን ጥቅም እንደቆሙ ለማየት አንቸገርም። የጥቂቶች ስልጣን ሊቆይ የቻለውና የሚቆየው የእርስ በርስ ጥላቻንና ግጭትን በማቀጣጠል፤ ሰብአዊ መብቶችን ፍፁም በሆነ መንገድ በማፈን፤ በተለይ የአማራውንና የኦሮሞውን ሕዝብ በማጋጨት፤ እልቂት እንዲስፋፋ በማድረግ፤ አብሮ በመስራትና አብሮ ችግሮቾን በመፍታት ፋንታ ህብረተሰቡን በማራራቅ፤ ባጭሩ በውይይትና በዘዴ ሰላምና እርቅ ስኬታማ እንዳይሆን በማድረግ ነው። ታዛቢዎች አስቸጋሪ ሆኖ ያገኙት አንዳንድ ለፍትህና ለዲሞክራሲ የቆሙ ስብስቦች የህወሓትን የጥላቻ ፈለግ ተከትለው ከሳቱ ላይ ቤንዚን መጨመራቸው ነው። ዙሮ ዙሮ የጥላቻ ፖለቲካ የሚረዳው የሚቃወሙትን ህወሓትን መሆኑን ዋጋ አልሰጡትም። ጥላቻን በጥላቻ፤ እልቂትን በእልቂት፤ አፈናን በአፈና፤ የቂም በቀልን በቂም በቀል ወዘተ የሚተካ ወይንም እነዚህን የመሰሉ የፖለቲካ ባህሎችና ልምዶች የሚያጠናክር ስብሰብ ወይንም ግለሰብ “ለቆመለት ሕዝብ” እውነተኛ አገልጋይ መሆኑ ያጠራጥራል። ህወሓት የሚፈልገውን የሚያደርግ መሆኑ ግን አያከራክርም። ለፍትህና ለእውነተኛ እኩልነት መቆምና የብሄር፤ ብሄረሰብ፤ ኃይማኖት ጥላቻን ማራገብ ሰማይና መሬት ናቸው። አይገናኙም። [ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]

Donnerstag, 29. Mai 2014

አንድ መቶ ሺሕ ዶላር ለማግኘት ያሰቡ ግለሰቦች ሁለት ሚሊዮን ብር መዘረፋቸው ተጠቆመ

May 29/2014
በአዲስ አበባ ከተማ ኢትዮጵያ ሆቴል አካባቢ በሕገወጥ መንገድ የውጭ አገር ገንዘቦችን የሚዘረዝሩ ግለሰቦች፣ አንድ መቶ ሺሕ ዶላር ለማግኘት የማያውቋቸው ግለሰቦች ዘንድ ሄደው ሁለት ሚሊዮን ብር መዘረፋቸው ተጠቆመ፡፡
በዕለተ ሰንበት እሑድ ግንቦት 17 ቀን 2006 ዓ.ም. የስልክ ጥሪ የደረሳቸው ግለሰቦች ስለሚያገኙት ሥራና ትርፍ እንጂ ሊገጥማቸው ስለሚችለው ችግር አለማሰባቸውን የገለጹት ምንጮች፣ በደረሳቸው የስልክ ጥሪ ‹‹አንድ መቶ ሺሕ ዶላር አለን›› ያሏቸው ግለሰቦችን ማንነት ሳይሆን፣ የሚገኙበትን ሥፍራ ብቻ መጠየቃቸውን አውስተዋል፡፡
በእጃቸው አንድ መቶ ሺሕ ዶላር ቀርቶ ምንም ነገር ያልያዙት ግለሰቦች ያሉበትን ቦታና የያዙትን የተሽከርካሪ ዓይነት ሲነግሯቸው፣ ተዘራፊዎቹ ግለሰቦች ሁለት ሚሊዮን ብር ይዘው ለመድረስ ጊዜ እንዳልፈጀባቸው ምንጮች ገልጸዋል፡፡
ሁለት ሚሊዮን ብር ተሸክመው አንድ መቶ ሺሕ ዶላር ለመግዛት የሄዱት ግለሰቦች የጠበቃቸው አንድ መቶ ሺሕ ዶላር ሳይሆን መሣሪያና ከፍተኛ ማስፈራሪያ በመሆኑ፣ ምንም ሳያንገራግሩ ሁለት ሚሊዮን ብራቸውን እንዳስረከቡ ምንጮቹ ጠቁመዋል፡፡
የደረሰባቸውን ተጨማሪ በደል መግለጽ ያልፈለጉት ተዘራፊዎች፣ የተንቀሳቀሱበት ጉዳይ ሕገወጥ ቢሆንም ገንዘቡ ሁለት ሚሊዮን ብር በመሆኑ ያዋጣናል ወዳሉትና የመጀመሪያው የሕግ ማስከበሪያ ቦታ ወደሆነው ፖሊስ ማምራታቸውን ምንጮች ተናግረዋል፡፡
የሆኑትን ሁሉ ለፖሊስ ቃላቸውን የሰጡት ተዘራፊዎቹ፣ የዘራፊዎቹን አጠቃላይ ሁኔታ እንዲገልጹ በፖሊስ ሲጠየቁ፣ መሣሪያ የያዙና ፈርጣማ አቋም ያላቸው መሆናቸውን  በዝርዝር ማስረዳታቸውን ምንጮች አክለዋል፡፡
ጉዳዩን ይዞ ሁለት ሚሊዮን ብር ዘርፈው የጠፉትን ግለሰቦች እያፈላለገ ነው የተባለውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኃላፊዎችን ለማግኘት ተደጋጋሚ ጥረት ቢደረግም ምላሽ ለማግኘት አልተቻለም፡፡

በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ ድንበር ላይ አልሸባብ ባደረሰው ጥቃት 40 ያህል ሰዎች ተገደሉ ተባለ፡፡

M
አልሸባል ጥቃቱን ያደረሰው በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ ድንበር ላይ በምትገኝ አንድ መንደር ላይ መሆኑን ዘገባዎች አመላክተዋል፡፡
የሶማሊያ የባኮ ክልል አስተዳዳሪ ሙሃመድ አብዱል ታል ለቪኦቬ እንዳሉት ኮሆነ 27 የመንግስት ሚሊሻዎችን እና 12 የአልሸባብ ተዋጊውች ሞተዋል፡፡
አስተዳዳሪው አክለውም የአልሸባብ ጥቃት በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ ድንበር አካባቢ በነበሩ የጸጥታ ሃይሎች በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል፡፡
አልሸባብ በአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ሃይል ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት ቢሆንም አሁንም የአካባቢው የጸጥታ ችግር መሆኑ በዘገባው ተመልክቷ፡፡
The governor of Somalia’s Bakool region, Mohamed Abdi Tall, told VOA that the Islamist militant group raided the village of
Aato early Tuesday.
He said 27 pro-government militiamen and 12 al-Shabab fighters were killed in the ensuing clash.
Afterward, the town remained in control of the militias, who have been working with governments on both sides of the border
Al-Qaida-linked Al-Shabab has lost most of the territory it once controlled in Somalia but remains a threat to the country’s African
Union-backed government.
On Saturday, al-Shabab fighters stormed Somalia’s parliament building in Mogadishu, killing 10 security personnel and wounding
four lawmakers. Eight militants were also killed.
In February, al-Shabab attacked the presidential palace. The president was unharmed but at least 17 other people were killed.
Source VOA

በደብረማርቆስ ከተማ ከ400 በላይ ቤቶች በዶዘር እየፈረሱ ነው

May 29/2014


በዛሬው ዕለት ደብረ ማርቆስ ከተማ ውስጥ ህገ ወጥ ናቸው የተባሉ ቤቶች በዶዘር እየፈረሱ እንደሚገኙ ከቦታው የደረሰን መረጃይጠቁማል፡፡ በተለይ ቦሌ እየተባለ የሚጠራው ሰፈር የሚገኙ ቤቶች በዛሬው ዕለት እየፈረሰ እንደሚገኝና ህዝብ ይቃወማልበሚል ቡችሌ፣ ሚሊሻ፣ ህዝባዊና ልዩ ፖሊስ ከፍተኛ ጥበቃ እያደረገ እንደሚገኝ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ተናግረዋል፡፡(ደብረማርቆስ ከተማ)ይህ ቦሌ ተብሎ የሚጠራው ሰፈር ትናንት ሊፈርስ የነበረ ቢሆንም በግንቦት 20 ምክንያት እንደታለፈ ተገልጾአል፡፡

ደብረ ማርቆስ ውስጥ ቤቶችን ማፍረስ የተጀመረው ግንቦት 18ና 19/2006 ዓ.ም ሲሆን ቀበሌ አራት (4) በተለይም ሞንቃተብሎ በሚጠራው ሰፈር 400 ያህል ቤቶች እንደፈረሱ ታውቋል፡፡ በተመሳሳይ ቦሌ የተባለው ሰፈር እንዳይፈርስ በተደረገበትበትናንትናው ቀን ከ23 አመት በላይ ግብር ሲከፈልበት የኖረ የአንድ ግለሰብ ቤት መፍረሱም ታውቋል፡፡

 አፍራሽ ግብረሃይሉየቤቱን ጣራ ካፈረሰ በኋላ ግለሰቡ ለ23 ዓመት ግብር ሲከፍልበት የነበረ መሆኑንበመገለጹግድግዳው ብቻ እንደቆመ ወደአቤቱታ መመራቱን ምንጮች ጨምረው ገልጸዋል፡፡

ደብረ ማርቆስ ውስጥ አብዛኛዎቹ ቤቶች ከ1997 ጀምሮ የተሰሩ ሲሆኑ አብዛኛዎቹ ቤቶች አርሶ አደሮች በአሁኑ ወቅት ወደከተማ በተከለለው መሬታቸው ላይ የሰሯቸው እንደሆኑ ታውቋል፡፡ ‹‹የአርሶ አደሮቹ መሬቶች ወደ ከተማ ሲከለሉ መንግስትተለዋጭ ወይንም ካሳ የመስጠት ግዴት የነበረበት ቢሆንም በአሁኑ ወቅት በህገ ወጥነት እያፈረሰ እያፈረሰ ይገኛል›› ያሉት አንድየከተማዋ ነዋሪ እርምጃው ህገ ወጥ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

መደመጥ ያለበት ዉይይት ከኦሮሞ ምሁራን ጋር (ከአሜሪካን ድምጽ ራዲዮ የተገኘ)

May 29/2014
አሁን በኢትዮጵያ ባለው በቋንቋ ላይ ብቻ የተመሰረተ፣ የብሄረሰብ ፌዴራል አወቃቀርን በተመለተ ከሶስት የኦሮሞ ምሁራን ጋር የአሜሪካን ድምጽ ራዲዮ ያደረገው
መደመጥ ያለበት ዉይይት !
 http://www.abugidainfo.com/amharic/index.php/14673

የመብት ረገጣውንና የከፋፋዮችን ሤራ በጋራ እናስወግድ! የIትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ)

May 28/2014
Ethiopian People's Congress for United Struggle (Shengo)
www.ethioshengo.org     shengo.derbiaber@gmail.com
ግንቦት 19፣ 2006 (ሜይ 27፣ 2014)
በሀገራችን ውስጥ ሀሳቡን በነፃ ለመግለጽ የሚሞክር ሁሉ ከገዥው ቡድን የሚሰጠው ምላሽ
የሚያነሳውን ጥያቄ በመመርመር፣ የደረሰበትን ብሶት በማዳመጥ ሰላማዊ መፍትሄ ከመሻት
ይልቅ ድብደባ፣  Eሥራት፣ ስቃይና ግድያ  Eንደሆነ የሚታወቅ ነው።    ይህ ለሃያ ሦስት
ዓመታት ሳያባራ የቀጠለው የግፍ ተግባር  Eነሆ በቅርቡ በAምቦ፤ በነቀምት፤ በጊምቢና
በሌሎቹም የሀገራችን ክፍሎች ውስጥ በዘግናኝ መልኩ ተደግሟል።    ጨካኙ
የህወሓት/IህAዴግ Aገዛዛ በሥርዓቱ ፖሊሲ ላይ ተቃውሟቸውን ለማሰማት ሰላማዊ ሰልፍ
ያካሄዱ ተማሪዎችን፣ ከAሁን በፊት በጎንደር፣ በAዋሳ፣ በAዲስ  Aበባና በሌሎች ቦታዎች
Eንዳደረገው፣ ዛሬም በጥይት ደብድቦ ብዙዎችን ገድሏል፤ ሌሎችንም Aቁስሏል።  
ደግመን ደጋግመን Eንደገለጽነው፤ ይህ ሰብዓዊ ርህራሄ የጎደለው ተግባር በIትዮጵያውያን
ሁሉ መወገዝ Aለበት።  በሀገራችን ምድር ውስጥ በፍጹም Eንዳይደገምም ሁሉም ተባብሮ
ሊነሳና Aምቢ፤ በቃ ሊል ይገባዋል። ይህን ዓይነት Aስከፊ ወንጀል የፈጸሙ ሁሉ ለፍርድ
መቅረብ ይኖርባቸዋል።
Aገዛዙና በግድያው የተሳተፉት ሁሉ ሊገነዘቡት የሚገባው ነገር ቢኖር የዚህ ዓይነት
ጭፍጨፋና መንግሥታዊ ሽብርተኝነት የሕዝብን ብሶት  Aባብሶ፣ ሰሜቱን  Eንዲሸፍት
Eንደሚያደርገው Eንጂ Aፍኖ ማጥፋት  በፍጹም Eንደማይቻል ነው።  የሕዝብን ተቃውሞ
በጉልበት ማጥፋት የሚቻል ቢሆን ኖሩ ለ23  ዓመታት የተካሄደው ማለቂያ የሌለው ግፍ
ሕዝቡን ሰጥለጥ Eንዲል ባደረገው ነበር።
በሀገራችን ውስጥ ያለውን Eውነታ በትክክል መረዳት ለሚፈልግ ሰው የገዥው ቡድን የግፍ
ተግባር  Eየከፋ በሄደ ቁጥር የሕዝቡም  Eምቢኝ ባይነት  Eየጠነከረና  Eየተስፋፋ መሆኑን
በቀላሉ ማየት ይችላል።
ህወሓት/IህAዴግ በሥልጣን ላይ ለመቆየት የመብት ረገጣ ብቻ ሳይሆን ሕዝባችንንም
Eርስበርሱ በጥርጣሬና በጠላትነት  Eንዲተያይ  Aንዲሁም የAንዱ ቋንቋ ተናጋሪ የሌላው
ቋንቋ ተናጋሪ፤ የAንዱ ሃይማኖት Eምነት ተከታይ የሌላው ሃይማኖት Eምነት ተከታይ
ጠላት  Eንደሆነ  Aድርጎ የሚያራመደው የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ የሀገራችን ችግር መንስዔ
መሆኑን በገልጽ መረዳት ይቻላል።
Aገዛዙ ሲያራምደው የቆየው የሃያ ሦስት ዓመት ከፋፋይ ፖሊሲው በAሁኑ ወቅት  Aስከፊ
ገጽታው በተለያየ መልክ በመገለጥ ላይ ነው።    ዜጎች በፍቅርና በሰላም ተከባብረው
  Tel: 44 7937600756 , +1 9168486790  E-mail : shengo.derbiaber@gmail.com ተረዳድተውና  Aንድ ሆነው መኖር ሲገባቸው    Eርስበርስ  Eንዲጋጩ  Eየተደረገ ነው።
Aንዱ  Iትዮጵያዊ ሌላውን ከAካባቢው ለቅቆ  Eንዲሄድ የማስጨነቅ፣ የማሰፈራራት
የማስገደድ ተግባሮች ከቀን ወደቀን Eጅግ Aሳሳቢ በሆነ መልኩ Eየተካሄደ ይገኛል።
የተለያዩ መረጃዎች  Eንደሚያሳዩት ይህ ተግባር የሚፈጸመው በAብዛኛው ባለሥልጣኖችና
ካድሬዎቻቸው  Aማካኝነት ነው።    ለምሳሌ ከጉራፈርዳና ከሌሎችም የቤነሻንጉል  Aካባቢ
በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች  Eንዲባረሩ የተደረገው፡ በAካባቢው ከፍተኛ ባለሥልጣኖች
ትEዛዝ ነው።    ከጥቂት ዓመታት በፊት ከወለጋ ንብረታቸውን ተነጥቀው በጉልበት
ተፈናቅለው የተባረሩት በሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችንም ግፍ የተፈጸመባቸው በAገዛዙ
ባለሟሎች  Aጋፋሪነት    ነበር።   ይህ የAንዱን ቋንቋ ተናጋሪ  Iትዮጵያዊ የሌላው ጠላት
Eንዲሆን፤ የAንዱን ኅብረተሰብ ክፍል ጥቅም ለማስጠበቅ ሌላውን ማግለል  Eንደሚገባው
በሚያደርግ ከፋፋይና  Aርቆ  Aሳቢነት የጎደለው  Aመለካከት በፈጠረው  Aጥፊ ሁኔታ
ተጠቅመው የAገዛዙ ባላሟሎች ብቻ ሳይሆኑ ጠባብ ብሄረተኞችም በሕዝባችን ውስጥ
Aለመተማመን፣ ጥርጣሬና መርዘኛ ክፍፍል ለመንዛት መሞከራቸው  Aልቀረም።   በቅርቡ
በAንዳንድ ቦታዎች የተከሰቱት ሁኔታዎች  የሚያመለክቱትም ይህንኑ ነው።
ዓይኑን ጨፍኖ በክህደት ውስጥ የሚገኘውና የከፋፋይነትን መርዝ የዘራው
የህወሓት/IህAዴግ Aገዛዝ ግን በሀገሪቱ ውስጥ ሰላም Eንደሰፈነ ብቻ ሳይሆን ሁሉም ነገር
ተንበሽብሾ ሕዝቡም የደስታ ኑሮ  Eየኖረ  Eንደሆነ ሊነግረን ይሞክራል። ሃቁ ግን
የተገላቢጦሽ በመሆኑ በሀሰት ፕሮፖጋንዳ ራስን ለማታለል ካልሆነ በስተቀር ሕዝብን
መሽንገል Eንደማይቻል ግልጽ መሆን Aለበት።
ሕዝባችን መሠረታዊ በሰላም የመኖር መብቱን ከተገፈፈ ቆይቷል። የህልውና ዋስትናውን
Aጥቷል። በሰላም ገብቶ የመውጣት፣ ውሎ የማደር መብትና ዋስትና ሊያገኝ  Aልቻለም።
ይህ  Aደገኛ ሁኔታ በዚሁ ከቀጠለ ሀገራችንንም ሆነ ሕዝባችንን  Eጅግ ዘግናኝ ሁኔታ
ይጠብቃቸዋልና ዛሬውኑ  Eንዲቆም የምንችለውን ሁሉ ማድረግ  Aለብን።    ከዚህ ዓይነቱ
የርስበርስ ጥላቻና ግጭት የሚጠቀም ማንም Eንደማይኖር መረዳት ያስፈልጋል።  
በIትዮጵያችን ውስጥ በሁሉም ላይ  Aስከፊ የመብት ረገጣ  Eየተካሄደና የሕዝባችንም
ስቃይ ከጊዜ ወደ ጊዜ  Eየከፋ ነው።    በመሆኑም የሀገራችንን ችግር ለመፍታት የትግል
ትኩረታችን ከፋፋዩንና ጨቋኑን የህወሓት/IህAዴግ የግፍ  Aገዛዝ በጋራ  Aስወግደን
በምትኩ  Aንድነቷ በተጠበቀ ዴሞክራሲያዊት  Iትዮጵያ ውስጥ ሁሉንም ዜጋ በEኩልነት
የምታስተናግድ ዴሞክራሲያዊና ህገ-መንግሥታዊ ሥርዓት የሚያከብር ሕዝባዊ ሥርዓት
መመሥረት ነው።  ይህን ለማድረግ ደግሞ ሁሉም Iትዮጵያዊ የከፋፋዩችን ሴራ ተረድቶ
ራሱን ከስህትት መጠበቅ ይኖርበታል። በየቦታው የተከሰቱ ስህተቶችንም በAስቸኳይ
ማስቆምና Eንዳይደገሙም ማድረግ ይገባል።  በተለይም የኃይማኖት ተቋማትና መሪዎች፣
የሀገር ሽማግሌዎች  Eንዲሁም የፖለቲካና የሲቪክ ማኅበራት ይህንን  Aደጋ ለማስቆም
ሳይዘገዩ  Eንዲነሱ ሸንጎ ጥሪውን ያቀርባል።    የሀገራችንን ውስብስብ ችግሮች ሁሉንም
  Tel: 44 7937600756 , +1 9168486790  E-mail : shengo.derbiaber@gmail.com ባካተተና በብሄራዊ መግባባትና በብሄራዊ  Eርቅ ለመፍታት ጥረታቸውን  Eንያጠናክሩ
Eናሳሰባለን።
ህወሓት/IሕAዴግም በዜጎች ሕይወትና በንብረት ላይ ለሚደርስ  Aደጋ ሁሉ ተጠያቂ
Eንደሚሆን  Eያሳወቅን፣ ሃላፊነት ከጎደለው የከፋፋለህ ግዛና ተንኳሽ ተግባሩ በAስቸኳይ
Eንዲታቀብ  Eናሳስባለን።    የAገዛዙ  Aደገኛና ከፋፋይ ፖሊሲ  Eስካሁን ያደረሰውንና
ወደፊትም ሊያደርስ የሚችለውን  Eጅግ  Aሳዛኝ ሁኔታም ዓለም  Aቀፉ ኅብረተሰብ
Eንዲገነዘበውና Aስፈላጊውን Eርምጃ Eንዲወስድ ጥሪያችንን Eናቀርባለን።
Aንድነት ኃይል ነው!
የከፋፋዮችን ሴራ በጋራ Eናክሽፍ!
  Tel: 44 7937600756 , +1 9168486790  E-mail : shengo.derbiaber@gmail.com 

Mittwoch, 28. Mai 2014

ሰበር ዜና:- ጋዜጠኛ ተሰማ ደሳለኝ ሀገር ጥሎ ተሰደደ መንግስት አሁንም ሌላ ጋዜጠኛ አስሯል

May 28/2014


የኢትዮጵያ መንግስት በቅርቡ በጋዜጠኞች እና ብሎገሮች ላይ የፈፀመውን እስር ተከትሎ የኢቦኒ መፅሔት መስራች እና ማኔጂንግ ዳይሬክተር የነበረው ጋዜጠኛ ተሰማ ደሳለኝ ሀገር ጥሎ ተሰደደ፡፡ጋዜጠኛው በሀገሪቱ ያለው የፕሬስ ነፃነት አፈና ተጠናክሮ በመቀጠሉ እናመንግስት ሊወስደው ያሰበውን እርምጃ በመሸሽ እንደተሰደደ ምንጮቻችን አረጋግጠዋል፡፡ በተለይ የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን፣ አዲስ ዘመን ጋዜጣ፣ ዛሚ ኤፍ ኤም፣ እና በሌሎች የኢህአዴግ ደጋፊ ናቸው በሚባሉ እንደነ አይጋ ፎረም እና ሆርን አፌይርስ የመሳሰሉ ድህረ-ገሮች የተለያዩ ጋዜጠኞች እና የኢትዮጵያ ዞን 9 ብሎገሮች እንዲታሰሩ እና እንደሚታሰሩ ፍንጭ መስጠታቸው ለስደቱ ምክንያት መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ከመጪው ምርጫ 2007 ዓ.ም. በፊት የመንግስትን ብልሹ አሰራር እና ኢሰብዓዊ ድርጊት በመኮነን ያጋልጣሉ የተባሉ የነፃው ፕሬስ ጋዜጠኞች እና ብሎገሮች እንደሚታሰሩ በተለያየ ጊዜ የተነገረ ቢሆንም፤ በቅርቡ 3 ጋዜጠኞች እና 6 ብሎገሮች መታሰራቸው ይታወቃል፡፡ በመንግስት የተወሰደው የጋዜጠኞ እና ብሎገሮች እስር ተከትሎ ሌሎችም ሊታሰሩ እንደሚችሉ በተዘዋዋሪ መንገድ መገለፁን ተከትሎ ከጋዜጠኛ ተሰማ ደሳለኝ በፊት ጋዜጠኛ በትረ ያዕቆብ እና ፍስሃ ያዜን ጨምሮ አራት ጋዜጠኞች መሰደዳቸው ታውቋል፡:

 ጋዜጠኞቹ ከሀገር ጥለው መሰደዳቸው በስተቀር እስካሁን ያሉበትን ሁኔታ ማረጋገጥ አልተቻለም፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የእንቁ መፅሔት ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ከስራው ጋር በተያያዘ በእንቁ መፅሔት በተፃፈ ፅሑፍ ከማዕከላዊ ቃሉን እንዲሰጥ በስልክ በተደረገለት ጥሪ ትናንት ሰኞ ግንቦት 18 ቀን 2006 ዓ.ም. ወደስፍራው ቢያቀናም ማረፊያው እዛው ማዕከላዊ እስር
ቤት ሆኗል፡፡ ይሁን እንጂ ዛሬ በዋስ ይለቀቃል ተብሎ ቢጠበቅም እስር ቤቱ ፍርድ ቤት አቅርቦት የዋስ መብት ሳይከበርለት ለተጨማሪ 7 ቀናት እዛው ማዕከላዊ ታስሮ እንዲቆይ ተጠይቆበት በእስር ላይ ይገኛል፡፡

የጥሎ ማለፍ ቦለቲካ

May 28/2014
#ሳምቮድሶን #አብቢንኢትዮጵያ ሃገራችን ውስጥ ያለውን የፖለቲካ ጨዋታ በትክክልም የጥሎ ማለፍ ጨዋታ የሚያስመስሉት የሚስተዋሉ እውነታዎች አሉ፡፡ የማህበራዊ ድረገፆች ተፅዕኖ የፖለቲካ ፓርቲዎች ህብረተሰባችን ላይ ከፈጠሩት ጫና በላይ ለሃገሪቱ የለውጥ ጎዳና ጥርጊያ ሲፈጥሩ መታየቱ እሰየው የሚያስብል ተቃዋሚ ነን የሚሉ የፖለቲካ ድርጅቶችንም ያስናቀ እደጉ ተመንደጉ የሚያስብል ንቅናቄ ነው፡፡

የአረብ ባህረሰላጤውን ለአብዮታዊ ምንቅስቃስ ያበቃው ፖለቲካ ፓርቲዎች መዥጎድጎድ የፖለቲካ ፓርቲዎች ያላሳለሰ ጥረትና መንግስት የሚሉት አካል ላይ በሚያደርሱት ተፅዕኖ አደለም ነገር ግን ያን ያልል ህዝብ መስዋዕት ተከፍሎበት ድል ለህዝብ ሊሆን የቻለበት እውነት የተቀናጄና በማዕበራዊ ድረገፆች ቅብብሎሽ በሚካሄዱ አብዮታዊ እንቅስቃሴዎች አማካኝነት ነው፡፡

እነዚህ አብዮታዊ ለውጥን ማጎናፀፍና የሚችሉና የሰፊውን ህዝብ ጩኸት ሊያሰሙ ከዚያም ወደ ሙሉ ትግል ሊያስገቡ የሚችሉ ህዝቡን ምንም ያህል ተፈጥሯዊ ልዩነት ሊኖር ቢችልም እንኳን ሃገራዊ በሆነ ጉዳይ ላይ አገርን እና ህዝብን ከማዳን አንግል አንድነታቸውን አንድ አድርገው ተፋቅረውና ተሳስበው እንዲታገሉ ተፅዕኖ መፍጠር የሚችሉ የአረቡ ክፍለዓለም አብዮት ቀስቃሾችና ለውጥ አራማጆች በዚህም ስኬታማ ነበሩ ምንም እንኳን አብዮታዊ እንቅስቃሴው በተሳሳተም መንገድ በመሄድም ይሁን በትክክለኛ ብቸኛ አማራጭ ሄዶ የብዙ ህዝብን እና ንብረትን መስዋዕትነት ጠይቆ መንግስት ነኝ ባዩን አምባገነን ስርዓት ሁሉ አፈር ድሜ ቢያበላም፡፡

የሆነው ሁሉ ትክክለኛ የለውጥ መስመር ላይሆን ይችላል ነገር ግን የትኛውም የለውጥ መስመር ይሰመር ዋናው ጉዳይ ብሄራዊ እና ሃገራዊ እዲሁም ህዝባዊ ጉዳይ ላይ አንድ መስመር ብቻ መያዙ ላይ ነው፡፡ ይህም ደሞ አንድ መስመር መያዙ ግዴታ ነው፡፡ ይህ ባልሆነበት አግባብ ትግሉ ከሚፈልገው ደረጃ በሚፈልገው ሰዓትና ወቅት ለድል ይበቃል ማለት ላም አለኝ በሰማይ ነው… ምክንያቱም ድል የብዙዎች ኋላ ደጀንነትንና የብዙዎችን ፊታውራሪነት የሚጠይቅ ምናልባትም ከፊት ለፊት ብቻ ግጭት የሚሻ በጎን ከኋላ ግጭትን መጋጋጥን የማይፈልግ ሊሆን እንደሚችልም መገመት አስፈላጊ ነው፡፡

ይህ ሲባል ግጭትና መላላጥ መጋጋጥ አይኖርም ለማለት ሳይሆን መላላጥና ግጭቱ ከፊት ለፊት ከአንድ አካል ማለትም ልንለውጠው ከሚገባው ከምንታገለው አካል ብቻ መሆን አለበት፤ እርስ በራሳችን ሽህ መስመሮችን በልዩነቶቻችን ልክ እና በግለሰቦች ግላዊ ዓላማ መሳካት ልክ ተለያይተን ለትግል የተለያዩ መስመሮችን ግንባሮችን የምፈጥር ከሆነ አንድም ደጋፊ ሃይላችን ስንከፋፍልና ስንበታትነው በአንድነት የሚኖረውን ጥንካሬና አብሮነት መንፈስ አንድነታችን እየበታተንነው መሆኑን መዘንጋት የለብንም ኢህአዴግ ወያኔም ይህንን ክፍተታችን ነው እየተጠቀመበት ዕድሜውን እያራዘመበት ያለው፡፡

ስዎች ኢህአዴግ አንድነታችን ወዶ አደለም የሚፈራው መመከት ማይችለው ናዳ እንደሆነ ያውቃል አንድነታችን አንድ ብቸ ጠንካራ ብቻ አደለም የሚያደርገን አንድነታችን በሁሉም አቅጣጫ ያሉ የውጭም ይሑን የውስጥ አካላት ትኩረታቸውን አንድ ማንነታችን ላይ ሲያሳርፉ ትኩረታቸው ሁሉ ያለንን ጫና የመቀበል እንጅ ያለመቀበል ማቅማማት አያሳዩም፡፡ ይህም ሌላው ጥቅም ነው አንድ በሆንን ቁጥር፡፡

ኢህአዴግ ወያኔ አረመኔና አስከፊ የአደገኛ ቦዘኔ ስብስብ አምባገነን ስርዓት መሆኑን ማንም አደለም ህዝቡ ራሱ አህአዴግም ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ ይህ ችግር እንደማያመጣበትም ጠፍቶት ሳይሆን ይህንን ችግሩን በዚህ ባህሪው ምክያት የሚመጣበትን ፈተና እንዴት መወጣት እንደሚችል ስለሚያውቅ እንጅ፡፡ ይህ የሚያውቀው የፈተናው የህዛባዊ አመፅ ማስታገሻ ብቸኛና ያለ የሌለው መፍትሄና ማሻሪያው ግን አንድና አንድ የሆነ በመካከላችን እንደ ጎርፍ እየሰረሰረ በመግባት ልዩነቶቻችን በመካከላችን በመርጨት እኛ ስንናቆርለት እርሱ የሰራውን ቢሰራም ያለ አንድነታችን ምንም እንደማናመጣ ያውቃልና በእርስ በእርስ ልፊያችን እንደ ሳይጣን ሳናየው ይስቅብናል፡፡ ይህንን ስለማድረጉ ደግሞ ከአመታት በፊት በድብቅ ሲያደርገው ነበረውን አሁን አሁንማ በግላጭ በጠራራ ፀሃይ ሃውልት እስከ መስራትም ደረሰልን እኮ የእኛ ጀግና ስርዓት አልባ መንግስታችን፡፡

ይህች ብቸኛ አማራጭ ብቻ እንዳለቸውም ያውቃል ለዚህም ነው ወገቡን አስሮ ያፋጀን ያሰበው፡፡ ይህንን ነው መታገል ያለብን በመካከላችን ኢህአዴግ እየሰረገ እየገባ መከፋፈሉን ተገንዝበን እኛም እየተከፋፈልንለት መሆኑን አውቀን ይህም የኢህአዴግን የስልጣን ዘምን ሲያራዝም የኛን ነፃነት ትግል እንደሚያቆረቁዘው አስበን ራሳችን ከተኛንበት ምቹ የስንፍና አልጋ ላይ ነቅተን ማውረድ አለብን፡፡ ይህች ብቸኛ አማራጭ ማለትም "…ታሪካዊ ክፍተትን መጠቀም…" መንግስት እንደትልቅ እድል ቆጥሮ አጋጣሚዋን ህዝብ ሳያውቅበት ማስፋፋት ይፈልጋል ሆኖም እድሜ ለነፃነት ታጋይ አጋሮቻችን በተለያዩ ሚዲያዎች

…ኢህአዴግ አቁም ነቅተንብሃል እኛ አንድ ነን በአንተ ሴራ አንከፋፈልም ኢትዮጵያ አንድ ናት ህዝቦቿም አንድ ናቸው…፡፡

እያሉ በመለፈፍ አሁን አሁን ህዝቡ በመጠኑም ቢሆን በመንቃት ላይ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ እዚህ ላይ የመብት ጥያቄ የይገባኛል ጥያቄ የብሄራዊ አንድነትና ክብር ጥያቄ ያነሳል ኢህአዴግ ለመልሶቻችን ምንም አይነት ደንታ የለውም፡፡ ያችን ቁልፍ ታሪካዊ ክፍተትና ልዩነቶቻቸን ብቻ ዞር ማድረግ ነው መፍትሄው ብሎ ስርዓት አልባው መንግስትም "ከፈሱም አይጥፈን"፡፡ ለምን ስንል ደግሞ በእጁ የተፃፉትን መፅኀፍት አንብቦ ምሁር የሆነ የሚመስላቸውን ጅልና የስርዓቱ መሃይም አቀንቃኞችን በመጠቀም የታሪክ ክፍተቶችን በአንድ ሌሊት ቁጭ ብለው ያነቡና ያንን ክፍተት የሚሉትን የታሪክ ሽንቁር ካለ እንኳን ተምረንበት ልናልፍ የሚገባውን ሊደገሙ የማይገባቸውን ስዕተቶችን /ምናልባት ካሉ/ራሳቸውን ለህዝብ ባላደረጉ በስርዓቱ ልሳናት አንድም ቀን ህዝብን ከማደንቆር ውጭ አንድም ፋይዳ የሌላቸውን ልሳናት በመጠቀም ለሚዲያ ያበቁታል፡፡

ይህንን ሽንቁር አነበብኩ ለካስ እንደዚህ ነበር ብሎ ራሱን እሳት ውስጥ መክተቱን ያላወቀውና ለስርዓቱ መጠቀሚያ ማሽን እየሆነ እንዳለ ያላወቀው ምስኪን የየትኛውም ቋንቋ ተናጋሪ ኢትዮጵያዊ ደግሞ ያራግበዋል፡፡ ካነበበው ላይ በራሱ የወግ ማጣፈጫ ሲጨምር እንኳን ሌላ ቃል ሲጨምር አሁንም ሌላ ሲጨምር… ቆልሎ ቆልሎ ስርዓቱ ሊጠቀምበት ካሰበው በላይ በማድረግ ለሚቀርቧቸው ሁሉ ይነዙታል፡፡ ያኔ ኢህአዴግየ በክፍተቶች ስፋት በተፈጠሩት ልዩነቶች እየጨፈረ ዳንስ ቤት ለዳንስ ቤት በየፖለቲካ ዳንስ ቤቶች እና ሙዚቃዊ ዳንስ ቤቶች ሁሉ እየዞረ ሲዘልል እንደ እንቦሳ ሲቦርቅ ያድራል… ያኔም ሌላ ሴራ ይሸርባል፡፡

በጣም የሚገርመኝ ሁለት ነገር ውስጥ የኢህአዴግ ደካማ ጎናችን ወይም ኳርታችን ማወቅ መቻሉና እኛ ደግሞ ያለብንን ያላረጋገጥነውን ከየትም ያገኘነውን ወሬ የመንዛት አባዜ እውነቶች ናቸው፡፡ ህዝቡ በተለይ ሳያውቁም ሆነ እያወቁ አንዳንድ ለስርዓቱ መሳሪያ የሚሆኑ አካላት በልዩነቶቻችን የሚገቡ ጋሬጣዎችን ስንጥሮችን ያለ የሌለ ሃይላቸውን በመጨመር ግንድ ያህል ያሳድጓቸዋል፡፡ እነዚህን ግንዶችም ወደ ድልድይ ያሳድጓቸዋል… ድልድዮችንም ይሰብሩና ያለያዩትና ዓለማትን ይፈጥራሉ ሃገራትን ይመሰርታሉ ከዛም እናንተ ሌላ እነዚህ ሌላ ምን አገናኝቷችሁና አንድነትን ትሻላችሁ የሚል አስተሳሰብን ይጭኑብናል፡፡

ይህን የሚያደርጉት ኢትዮጵያዊነታቸውን ረስተው ጎጠኛና ራሳቸውን ለሚያዩትና ሚሰሙት ብቻ የሚያጠቡ ከእንሰሳ ያልተሸለ አስተሳሰብን ይዘው በአንድ በኩል ኢህአዴግን የሚታገሉ የሚመስላቸው በሌላ በኩል ደግሞ ሳያውቁትም ሆነ አውቀውት ለዚሁ ሳይጣናዊ ስርዓት የሌለው ስርዓት መሳሪያ ሆነው የሚያገለግሉ እነዚህ ልዩነቶቻችን በመፈጠራቸው ለሚደሰተው የስልጣን እድሜውን ማራዘም ለሚፈልገው መንግስት ትልቅ የምስራች እየፈጠሩለት እንደሆነ አለማወቃቸው ያሳብዳል፡፡

ታዲያ ይህ የእቅልፋሞችና አንድም ሳያውቁ ያወቁ የሚመስላቸው አካላትና የስርዓቱ አገብጋቢዎች ባይኖሩማ መች ይሕን ያህል ልዩነነት ይኖር ነበር፡፡ መች ያለፉት ስርዓቶች የተባለውን ያህል ግፍ ሰሩና… መች ያለፉት ስርዓቶች የሚነገርላቸው መልካምና አስተማሪ ተግባራትበን መስራታቸው አደለም ኢትዮጵያዊውን አለምን ማስተማር የሚችሉ ተግባራትና ስኬቶችን አጡና… መች ከስዕተቶቻቸው መማርና አለመድገም ሲገባን መች ከስዕተቶቻቸው ሌላ የከፋ ስዕተት እንማር ነበርና…

ይህን ሁሉ ሴራ ማን ሸረበውና…ይህንን ሁሉ ቂም እና ሳል ማን አቋረሰንና ኢህአዴግም አደል እንዴ…ይህን ሃቅ የሚክድ በምንም መስፈርት ጤነኛ አዕምሮ አለው ማለት አይቻልም፡፡ ይህንን ሃቅ ክዶ ሊያስተባብል የሚፈልግ ጤነኛ አዕምሮ የለውም ካልን ደግሞ የምንመራው ምንም ጤነኛ አዕምሮ አላቸው በማንላቸው አካላት ነው ማለት ነው፡፡

እጅግ በጣም የሚያሳዝነኝ እኮ ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ ስንትና ስንት መስራት እየቻለና እየሰራ ይህንን ሴራቸውን አውቀው ከሚደግፉት ልበ ስውራን ይባስ ማወቅ አለመቻልና ኢህአዴግን አውቄብሃለው ኢትዮጰያ የምትባል ሃገር እንዳትኖር ካለህ የቆየ ህልም ነው ብሎ አንኳን በአደባባይ ወጥቶ የተከፋውን ያህል መታገል አለመቻሉ እና ለመታገልም ለሆዱ ሲል ብቻ እና ከኔ እስኪደርስ በሚል ራስ ወዳድ ድድብና መነሳት አለመቻሉ የአንዱ ኢትዮጵያዊ መበደል በቡድንም ሆነ በግለሰብ የራሱ መበደል የራሱ መለገፋት መሆኑን ለዛች ቅፅበታው ጥቅሙና ሰላም አብሮት እንደሚኖረው ሁሉ ለሃብት እና ሆዱ ሲል ሰላምና የሰፈነባት የዜጎች መብት የተከበረባት ሃገር ከሌለች ሃብቱን አብሮት እንደሚቀበረው ሁሉ ድምጥማጡን አጥፍቶ መተኛቱ ነው፡፡

ስለዚህ መጀመሪያ ይህንን ሃይልም ማንቃትና ለሌሎች በደል መነሳትን ማሳየት አለብን፡፡ በመሰረቱ አንዱ ሲበደል ዝም ብሎ ማለፍን እንደመብት የሚቆጥር ሰው መብቱ እንደሆነ አድርጎ የሚያስብ ከሆነ ትልቅ ስዕተት እየሰራ እንደሆነ ሊያውቀው ይገባል፡፡ ዝምታ ዝም ማለት ከሚገባው ቦታ ላይ እንጅ የብቃት መለኪያ የአዋቂነት የሃብት የስብዕና መለኪያ አወንታዊ ምላሽ አደለም፡፡ ዝም ማለት ሳያስፈልግ ዝም ማለት ጤና መጉደል እንጅ ጤነኛነት አደለም፡፡

የራበው ህዝብ መብላት የሚጀምረው መሪውን ከዛም የተመሪ መሪዎችን ነው፡፡ እያለ ይቀጥላል፡፡ የተራበ ህዝብ የራቡን ጥማት ሁሉ ይወጣል፡፡ የሚርበው ምግብ ብቻ ላይሆን ይችላል፡፡ ስንት እራብ አለ ስዎች እንንቃ እንጅ፡፡ የዲሞክራሲ ርሃብ አለ፤ የየትኛም ነፃነት እራብ አለ፤ የምግብ ረሃብ አለ፤ የልብስ ረሃብ አለ፤ የመሰረታዊ ፍላጎት ምሟላትና አለመቻል ረሃብ አለ፤ እጅግ ብዙ ምናልባትም የህዝቡን ቁጥር ያህል የተለያየ ረሃብ አለ፡፡ እኛ ሃገር ላይ ሁሉም አይኘት ረሃቦች አሉ፡፡ ታዲያ ይህ ህዝብ የራበውን ያህል መልስ ባልተሰጠው ቁጥር ረሃቡም በጣም እየራበው ረሃቡን ማርኪያ ፍላጎቱም በጣም እየናረ ነውና የሚሄድ ይህንን በሁሉም አቅጣጫ የራበው ህዝብ ማርካት ግድ ይላል፡፡ ለረሃብ አምጭና ለርሃብ ተባባሪ መሆንና ረሃብ በበር ሲያልፍ ዝም ብሎ ማሳለፍ በራበው ከመበላት አያድንም ብያለው፡፡

ኢህአዴግ ብልጥ ነው ማለትም ይቻላል፡፡ አንዱን የህዝብ ጥያቄ በሌላ ህዝብ ጥያቄ ነው እንዲረሳ የሚያደርገው በደልና ግፎችን ሲደራርባቸው መነሳት የሚገባው ሳይነሳ መነሳትና መዘብዘብ የሌለበት ላይ ህዝብ ጊዜውን ያጠፋል፡፡ ይህም ኢህአዴግን ይጠቅመዋል፡፡ ህዝቡ ቀልቡን ሰብስቦ አንድ ጥያቄ ይዞ ምላሽ ፍለጋ ወደ እሱ እንዲሄድበት አይፈልግም፡፡ ለዚህም ነው ህዝብ አንድ ጉዳይ ላይ ጥያቄ ሲያነሳ ሌላየህዝብ ጥያቄ ሊሆን የሚችል ጉዳይ እያወቁ ያመጣሉ ያጠፋሉ፡፡ ያኔ እንደለመድነው ጯጩኸን ዝም እንላለን፡፡ አስቡት እስቲ ስንት ጉዳዮች አስጩኸውን ስንቶችን ረሳናቸው፡፡

ይህ በትግል አንድነታችን እያመጣን እያለ ሌላው ደንቃራችን ነው፡፡ የሃሳቦች መበታተን ገጥሞናል፡፡ ይህን ጉዳይ ማሰሪያ ለማበጀት ደግሞ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ትልቅ ሚና አላቸው ሃላፊነትም አለባቸው ጥቅልል ያለ ፖሊቲካዊ ጥያቄ እንድናነሳ መሪ ልትሆኑን ይገባል እስከመፍትሄው ድረስ እስከመጨረሻው መታገል ያስፈልጋል መፍትሄ ካልተገኘ ደግሞ መጮህ የሙስሊሙ እንቅስቃሴ ምርጥ ምሳሌ ነው ለዚህ፡፡

በትርኪ ምርኪው ሁሉ ከምታስጮኹን ይልቅ ጥቅልል ያለ ሃሳብና ጥያቄ ይዛችሁ ጥያቄያችን ጥቅልል አድርጋችሁ አታግሉን መፍትሄውን እስክናገኝ ድረስ አስቀጥሉን፡፡ እኛ እስከመጨረሻው አብረናችሁ ነን ልንላቸውም ይገባል አለያ ይህ የጥያቄ ፖሊቲካ ጥሎ ማለፍ የትም አያደርሰንም፡፡ ጥያቄያችን ተቀጣጣይና የብዙሃኑን ነፃነት ናፋቂ ሃሳብ የያዘ እና እስከመፍትሄው ልንሄድለት የምንችለው እጅ መሆን ያለበት እንዲያው ለይስሙላ ምን ያህል ህዝብ ኢህአዴግን ይጠላዋል እስቲ ምን ያህል ህዝብ ለሰላማዊ ሰልፉ ይወጣል ገለመሌ ብሎ ዘላቂ ያልሆነ አላማ ይዞና እንዲያው ለከንቱ የሚዲያ ውዳሴ ብለን ከወጣንና ሰላማዊ ሰልፍ ምናምን ከጠራን ስዕተቱን የሰራችሁት እናንተ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ናችሁ፡፡ በእርግጥ የፋይናንስ ምንጭ ችግር ሊኖር እንደሚችል ጠፍቶኝ አደለም፡፡ ብዙ ጊዜ ወጣን እኮ፡፡

ነገር ግን ያነሳናቸው ምን ያህል ጥያቄዎች ናቸው ምን ያህሉስ ምላሽ አገኙ? ምን ያህሉንስ እስከምላሻቸው ድረስ ልንሄድባቸው አስበናል? በበነጋታው ለምንረሳቸው ጥያቄዎቻችን ከሆነ የምንጮኸው ከዚች ዕለት ጀምሮ ማንም ሰላማዊ ሰልፍ ብሎ ባይወጣ የሚኖረውን ያህል ዋጋ ብቻ ነው የሚኖረው ባይ ሆኘ እንዳላርፍ የውጭ ተፅዕኖ መንግስት እንዲያርፍበት ስለሚያደርግ ሃሳቤን በዚህ አልቋጨውም ሆኖም ግን ትግላችን እስከ እስርና አስከ ቃሊቲ እስኪያበቃን ሳይሆን መሆን ያለበት አስከ ምላሽ ማግኘትና እስከ የሚታይ ለውጥ ድረስ መሆን አለበት፡፡

ጥያቀዎቻችን ካለተመለሱ አሁንም ያንኑ ጥያቄና አዳድስ ጥያቄዎቻችንን የመብት ጩኸታችንን ማቅለጥ ምላሽ እስኪያገኙና ለውጥ እስኪመጣ አለያ ግን ውሃን ቢወቅጡት እምቦጭ ነው ሚሆነው፡፡ እስቲ ሁላችንም ልብ ይስጠን፡፡

ቀጣይነት ያለው ያላሰለሰ ትግል ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ አለያ ጠየፖሊቲካ ጥሎ ማለፍ ስልጣን ላይ ላለው ሲጠቅም ለነፃነት ናፋቂው ግን ክስረትና የከፋ ግፍን ያስከትላል

#አብቢን ነኝ

Montag, 26. Mai 2014

ግንቦት 20 ያለመለስ ስንት ይቆይ ይሆን?

May 25/2014
ግርማ ሠይፉ ማሩ 
girmaseifu32@yahoo.com
ሰሞኑን ልባችን እሰኪጠፋ የግንቦት 20 ፍሬዎች የተባሉት “ልማትና ዲሞክራሲ” በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን 
ድርጅት እንዲሁም እየተከፈላቸው በማህበራዊ ድህረ ገፅ የስድብ ናዳ የሚያወርዱትን ስዶች ጨምሮ እንደ ፍራፍሬ 
እየበላን እንደ ወተት እየተጋት ነው፡፡ ሚዛናዊ ሆኜ ግንቦት 20 ያመጣልኝን ፍሬ ሳስብ የምር ግራ ይገባኛል፡፡ የእኔ ግርታ 
የሚመነጨው አሁን ያለንበት ደረጃ ለመድረስ በእርግጥ 23 ዓመት ያስፈልገን ነበር ወይ? የሚል ነው፡፡ በእኔ እምነት ግንቦት 20 የስርዓት ለውጥ የመጣበት ቀን እንደሆነ ለመቀበል አልቸገርም፡፡ ደርግን የተካው ዳግማዊ ደርግ በመባል 
የሚታወቀው ኢህአዴግ ግን ከምን ከምን አንፃር ከደርግ እንደሚሻል ሊገባኝ አልቻለም፡፡ እኔ በፍፁም የማላደርገው 
ኢህአዴግን ከደርግ ጋር ማወዳደር ነው፡፡ በሂሣብ ትምህርት ፍየልና በግ እንደማይደመረው ማለት ነው፡፡ ኢህአዴጎች ደስ የሚላቸው ሁሌም ውድድሩ ከደርግ ጋር እንዲሆን ነው፡፡ ሲያስፈልግም ከምኒሊክ ጋር መወዳደር የሚያሻቸው በተለይ ባቡርና ስልክ ሲነሳ ነው፡፡ ሊያፍሩበት በሚገባ ነገር ውድድር ይከጅላሉ፡፡ እኔ ኢህአዴግን እንዲመዘን የምፈልገው ስመዝነውም የሚቀልብኝ ከዓለም አቀፍ መለኪያ እንዲሁም እኛ ኢትዮጵያዊያን ከሚገባን ደረጃ አንፃር ነው፡፡
አፍቃሪ ኢህዴጎች “ኢህአዴግ ባይኖር ኖሮ ይህች ሀገር ትፈራርስ ነበር” ለማለት አፋቸውን እንኳን ያዝ አያደርጋቸውም፡፡ ይህንን መፈራረስ የገታው ደግሞ “የኢህአዴግ የብሔር ብሔረሰብ ፖሊሲ ነው” ይሉናል፡፡ በእኔ እምነት የመፈራረስ ሟርትም ሆነ የሟርቱ 
ማፍረሻ ፖሊሲ ተቀባይነት የላቸውም፡፡ ኢህአድጋዊያች ለዚህም ማሳያው የሚሉት በሽግግር ኮንፈረንስ ላይ ተሳታፊ ከሆኑት ውስጥ ከአስር በላይ የሚሆኑት መገንጠል አለብን የሚሉ ነበሩ በማለት ነው፡፡ ልክ ነው በዚህ ማህበር ውስጥ እንደዚህ ዓይነት ሃሣብ የሚያራምዱ ቢበዙ እንጂ የዚህ አቀንቃኞች ሊያንሱ አይችሉም፡፡ ህወሃትን ጨምሮ ኦነግ፣ ኦብነግ፣ የመሳሰለሉት ከስማቸው ጭምር የመገንጠል ደቀ መዝሙሮች እንደሆኑ ይታወቃል፡፡ በእነርሱ ጋባዥነት የሚመጣ ድርጅት እንዴት አድርጎ ከዚህ የተለያ ሃሳብ ሊያራምድ ይችላል ተብሎ ይገመታል፡፡ ለዚያውም እነዚህ ጋባዦች በለስ ቀንቷቸው መሣሪያ ታጥቀው አራት ኪሎ ቁጭ ብለው ባሉበት ወቅት፡፡ ይህ ግን በፍፁም 
የኢትዮጵያ ህዝብ ለመገንጠል ዝግጁ ነበር የሚያስብል አይደለም፡፡ ኢትዮጵያዊያን ከኢህአዴግ በፊትም በቋንቋቸው ይናገራሉ፣ ይዘፍናሉ፣ ያለቅሳሉ፡፡ በኢህአዴግ ጊዜ የተጨመረልን “ቁቤ የሚበል” ፊደል እና ወጣቱ በተለይ በኦሮሚያ አካባቢ ኢትዮጵያዊ ራዕይ እንዳይኖረን 
መደረጉ ነው፡፡
የዚህ ፍሬ ምስራቹን በቅርቡ በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ደርሶ ተመልክተነዋል፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ችግር 
በኢትዮጵያ ጥላ ስር ይፈታል ጥቅሙም ይረጋገጣል ብዬ ነው የማምነው የሚለው ኦህዴድ፤ አባል የሚመለምለውና የሚያደራጀው በኦነግ ፕሮግራም እንደሆነ ያጋለጠ ክስተት ነበር፡፡ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒሰትር አሉት የሚባለው “ኦህዴድ ሲፋቅ ኦነግ ነው” የሚባው በዚህ ክስተት ኦህዴድ ሳይፋቅም ኦነግ ሆኖ ነው የተገኘው፡፡ ይህ በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ሀገራት ለውህደት በሚሰሩባት ዓለም የመገንጠል ጥያቄ በወጣቶች ላይ የዘራው ኦህዴድ/ኢህአዴግ ያሰገኘልን የግንቦት 20 ፍሬ ነው፡፡ ኢቲቪም ሆነ ተሳዳቢዎቹ የማህበራዊ ድህረ ገፅ 
ካድሬዎች ይህን የግንቦት 20 ፍሬ አያነሱትም፡፡
ዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ በአንድ ሳምንት ተበጥብጦ የሚጠጣ አይደለም የሚል አዲስ መፈክር መጥቶዋል፡፡ በእኔ እምነት ሃያ ሶስት ዓመት ሙሉ ተዓማኒነት ያለው እና ተቀባይነት ያገኘ ምርጫ ማካሄድ ያለመቻልን የሚያክል ብቃት ማነስ በዓለም ያለ አይመስለኝም፡፡ 
ለነገሩ በብቃት ምርጫ ማጭበርበር እንደ ብቃት ከተወሰደ ደግሞ ገዢውን ፓርቲ የሚያሽልም ነው፡፡ ለልምድ ልውውጥም ብዙ አንባገነን መሆን የሚፈልጉ እንደ ጆርጅ ኦሩዌል መፅሃፍ ሊጠቀሙበት ይችላሉ፡፡ የዲሞክራሲ ስርዓት ገንብቻለው የሚል መንግሰት ዜጎች በምርጫ ለመወዳደር፣ አማራጭ ይዞ በፖለቲካ ውስጥ መሳተፍ፣ ምርጫን ያለስጋት መታዘብ፣ የመሳሰሉትን ዲሞክራሲያዊ መብቶች ለመጠቀም 
በፍርሃት እየራዱ ብዙዎች “አታነካኩኝ ልኑርበት” የሚሉበት ሀገር ሲሆን፤ የዲሞክራሲ ስርዓት ለማስፈን ነው ትግሉ እየተባሉ በዱር በገደል ህይወታቸውን የሰዉ ሰማዕታት ድንገት ቀና ቢሉ ምን ምን ዓይነት መልስ እንደሚሰጧቸው መገመት ያስቸግራል፡፡ የሚያሳዝነው 
እራሳቸውን ለመስዋዕትነት አዘጋጅተው የነበሩ በአጋጣሚ በህይወት የተረፉት ይህ ነው ዲሞክራሲው ሲባሉ እሺ ብለው መቀበላቸው ነው፡፡
ከመሰዋዕትነት መትረፋቸውን እንደ አንድ ትርፍ ቆጥረው በአንድ ወይም በሌላ የሚያገኙትን ጥቅም እያገኙ እነርሱም ቀሪ ህይወታቸውን ማጣጣም ተያይዘውታል፡፡ በህይወት ለሚገኙ ኢህአዴግ ታጋዮች ፍሬው የእነርሱ በህየወት መትረፍ ሆኖወል፡፡ የሰመሃታቱን ቃል ኪዳን መብላት ግንቦት 20 ፍሬ ነው፡፡
የዛሬን ግንቦት 20 ለሃያ ሶስተኛ ጊዜ ተከብሮዋል፡፡ ዋና የቡድን መሪያቸውን አጥተው እውር ድንብር መሄድ ከጀመሩ ደግሞ ለሁለተኛ ጊዜ ያከበሩት ኢህአዴጎች ዛሬም ሃሳብን በነፃነት መግለፅን ማረጋገጥ አልቻሉም፡፡ ከዚህ በኋላ ስንት እንደሚቆዩ አይታወቅም፡፡ ለዚህ ነው ስንት ይቆዩ ይሆን ብዬ መጠየቅ ያማረኝ፡፡ ኢህአዴግ በእርግጥ የተሳካለት ይህን መብት መረጋገጡ ላይ ነው፡፡ በህገመንግሰት ውስጥ ወርቃማ ነፃነቶችን ለማስቀመጥ ያልፈራው ኢህአዴግ በጠመንጃ ለማነጋገር ከተዘጋጁት ይልቅ በብዕራቸው ጉድለቱን ሊያሳዩት የሚጥሩትን ጋዜጠኞች ዓይናችሁን ላፈር ብሎ እያሳደደ ነው፡፡ ኮምፒዩተር ላይ ቁጭ ብለው ሃሣባቸውን በነፃነት እዚህ ግባ ለማይባል ማህበራዊ ገፅ ተጠቃሚ ስላካፈሉ ብሩዕ ተሰፋ ያላቸውን ወጣቶችን እስር ቤት ያጉራል፡፡ ርዕዮት ዓለሙ፣ ውብሽት ታዬ፣ እስክንድር ነጋ አንድም ጥይት 
የላቸውም፡፡ 
የሚያስገርመው ጠመንጃ ከያዙት ይልቅ ግን ገዢውን ፓርቲና መንግሰትን ያርበደብዱታል፡፡ “ዞን ዘጠኞች” በምን መለኪያ ነው ብጥብጥ የማስነሳት አቅም ያላቸው፡፡ የእነሱ አቅም የነበረው ሃሣብን በነፃነት ገልፆ በሰላም መተኛት ነው፡፡ ለነገሩ እነርሱም ወደ ሌላ ግርማ ሠይፉ ማሩ ዞን ተዛወሩ እንጂ ሀገሪቱ እራሷ እስር ቤተ መሆኗን ለማመላከት ነው “ዞን ዘጠኝ” ብለው እራሳቸውን የሰየሙት፡፡ ኢህአዴግ እነዚህ
ወጣቶች በሀገራችን ጉዳይ ያገባናል ብለው ስለተንቀሳቀሱ እስር ቤት አጎራቸው፡፡ በተቃራኒው ግን እነዚህ ወጣቶች በየካፍቴሪያውተጎልተው ቢውሉ፣ በየጫት ቤቱ ሺሻ ሲያጨሱ ቢውሉ እና ዲቪ ሲሞሉ ወይም ከሀገር መውጫ መንገድ ሲቀይሱ ቢውሉ፣ ስለዚህች ሀገር 
አያገባንም ብለው ቢጦምሩ ጫፋቸውን አይነካም፡፡ ዝንባቸውን እሽ አይልም ነበር፡፡ የግንቦት 20 ፍሬያችን ከሃያ ሶስት ዓመት በኋላ ያገኘነው በግልፅ በህገ መንግሰት የተደነገገን ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት የማይከበርበት ስርዓት መገንባት ነው፡፡ የስርዓት ለውጥ ብቻ፡
፡ ከደርግ ወደ ዳግማዊ ደርግ በመጀመሪያው ዘመናቸው ቡድናዊ አንባገነንነት፡፡ በኋላም ወደ ግለሰብ አንባገነንነት ማለትም ከመንግስቱ ሀይለማሪያም ወደ መለስ ዜናዊ መሸጋገር ነው፡፡ይህን ኢቲቪ ሊያሳየን አቅም የለውም፡፡ ተከፋይ የድህረ ገፅ ተሳዳቢዎችም አይሞክሯትም ለምን ቢባል እንጀራ ነው፡፡
ግንቦት 20 እንደ መሰከረም 2 ወደ መቃብር እንዳይወርድ በቀጣይ የሁላችንም ኢትዮጵያዊያን ባህል ይሆን ዘንድ ግን ኢህአዴግ አሁንም እድል አለው፡፡ ሃያ ሶስት ዓመት ዘግይቶም ቢሆን ሰመዓታቱን ሊያስከብር የሚችለውን የዲሞክራሲ ስርዓት ለመገንባት ቁርጠኛ መሆን ይኖርበታል፡፡ የኢትዮጵያን ህዝብ የሚመጥን የዲሞክራሲ ስርዓት አብዮታዊ ዲሞክራሲ ነው፤ ይህንንም ለማሳካት እኛ ሰላሣ እና አርባ ዓመት መግዛት አለብን የሚለው ተረት ተረት ተቀባይነት የሌለው ብቻ ሳይሆን በዚህች ሀገር ሌላ አብዮት የሚጠራ ገፊ ምክንያት ነው፡፡ 
ይህ አብዮት ሲመጣ ደግሞ መሰከረም ሁለት እንደተፈነገለው ግንቦት 20 ይፈነገልናል ሌላ ከዓመቱ አንድ ቀን ሌላ የድል የለውጥ ቀን ይመጣል፡፡ ለዲሞክራሲ ለፍትህ ሲባል ሰማዕታት ለሆኑት ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ሲባል ግንቦት 20 የድል ቀን ሊሆን የሚችልበት እድል ያለው በኢህአዴግ እጅ ነው፡፡ በማንኛውም ምክንያት ኢህአዴግ በክብር ሳይሆን በውረደት ከወደቀ ግንቦት 20 የዓመቱ አንድ ቀን ከመሆን አልፎ የድል ቀን ሆኖ ሊከበርበት የሚችልበት አንድም ምክንያት አይኖርም፡፡ አሁን ባለው ሁኔት ያለፉት 23 ዓመታት ለኢህአዴጋዊያን 
የድል ቀን ሲሆን ለእኛ እንደማነኛውም የዓመቱ አንድ ቀን ሆኖ ተገደን ከሰራ የምንቀርበት ቀንም ጭምር ነው፡፡ እንደ አሁኑ ደግሞ አርብ ቀን ሲውል ለረዥም የሳምንት መጨረሻ ግብዓት ሆኖ ያገለግላል እንጂ በመጀመሪያው ግንቦት 20 ጠዋት የሰማነውን ለህዝብ ጥቅም ሲባል 
የተሰራ አንድም ድል አይሸተኝም፡፡
ዐፄ ሀይለስላሴ ሰማኒያኛ የልደት ባህላቸውን፤ ደርግ የኢትዮጵያ ጥናት ኢንስቲትዮት ያቀረበለትን የስልጣን ይልቀቁ ጥያቄ ገፍተው እንደተዉት ሁሉ ኢህዴግም እሰከ ዛሬ ካሳለፋቸው እድሎች በተጨማሪ መቼ እንደሆነ በቅርብ ባይታወቅም እሩቅ ባልሆነ ጊዜ እድሉን ገፍቶ ይጥለዋል፡፡ በተለይ ደግሞ ከዋናው የቡድኑ መሪ መለስ ዜናዊ እልፈት በኋላ ለረዥም ጊዜ በሴራም በእውቀትም የሚመራው ሰው 
ያለው አይመስለኝም፡፡ ይህ ግን ከግምት በላይ ነው፡፡ ወንበሩን የወሰዱት ጠቅላይ ሚኒስትር ይህን ፍንጭ አላሳዩንም ይልቁንም ሌጋሲ ማስቀጠል በሚል የወይን ፋብሪካ ምረቃን ጨምሮ ተቀባይነት የሌላቸው በምረቃ ስራ ተጠምደው መዋላቸው ለሌላ ሰትራቴጂክ ሰራ ጊዜ 
እንደሌላቸው የሚያሳብቅ ነው፡፡ 
እነዚህን ሁሉ ደምረን ስናይ ግንቦት 20 እንደ መስከረም 2 ሳይዋረድ ከመለስ እልፈት በኋላ ስንት ዓመት 
ይቀጥላል? ብለን እንድንጠይቅ የሚያስገድደን፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ ግንቦት 20 በግራዋ ዛፍ ላይ የበቀለ መራራ አፕል ነው፡፡
ቸር ይግጠም!!!! 
ግርማ ሠይፉ ማሩ
ኢትዮሚድያ 
May 25, 2014

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምተሃታዊ ማጭበርበር ተፈጽሞብናል ያሉ ደንበኞች ቅሬታ አሰሙ

May 25/2014
በኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት ከሚተዳደሩ ባንኮች ውስጥ አንዱ እንደሆነ የሚነገርለት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዲስ አበባ ብቻ ከ45 የሚበልጡ ቅርጫፎች እንዳሉት ይታወቃል። ባንኩ ለደነበኞቹ በሚሰጠው የተቀላጠፈ አገልግሎት ከግዜ ወደግዜ አቅሙን እያጎለበት በሃገር ውስጥ ብቻ ከ205 በላይ የሆኑ ቅርንጫፍ መ/ቤቶችን በመክፈት ከ8000 በላይ በሆኑ ሰራተኞች በመታገዝ የአገልግሎት አድማሱን እስከ ጅቡቲ ድረስ ተደራሽ ለማድረግ ቢጠረም በተለያዩ ግዜያት በሚፈራረቁበት አሰታዳሪዎቹ ተቋሙ ቀደም ብሎ የነበረውን ስም እና ዝና ይዞ መቀጠል እንደተሳነው የሚናገሩ ምንጮች ባንኩ ከደንበኞቹ ቆጥሮ የተረከበውን ጥሬ ገንዘብ በእምነት መስጠት እንደተሳነው ይናገራሉ ። በተለይ 1000 እና ከዛ በላይ የሆኑ ተቀማጭ ገንዘቦችን ባንኩ ለደንበኞቹ ሲያስረከብ በባንኩ ማህተም የታሸጉ ባለ መቶ ኖት ብሮች ላይ የሁለት መቶ እና ከዛ በላይ ጉድለት የሚታይባቸው መሆኑን የባንኩ ተገልጋይ 
ከቅሬታ አቅራቢዎቹ በመረጃ አስደግፈው ይገልጻሉ።
ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለተለያዩ ጉዳዩች ከፍተኛ አሃዝ ያለው ገንዘብ በየቀኑ ውጪ የሚያደርጉ ነጋዴዎች ከ2 እስከ 5000 በር እንደሚጎድልባቸው የሚናገሩ ምንጮች ከተጠቀሱት የባንኩ ቅርንጫፍ መ/ቤቶች በቀን በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ከደንበኞች ኪስ እንደሚመዘበር ይናገራሉ ። ባንኩ በስህተት ትርፍ ገንዘብ እንደማይሰጥ የሚናገሩ ቅሬታ አሰሚዎች ጉድለቱ የተለመደ ነው ከማለት ውጭ በባንኩ ፀያፍ ተግባር አቤት ለሚሉት አካል አጥተው በዚህ መንግስታዊ ተቋም ስም በዜጎች ላይ በጠራራ ፀሃይ እይተፈጸመ ባለው ማጭበርበር ማዘናቸውን ይገልጻሉ ። ሰሞኑንን በቅሎ ቤት አካባቢ የሚገኝ ንግድ ባንክ በአደራ ያስቀመጡትን 25 0000 ብር ወጪ ለማድረግ ወደ ቅርጫፍ መ/ቤት ጎራ እንዳሉ የሚናገሩ አንድ እማወራ የባንኩ ሰራተኞች በማህተም አሽገው ለእማኝነት ሁለት የታሸጉ ርብጣ ብሮችን ቆጥረው እንዳስረከቦቸው ጠቅሰው እቤት ደርሰው በተቀሩት ባለመቶ ኖት ብሮች ላይ ቆጠራ ሲያደርጉ 600 በር ጉድለት ማሳየቱን ገልጸው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምተሃታዊ ማጭበርበር እንደተፈጸመባቸው የምስክርነት ቃላቸውን ስጥተዋል።
ለደንበኞቻቸው ክበር እና ዴታ የሌላቸው አንዳንድ ስረአት አልበኛ የባንኩ ሰራተኞች ጉዳዩን እንደሚያውቁ የሚናገሩ አንድ በንገድ ስራ ላይ የተሰማሩ የባንኩ ደንበኛ የታሸገው ገንዘብ ይቆጠርልኝ ብለው ጥያቄ የሚያቀርቡላቸውን ተገልጋዩች እንደሚያመናጭቁ ገልጸው ጡንቻው ፈርጠም ያለ እና የመናገር ችሎታ ያለው ተገልጋይ ሲገጥማቸው ሰራተኞች የጎደሉ እሽግ የብር ኖቶች በእጅቸው መዝነው ስለሚለዩቸው ትክክለኛ የሆኑ ርብጣ ብሮች ለናሙናነት ቆጥረው ለተገልጋዩ በማሳየት በተለመደው መተሃታዊ ስልታቸው ለፍቶ ጥሮ ግሮ የሚያመጣውን የኔ ቢጤ የባንኩን ተገልጋይ ያስለቅሳሉ ብለዋል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሽጎ ለተገልጋዩ ያስረከበውን ጥሬ ገንዘብ ከደንበኞች የባንኩ ሰራተኞች ሲረክቡ እንደሚቆጥሩ የሚናገሩ ቅሬታ አሰሚዎች የታሸገው ገንዘብ ለሚያሳየው ጉድለት መፍትሄ ከመሻት ይልቅ ደንበኛው ሃላፊነት እንዲወስድ በማስፈረም በባንኩ ማህተብ ለተፈጸመው ጸያፍ ተግባር ሽፋን ለመስጠጥ ተገልጋዩን ሲያመናጭቁ እና ሲገላምጡ ይስተዋላል ብለዋል ። 
ይህ በባንክ ሽፋን በዜጎች ላይ በጠራራ ፀሃይ በሚፈፀመው ዘረፋ የገዢው ፓርቲ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ባለስልጣናት እጅ ይኑርበት አይኑርበት እስካሁን በተጨባጭ የተረጋገጠ ነገር እንደሌለ የሚናገሩ ምንጮች የኢትዮጵያን ንግድ ባንክ አካባቢ እያገረሸ የመጣውን የተለመደ ግን ለጆሮ የሚቀፍ አሰራር ማየት ተስኖት ስለባንኩ አትራፊነት በየአመቱ የሚደሰኩረው ገዢው የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት በግንባር ቀደም ሊጠይቀበት እንደሚገባ ያሰምሩበታል ።
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መንግስት በሃላፊነት ቦታ ላይ ያስቀመጣቸው አንዳንድ ሃላፊዎች እንዳይንቀሳቀስ ከታገደ ሂሳብ ሚስጥራዊ የይለፍ ቁጥሮችን በስልጣናቸው በመውሰድ በወል የማይታወቅ ገንዘብ በተለያዩ ቤተስቦችቻው ስም ከባንኩ በማውጣት ለግልጥቅማቸው ሲያውሉ በፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን እጅ ከፍንጅ ተይዘው ውህኒ ሲወርዱ ማየት የተለመደ በመሆኑ ግዜ ጥብቆ በተገልጋዮች ላይ እያገረሸ የመጣው ይህ መተሃታዊ ማጭበርበር ስረአቱ የፈጠረው የዚሁ ብልሹ አሰራር አንዱ አካል መሆኑን አያሌ ታዛቢዎች ይናገራሉ፡፡፤በዚህ ዙሪያ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሃላፊዎች ለማነጋገር ያደረኩት ሙከራ ለግዜው አልተሳካም 

እኔ እኮ ከማይገባኝ ነገር ውስጥ የኢትዮጵያ ህዝብ እምቢ ካለ… አምባገነኖች ምን መብት ይኖራቸዋል፡፡

May 25/2014
‪#‎አብቢን‬ ‪#‎ሳምቮድሶን‬
እኔ እኮ ከማይገባኝ ነገር ውስጥ የኢትዮጵያ ህዝብ እምቢ ካለ… አምባገነኖች ምን መብት ይኖራቸዋል፡፡ የሶሊያና ቤት ተበረበረ እና ፍሪጁ ጀርባ ወይ ምናምን ስር የግንቦት ሰባትን መርህና ራዕይ የያዘ ወረቀት በማግኘታቸው በዚህ አሳብበው ሊከሷት አስበዋል ምናምን እያልን እንዘግባለን እንፅፋለን፡፡ በራሪ ወረቀቱን ያመጡት ራሳቸው ፖሊሶች መሆናቸውን ስለነቁ እናቷ አልፈርምም አሉ ምናምን አንላለን፡፡
እኔ ግን እዚህ ላይ መድረስ አልፈልግም፡፡ እውነታውና ስለስርዓቱ ስርዓት አልበኝነትና የሚሰራቸውን ሁሉ ላለመደገፍ ከዚህ በፊት ማንም ሰው የፈለገው ጉዳይ ላይ የሚያጠነጥን መፅሃፍ ይዞ ሲያነብ ቢገኝ ችግሩ ምንድን ነው ስለዚህ የነፃ ፕሬስ ህጉ ጋር የሚጣረስ ከነፃ የመናገር የመፃፍና የመናገር ህግና መብቱ ጋር የሚጋጭና የሚጣረስ መሆኑ ብቻ የመንግስትን ሴራ ልናወግዝ እንችላልን በቂ ነው፡፡
የኔ መከራከሪያ ሃሳብ ያለው እዚህ ላይ ነው፡፡ አንድ መንግስት ወይም ስርዓት የስልጣን ዘመኑን ለማራዘም የፈለገውን መንገድ ይጠቀማል፡፡ ይገድላል፡፡ ያስራል፡፡ ያደረሰበት ሳይታወቅ ብርቅየ የሃገር ልጆች ደመ ከላባት ሆነው ይቀራሉ ወዘተ…
የኔ ጥያቄ መንግስት ስለሚገድልበት ስለሚከስበት ስለሚያስርበት ስለሚያሰቃይበት ምክንያት ገለመሌ አደለም…የኔ ሃሳብ ህዝብ የፈለገውን በፈለገው ሰዓትና ቦታ የመስራት መብት ሊኖረው ይገባል፡፡ ማንም ላይ በተግባር የተገለፀ ጉዳት አድርሶ እስካልተያዘ ድረስና ጉዳት እስካላደረሰ ድረስ፡፡ አደለም ማንበብ፡፡ አደለም መፅሃፍትን ይዞ መገኘትና ማንበብ መፃፍ መግዛት ወንጀል ስለመባላቸው አስፈላጊነት ለመናገር ይቅርና ማንም ሰው ከፈለገ ለምን ከሳይጣን የባሰ አለ እንዴ ለምን የሳይጣንን መመሪያኛ ራዕይና የስራ መርህ ይዞ አይገኝም፡፡
ኧረ ስዎች ምንድን ነው እየሆንን ያለነው፡፡ አፍተር ኦል እኮ እኛ ስዎች ነን፡፡ ማን ነው እኛን ወክሎ ህጉን እያረቀቀና እያወጣ ያለው የሚለውንም ማየት ያሻናል እኮ…እኛ የመረጥናቸው ቢሆኑም እንኳን የመቃወም በተግባርም ሆነ በመርህ ደረጃ የመቃወም መብት አለን እኮ፡፡ አደለም እኛ ፈልገንና ፈቅደን በምርጫ ባሎት ያልወከልናቸው የሚያወጡትን ህግና ደንብ ማፍረስ ይቅርና…
ሮበርት ኤ. ሄንሌን እንደሚከተለው ያለ እኮ ወዶ አደለም ይህ ነው መርሃችንና ህጋችን መሆን ያለበት
…"እኔ ነፃ ነኝ፣ ምንም ያህል የህግ እና መመሪያ ጋጋታ ቢከበኝም ቅሉ የምታገሳቸው ከሆነ ብቻ እታገሳቸዋለው፤ እኔን ግጥም አድርገው የሚያስሩኝ እና ነፃ የማያደርጉኝ ከሆነ አላከብራቸውም እጥሳቸዋለው…ምክንያቱም ነፃ ነኝ!! ምክንያቱም እኔ ራሴ የህሊና እና ሞራል ሃላፊነት አለብኝ ለእያንዳንዱ ለምሰራው ሁሉ…"
ያለው እኮ ለዚህ ነው፡፡ ፀረ-ሽብር አዋጁን አምነን ተማምነን የመረጥናቸው አካላት አውጥተውት ተቀብለናል እንዴ…? ተቀብለናል? በቃ ካልተቀበልን ለምን ወረቀቱን ፖሊስ ነው ያመጣው ገለመሌ ወደሚል እንገባለን፡፡ ለምን ክፍተትና ቀዳዳ እንፈጥርላቸዋለን፡፡ ለምን እንደተቀበልነው ሁሉ ስለአፈፃፀሙ እንከራከራለን? ለምን ስለአተገባባር ክፍተቱ እናወራለን፡፡ የኛ ጥያቄ ያለው እኮ ገና ህጉን አለመቀበል ላይ ነው፡፡ ሶልያና ቤት ምንም ላይ የሚያጠነጥን ወረቀት ይገኝ ጥያቄያችን ግን መሆን ያለበት
ሶልያና ለምን በአርቲቡርቲ የፍርድ ቤት የስካር ደብዳቤ /እንዲያውም በፍ/ቤት ተፅፎ ከሆነ/ እንዳሻቸው ይፈትሻሉ? እሽ ይፈትሹም፡፡ ለምን የመናገር የመፃፍና የማንበብ መብቷ አይከብርላትም ነው መሆን ያለበት የዛሬዋ ገፈት ቀማሽ እርሷ የነገ ደግሞ እኛ ስለሆንን፡፡ ግራ አንጋባ እንጅ ስዎች!!!
…ሶልያና የፈለገችውን ምንበብ መብት አላት፡፡ ምንም እቤቷ ይገኝ ምን ሶልያና ወንጀለኛ ልትሆን የምትችለው አሸባሪ ሆና ጥፋት ካደረሰች ብቻ ነው… ፀረ-ሽብር ህጉን እኛ አልተቀበልነውም፡፡ ሶልያና አትቀበለውም /አስፈራርተው በዶክመንትሪ ብቻ እቀበላለው እንዳያስብሏት እንጅ/ ሁላችንንም ወህኒ ለማውረድ የተፈበረከ ዝክንትል ነው እንጅ ማን ይሁን አለና ህጉን ለመቀበል ኢቭን ባለስልጣናቱ ራሳቸው እኮ አይቀበሉትም እኮ… ለአፈና እንደሆነ ስለሚያውቁት ግን ለስጣናቸው ብቻ ሳይሆን ስልጣናቸውን ቢለቅቁ እና ሌላ ሃይል በምንም መንገድ ቢረከብ የሚደርስባቸውን ካጠፉት አንፃር ስለሚያስቡት ሁሉ ምንም በማድረግ ለህዝቡን /ለእነርሱ ለጠላታቸው/ ክፍተት ላለመክፈት እንጅ፡፡
እኛ በመረጥናቸው ስለዜጎች መብት /የእኩልነት ጉዳይ ገና ሳይነሳ እንኳን/ በቆሙ ተወካዮቻችን የወጣ ህግ ባለመሆኑ…አንቀበለውም፡፡ በመረጥናቸው ቢወጣ እንኳን ከመቃወም እስከ አለመቀበል መሄድ መብት አለን ምክንያቱም ዲሞክራሲያዊ እና ሰብአዊ/ተፈጥሯዊ/ መብቶቻችንን እስካላከበረ ድረስ ህግ እግሩን ይብላ አንቀበልም ማለት መብታችን ነው ዲሞክራሲያዊ ሳይሖን ሰው በመሆናችን ብቻ ያገኘነው መብት ነው፡፡ ከእንሰሳት የምንለይበት ዋናው ጉዳያችን እኮ ማማዛዘን ይህኛው መልካም ይህኛው ክፉ ብለን መፈረጅ መቻላችንስ አደል እንዴ፡፡
በምድረ ኢህአዴግ ካድሬ ፓርላማ ተወካይ የፀደቀና ለስልጣን ማራዘሚያ ዜጎች ስለመብታቸው እንዳይቆሙ ማሸማቀቂያና ከዛሬ ነገን ለመጠቀም ሲፈልጉ ብቻ ገዥ ሳናደርገው ገዥ የሆነብን፤ ስርዓት ሳይኖረው ስርዓት ነኝ እያለ ራሱን እንደ ነፃ አውጭ አድርጎ የሚጠራው የኛ መንግስት ሳንለው መንግስታችሁ ነኝ የሚለው ግፈኛ አገዛዝ የጫነን ዳውላ ነው እንጅ ማን ተቀበለውና እስቲ ይህንን ብጣሽ ፅሁፍ ከምታነቡት ውስጥ የሚቀበለው አለ? ይህንን ፀረ-ሽብር ህግ /ምናልባት ለነፃነት እና መብታችን መታገላችን ለጊዜው ሳያውቁ አውቀውም ለሆዳቸው ሲሉ ብቻ የሚቃወሙት ሆድ አደሮችና ፍርፋሪ ለቃሚዎች ሊቀበሉት ይችላሉ/ ነገር ግን ሲውል ሲያድር እንደ አቶ ኤርሚያስ ለገሰ አብረው ያወጡትን አንድ ወቅት አብረው የጨፈሩለትን ስንቶችን ከርቼሌ የከተቱበተን ህግ ቀን ሲጥላቸው እና ቀን ሲያነሳቸው ስርዓቱን ሲከዱ ዜጎችን ለማፈን የተጠቀመበት ዘዴ ነው ገለመሌ እያሉ ምንም እንኳን እኛ እና እውነቱ የሚሻውን ቢሉም እንኳን እነዚህ ስዎች ለፍርድ ከምቅረብ ውጭ እኛን ወክለው ስለ እኛ የመናገር ሞራል ሊኖራቸው አይገባም፡፡ ፀረ-ሽብር ህጉን ያብጠለጥላሉ ልክ እንደ እኛ ግን ያወጡት እነርሱ ናቸው እኮ /አይ ሰው ለሰው ሞት አነሰው አለች…/፡፡
ስለዚህ መሰረታዊ ጥያቄያችን ሶልያናን በምንም ያዛት በምን በምንም አሰራት አሰቃያት በምን… ለምን መታሰር አስፈለጋት የፈለገችውን ቤቷ ውስጥ ይዛ ብትገኝ እስካላሸበረች ድረስ ለምን ወደ ወህኒ ትሄዳለች ለምን ቤቷ ያለፈቃዷ ይፈተሸል /አንዲት የፍ/ቤት ትዕዛዝ ብቻ ስለተጣፈች/ ፍርድ ቤቱ የማን ነውና በማን ስር ነውና…ቀድሞ ነገር ለምን ስላነበበች /ያነበበችው ምንም ይሑን ምን ስለምንም ይሑን ስለምን ስለማንም ይሁን ስለማን/ ለምን ትታሰራለች ነው እንጅ መሆን ያለበት፡፡ ወረቀቱን ራሱ ፖሊስ አምጥቶ ሲያበቃ…ገለመሌ ለምን እንላለን፡፡
አሁንም የምለው የትግል መሰረታችን እጅግ ከስሩ መሆን አለበት፡፡ ይህን አልን ማለት እኮ ለፋሽሽቱ በር እየከፈትንለት ህጉን እንደተቀበልን ግን ስለሶልያና ስናወራ ስንጠይቅ ችግራችን ሶልያናነ ያልያዘችውን እንደያዘች ተደርጋ ወንጀለኛ ተባለች ባልን ቁጥር እርሷን ወደ ባሰ አዘቅት ውስጥ እየከተትናት መሆኑን መዘንጋት የለብንም ኦኬ…እርሷ ምንም ነገር በምንም ጉዳይ ላይ የማንበብ መብት አላት ነው ዋናው፡፡
የማንበብ የመፃፍ የመናገር መብት ሆኖ ዋናው ህግ ህገ መንግስቱ ላይ ከተጻፈ ምንም ስለማንበቧ ለምን ለማሰሪያ ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ ቀድሞ ነገር ይህ ፓርላማ የሚያወጣው የትኛውም ህግ የኢትዮጵያን ህግ ሊወክለን አይገባም!!! አለቀ፡፡ ኢቭን ለካድሬዎችና ለኢህአዴግ ደጋፊዎች እንኳን አይወክልም ምክንያቱም ኢትዮጵያዊ ናቸውና፡፡
ሶልያና ስላነበበች ታሰረች ለምን ነው ማለት ያለብን ስዎች!!
#አብቢን ነኝ
ኢትዮጵያኝ እ/ር ይባርክ

በአዲስ አበባ ቀላል የከተማ ባቡር መስመር ዝርጋታ ከምሥራቅ ወደ ምዕራብ በሚገኘው የአያት መገናኛ መስመር ላይ የተነጠፈው ሐዲድ፣ ከመሥፈርቱ ውጪ በመሆኑ ምክንያት በሌላ ሐዲድ በመቀየር ላይ ነው፡፡

May 25/2014
babur
ከሳምንት በፊት የተጀመረው ቀደም ሲል የተዘረጋውን ሐዲድ የመቀየር ሥራ በአሁኑ ወቅት ከአያት ወደ ሲኤምሲ አካባቢ መድረሱን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ጉዳዩን በተመለከተ የፕሮጀክቱ ኮንትራክተር የሆነውን ቻይና ሬልዌይ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽንና የፕሮጀክቱ ተቆጣጣሪ የሆነውን ስዌድሮድ የተባለ የስዊድን ኩባንያ ሪፖርተር ለማነጋገር ቢሞክርም፣ በኮንትራት ስምምነቱ መሠረት ለሚዲያ መግለጫ መስጠት እንደማይችሉ ገልጸዋል፡፡

ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ግን የፕሮጀክቱ ኮንትራክተር የመጀመሪያውን ሐዲድ የማንጠፍ ሥራ ሲጀምር፣ በኮንትራት ስምምነቱ ላይ በተቀመጡት መሥፈርቶች መሠረት እንዲሠራ ተነግሮት ነበር ብለዋል፡፡
በኮንትራት ስምምነቱ ላይ የተቀመጠው መሥፈርት አንዱ ባለ 25 ሜትር ሐዲድ ከሌላኛው ጋር የሚገናኘው በኦክስጅን ብየዳ እንደሆነ ቢገልጽም፣ ኮንትራክተሩ ግን የተቀመጠውን መሥፈርት እያወቀና በተቆጣጣሪ (አማካሪ) ድርጅቱ በተደጋጋሚ እየተነገረው ሐዲዱን መዘርጋት እንደቀጠለበት ምንጮች አስረድተዋል፡፡
አማካሪ ድርጅቱ ባለበት ኃላፊነት መሠረት ጉዳዩን ከማሳሰብ ባለፈ ለተዘረጋው ሐዲድ የሚቀርብ የክፍያ ጥያቄን እንደማያጸድቅ ግልጽ በማድረጉና በሌሎችም ምክንያቶች፣ ኮንትራክተሩ የስምምነት መሥፈርቱን ለማክበር እንደተገደደ ያስረዳሉ፡፡
ከአያት መገናኛ ባለው መስመር ላይ ተነጥፈው የነበሩት ሐዲዶች ብዛት 960 ሲሆኑ፣ እያንዳንዳቸው 25 ሜትር ርዝመት እንዳላቸው የሚያስረዱት ምንጮች፣ እየተነሱ ያሉት በመሥፈርቱ መሠረት መበየድ የማይችሉ ሆነው ስለተገኙ እንደሆነ ገምተዋል፡፡
‹‹ሙሉ በሙሉ መቀየር አለባቸው፡፡ ይህ ማለት ግን አገልግሎት አይሰጡም ማለት አይደለም፡፡ ምናልባት ከአዲስ አበባ ጂቡቲ ለሚዘረጋው የባቡር መስመር ሊያገለግሉ ይችላሉ፤›› በማለት አስረድተዋል፡፡
አሁን ለተፈጠረው ችግር ምክንያቱ ኮንትራክተሩ እንደሆነ፣ ወጪውም ሙሉ በሙሉ የራሱ እንደሚሆን የሚያስረዱት ምንጮች፣ በዚህ ምክንያት የፕሮጀክቱ ጊዜ ተስተጓጉሏል ማለት እንደማይቻል ይገልጻሉ፡፡
የሚሰጡት ምክንያት ደግሞ ሐዲድ ማንጠፍ በዚህ ፕሮጀክት ላይ ቀላሉ የሥራ ዓይነት መሆኑን፣ በአጠቃላይ 34 ኪሎ ሜትሩ ላይ ሐዲድ የማንጠፍ ሥራ በአንድ ወር ማጠናቀቅ የሚቻል መሆኑን ይገልጻሉ፡፡
ጉዳዩን በተመለከተ የአዲስ አበባ ቀላል የከተማ ባቡር ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር በኃይሉ ስንታየሁ ተጠይቀው፣ የተነጠፈውን የሐዲድ መስመር የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቱ አፅድቆ እንዳልተረከበ ተናግረዋል፡፡
የኮንትራት ስምምነቱ የሐዲድ መስመሩ ‹‹ኮንቲኒየስሊ ዌልድድ›› ወይም አንድ የሐዲድ ብረት ከሌላኛው ጋር ያለምንም ክፍተት ተበይዶ መያያዝ እንዳለበት ያመለክታል ብለዋል፡፡ በመገናኛ አያት መስመር ላይ የተዘረጋው በዚህ መሠረት ሳይሆን ብሎን በማያያዝ በመሆኑና ይህ ደግሞ መሥፈርቱን የማያሟላ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
ሪፖርተር በሥፍራው ተዘዋውሮ እንደተመለከተውና በፎቶግራፉ ላይም እንደሚታየው ቀደም ሲል የተነጠፉት ሐዲዶች እየተነሱ ነበሩ፡፡
የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር በኃይሉ ግን፣ ‹‹እየተነሱ ያሉትን በማሳሰብና በማጠጋጋት ለመበየድ ነው እንጂ የሐዲድ ብረቶቹ እየተቀየሩ አይደሉም፤›› በማለት ያስተባብላሉ፡፡
የሐዲድ ማንጠፍ ሥራው ከመጀመሪያውኑ በመሥፈርቱ መሠረት ለምን በብየዳ አልተሠራም በማለት ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ ‹‹መጀመሪያና መጨረሻ የሚባል ነገር በአሁኑ ወቅት የለም፡፡ እኛ ገና አልተረከብናቸውም፡፡ ምክንያቱም ገና ሒደት ላይ ነው ብለዋል፤›› ብለዋል፡፡
ቀደም ሲል የተነጠፉትን ሐዲዶች በሌላ የመቀየር፣ እርስ በርስ የመበየድና የማያያዝ ተግባር በጐተራ መስመር ላይም መጀመሩን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በዚህ ላይም የተጠየቁት ኢንጂነር በኃይሉ፣ የተነጠፉት ሐዲዶች እርስ በርስ ባልተበየዱባቸው ወይም በብሎን ብቻ በተያያዙባቸው ቦታዎች ላይ ሁሉ የመበየዱ ሥራ እንደሚከናወን ገልጸዋል፡፡
ethiopianreporter/news
የአዲስ አበባ ቀላል የከተማ ባቡር ፕሮጀክት 34 ኪሎ ሜትር ሲሸፍን፣ ከምሥራቅ ምዕራብ እንዲሁም ከሰሜን ደቡብ የሚዘረጋ ነው፡፡ አጠቃላይ የፕሮጀክቱ ወጪ 475 ሚሊዮን ዶላር እንደሚሆን ሲጠበቅ፣ ከጠቅላላ ወጪው 85 በመቶ የተገኘው ከቻይና መንግሥት በብድር ነው፡፡

Sonntag, 25. Mai 2014

ፖሊስ አቶ አስራት አብርሃን አስሮ “ያሉበትን አላውቅም” አለ

May 25/2014
የአራት ፓርቲዎች መድረክ የሆነው መድረክ ትናንት በአዲስ አበባ ላደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ቀደም ብለው የቅስቀሳ ስራ ሲሰሩ የነበሩ አስራ ሁለት ሰዎች በቡራዩ ከተማ በፖሊስ መታሰራቸውን የሰሙት የአረና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ሐብታይ ገብረ ሩፋኤልና በቅርቡ አንድነት ፓርቲን የተቀላቀለው ደራሲና ፖለቲከኛ አስራት አብርሃ እስረኞቹን ሊጠይቁ በሄዱበት በወረዳው ከታሰሩ በኋላ ፖሊስ አቶ ሐብታይን ሲለቅ አቶ አስራትን በወረዳው አሳድሯቸው ነበር፡፡
ዛሬ ማለዳ አቶ አስራትንና የመድረክ አባላትን ለመጠየቅ ወደ ቡራዩ ያመሩት የአቶ አስራት ባለቤትና የአንድነት ከፍተኛ አመራሮች አቶ አስራት በፖሊስ ጣብያው አለመታሰራቸው ተነግሯቸዋል፡፡አቶ ሐብታይ በስፍራው በመገኘት ‹‹አስራት ከእኔ ጋር ታስሮ ነበር››ቢሉም የኦሮሚያ ፖሊስ ‹‹የምትሉትን ሰው እኔ አላሰርኩትም››የሚል ምላሽ ሰጥቷል፡፡
በቡራዩ ከተማ ሶስት ፖሊስ ጣብያዎች በመኖራቸው አስራትን ፍለጋ ወደ ፖሊስ ጣብያዎቹ ያመሩት የአንድነት አመራሮች ተመሳሳይ ምላሽ ተሰጥቷቸዋል፡፡
አብርሃ ደስታ በበኩሉ የአቶ አስራትን መታሰር በማስመልከት የሚከተለውን በፌስቡክ ገጹ አስፍሯል፦
ፖለቲከኛ አስራት አብርሃም በደህንነት ሰዎች ከቡራዩ ታፍኖ ወዳልታወቀ ቦታ ተወሰደ። ምንም ወንጀል ሳይሰራ በቡራዩ ከተማ ለሰለማዊ ሰልፍ ሲቀሰቅሱ የታሰሩ የመድረክ አባላትን ለመጠየቅ በመሄዱ ምክንያት ታፍኖ ከተወሰደ የሕገወጥ ዓማፂ ቡድን አባል ቢሆን ኑሮስ ምን ያደርጉት ነበር? ደሞ ሰለማዊ ሰዎችን እያፈኑ ከደርግ እንሻላለን ይሉናል! ደርግ ኮ እያፈነ የገደለን ሕገወጥ ዓማፂ ቡድን (ህወሓት) ስለነበረ ነው። በደርግ ግዜ ህወሓት ዓማፂ ሕገወጥ ቡድን ነበር። የህወሓት አባል የሆነ ወይ ህወሓትን የተባበረ ሁሉ እርምጃ ሲወሰድበት ደርግን እንቃወመው ነበር። አሁን ደግሞ ሰለማዊ ሕጋዊ ታጋዮችን እየታፈኑ የሚወሰዱበት ግዜ ላይ ደረስን! አሁን እንደ ህወሓት ያለ ሕገወጥ ድርጅት (ዓማፂ ቡድን) ቢኖር ኑሮስ ምን ያደርጉን ነበር? ወይ ግንቦት 20!

በአውሮፕላን ጎማ ስር ተደብቆ 5 ሰአት በአየር ላይ የተጓዘው ተአምረኛ ወጣት እናት ያለችው ኢትዮጵያ ነው

May 25/2014
ባለፈው ሰሞን ከካሊፎርኒያ ተነስቶ ሃዋይ ድረስ በአውሮፕላን ጎማ በመንጠላጠል የተጓዘው ወጣት ህይወት መትረፍ ተአምር መሰኘቱን መዘገባችን ይታወሳል። ይህ የ 16 ዓመት ወጣት ሶማልያዊ መሆኑ ሰሞኑን ሲዘገብ፣ እናቱ ደግሞ ያለችው ኢትዮጵያ መሆኑ አብሮ ተነስቷል።
ሶማሌያዊዋ እናት ምርጊቱ ከጭቃ በተሰራ ደሳሳ ጎጆ ውስጥ ተቀምጣለች። ግድግዳው ከመሳሳቱ የተነሳ ነፋስ እንዳያስገባ በአሮጌ አንሶላ ተሸፍኗል። ያለችው ሸደር በተሰኘ የስደተኞች መጠለያ ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ነው። እንግዲህ የካሊፎርኒያው የ 16 ዓመት ወጣት ሶማሌያዊ አውሮፕላን ላይ የተንጠለጠለው እዚህች ስደተኛ እናቱ ጋር ኢትዮጵያ ለመምጣት በመፈለጉ ነበር።
ዩባ መሃመድ የተባለችው ይህችው እናት፣ እሷን ናፍቆ አውሮፕላን ላይ ተንጠለጠለ የተባለው ይህን ልጇን ላለፉት 8 ዓመታት አላየችውም። ጸጉሯን የሸፈነችበትን ነጭና ጥቁር ሂጃብ እያሻሸች፣ ያህያ አብዲ ስለተባለው ይኸው ወጣት ልጇ ስትናገር በእምባ ጭምር ነው። ለ 5 ሰአት ተኩል በአውሮፕላን ጎማ ተንጠልጥሎ ከአገር አገር ሄደ መባልን ስትሰማ እንደተንቀጠቀጠች ትናገራለች።
ወጣቱ ያህያ አብዲ ካሊፎርኒያ ሊያሳድጉት በወሰዱት ቤተሰቦች ዘንድ ደስተኛ አልነበረም። ደስተኛ ያልሆነው በነሱ አያያዝ ሳይሆን፣ እናቱን እጅግ በመናፈቁ ነበር። እናም ናፍቆቱ ሲብስበት ባለፈው ኤፕሪል 20 ቀን ፣ ከቤቱ በመውጣት ሳንሆዜ ከተማ ባለው አለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አጥር ጥሶ ገባ። እናም በልጅነት ሃሳቡ ፣ ወደ እናቱ ሊወስደው የሚችለው አውሮፕላን ነውና ፣ ያገኘው አውሮፕላን ጎማ ላይ ተንጠላጠለ። አውሮፕላኑ ደግሞ እንዳጋጣሚ ወደ ሃዋይ የሚሄድ ነበረ።
እሱ እንደተንጠለጠለ ፣ አውሮፕላኑ ተነሳ፣ ጎማውን አጠፈና ወደውስጥ ከተተ፣ ያህያ አብዲም አብሮ ውስጥ ገባ። ከዚያ በኋላ ነው አምስት ሰአት ተኩል ፣ በነጌቲቭ 50 ዲግሪና በ32ሺ ጫማ ከፍታ የተጓዘው። በዚያ ቅዝቃዜና ኦክስጅን አየር በማይገኝበት ሁኔታ በህይወት መድረሱ እጅግ ተአምር ተሰኝቷል።
“በጣም ጎበዝ ልጅ ነው ..” ትላለች ዩባ ስለልጇ ስትናገር .. “ጎበዝ ልጅ ነው፣ በጣም ይወደኛል፣ እኔን ለማየት እንደሚፈልግና እንደሚናፍቅም በልቤ አውቃለሁ። ግን አባቱ በፍጹም ከኔ ጋር እንዲገናኝ አይፈልግም፣ ለዚህ ነው “እናትህ ሞታለች” ብሎ የነገረው”
አሁን በቅርብ ግን ወጣቱ ያህያ እናቱ በህይወት መኖሯን በወሬ ወሬ ሰማ። ከዚያ ወዲህ ናፍቆቱ ባሰበት። አባቱና ሶስት ወንድሞቹ አብረውት ካሊፎርኒያ ቢኖሩም ፣ እሱ ግን ድሮም ለ እናቱ ልዩ ፍቅር ነበረው።
በምስራቅ ኢትዮጵያ የሚገኘው ሸደር የስደተኞች ካምፕ ውስጥ ከ10ሺ በላይ ሶማሌያውያን ስደተኞች አሉ። ከነዚያ አንዷ የሆነችው የያህያ እናት የ 33 ዓመት ወጣት ስትሆን፣ ላለፉት 4 ዓመታት እዚያ ቆይታለች። በስደተኞቹ ካምፕ ውስጥም አትክልት በመሽጥ ትንሽ ገንዘብ ለማግኘት ትሞክራለች።
ባለፈው ዓመት ታዲያ ከካምፑ ወጥተው ካሊፎርኒያ መምጣት የቻሉ ኡዌይ እና ጃማ የተባሉ ስደተኞች፣ ካሊፎርኒያ ክደረሱ በኋላ ለያህያና ለሌሎቹም ወንድሞችና እህቶቹ “እናታቸው በኢትዮጵያው ሸደር ጣቢያ እንደምትገኝ” ይነግሯቸዋል። በዚያ ጊዜ የተፈጠረውን ሁኔታ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ መስሪያ ቤት ሃላፊ ፋቲ ሊዩኒ ሲናገሩ … “ልጆቹ በአባታቸው እንዴት ሞታለች ትለናለህ ብለው በጣም ተበሳጩ፣ አሁኑኑ ያለችበት ቦታ ካልሄድንም ብለው ተነሱ፣ አባታቸው ግን “ውሸት ነው ሞታለች” እያለ ይከራከራቸው ነበር” ነበር ያሉት።
ከዚያች ቅጽበት በኋላ ነው የ 16 ዓመቱ ወጣት ያህያ እናቱን ለማግኘት ቆርጦ የተነሳው። እናት ዩባ አብዱል ፣ ልጇ በአውሮፕላን ተንጠላጥሎ እሷን ፍለጋ መሄዱን የሰማቸው አሜሪካ ከሚኖርና ከምታውቀው ክበበው አበራ ከተባለ ሰው መሆኑን ትናገራለች። ከዚያ ወዲህ ከልጇ ጋር ለመገናኘት እሷም ውላ ማደር አትፈልግም። ሁሉም ተባብሮ እንዲያገናኛት ልመና ይዛለች።
ምኞቷም እውን ሊሆን የሚችልበት መንገድ መኖሩን የስደተኞች ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ይናገራል። አሁን ወደ አሜሪካ ሊወሰዱ ከሚችሉ ስደተኞች መካከል አንዷ ሆና የመጀመሪያውን ቃለመጠይቅ አልፋለች:፡ ሁለተኛውን ማጣሪያ ደግሞ ካለፈች በአንድ ዓመት ውስጥ አሜሪካ ልትሄድ ትችላለች። ተሳክቶላት ከመጣችም እሷን ለማግኘት ህይወቱን አደጋ ውስጥ ጥሎ በአውሮፕላን የተንጠለጠለውን ልጇን ታገኘው ይሆናል።