Netsanet: መጀመሪያ የልዩኘቶቻችን ሃኪም ሆነን ልዩነቶቻችን ማጥበብ ካልቻልን

Dienstag, 20. Mai 2014

መጀመሪያ የልዩኘቶቻችን ሃኪም ሆነን ልዩነቶቻችን ማጥበብ ካልቻልን

May 19/2014
መጀመሪያ የልዩኘቶቻችን ሃኪም ሆነን ልዩነቶቻችን ማጥበብ ካልቻልን ደግሞ ጊዜያችን እዚህ ላይ ሳናጠፋ ይህንን ልዩነታችን እየሸነቆረ እንዲያመረቅዝ ከሚያደርገን ስርዓት የሌለው ስርዓት ጋር ግብግባችን መቀጠል አለበት ነገር ግን ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ይህንን ስርዓት ማስወገድ ላይ ወይስ ልዩነታችን ማጥበብ ጋ.............?
................................................................................................................................... ...................................................
ይህን ስርዓት ያጣ ስርዓት የግፍ የእንግልት የእስር የሞትና ጣር ዘመን ያበቃ ዘንድ ማስወገድ ከፈለግን በምንም አይነት መልኩ በመካከላችን ያለውን ልዩነት ማጥበብ ላይ ብቻ መወዛገቡን ትተን ዋናው የጋራ ጉዳያችን ላይ ካላደረግን በከንቱ እንደቁራ መጮህ ነው የሚሆነው፡፡ ይህን የጋራ ትግላችን አቅጣጣ የስርዓት ለውጥ ማምጣት እና የጨለመውን የህዝባችን ተስፋ ብርሃን ማድረግ ስርዓቱን መናድና በህዝባዊ ስርዓት መለወጥ እንዲሁም ለዛም የጋራ መስዋዕትነትን መውሰድ ግድ ይላል፡፡

ኢህአዴግ ከኢትዮጵያዊያን የሚፈራው ነገር ቢኖር አንድነታችንና አብሮነታችን ነው፡፡ አስር እና ከዚያ በላይ ኢትዮጵያዊያን ከተለያየ ቋንቋ ተናጋሪ አካባቢዎች አብረው ወክ እንዲያደርጉ እንኳን አይሻም ምክንያቱም አንድነታችንና አብሮነታችን የሚፈልገው ለጥፋትን ለመለያየት ከሆነ ብቻ እና የራሱ ብሄራዊ የሚመስሉ ለስልጣኑ የሚያሰጉት ሃይሎች ጋር ለሚያደርግው ጦርነት ብቻ ነው፡፡ ይህ የሴራው የመበታተኛው ኢትዮጵያ የምትባል ሃገር ኖራ አንድነቷ የተጠበቀች ያለማየት ፍላጎቱ ወደተግባር ቅየራ የመጀመሪያ እርምጃ ነው፡፡

ይህ ህዝብ በምንም ለኢህአዴግ በሚመች መልክ በልዩነቱ ሌላ ልዩነት የሚጨማምርና በጊዜያዊ ብስጭትም ሆነ የብቀላ መንፈስ እየተከፋ ቢቀጥልና ቢሳሳት የሚመቸው ለኢህአዴግ ነው፡፡ ኢህአዴግ ራሱን የሚጠብቀው እኛ ባልፈለግነው ሁሉ እና ባልመረጥነው መስመር በመጓዝ ነው፡፡ እርሱ ስልጣኑን የሚያቆየው በእርስ በእርሳችን መበላላትና መተላለቅ በእርስ በእርሳችን መከፋፈልና አንድነት ማጣት ነው፡፡
አንድ ምሳሌ እንውሰድ፡-

አንድ አንበሳ በአንድ ወቅት ድኩላ ለማደን ይፈልግና በጣም ከመጎምጀቱ የተነሳ አፉን ክፍቶ አይኑን ድኩላው ላይ አፍጥጦ ልጋጉን እያዝረከረከ ድምጥማጡን አጥፍቶ ጫካው ውስጥ ጎድቦ ያደባል፡፡ እናም በአጋጣሚ አንዲት አይጥ ሆና የማታውቀውን ላዩ ላይ ትወጣለች በጎኑ ትሽከረከራለች፤ ትሮጣለች በአፉ ውስጥ ገብታ ትሽከረከራለች…አንበሳው ግን ምንም አይነት እንቅስቃሴ ሳያሳያት ዝም ብሎ…ታዳኙን ድኩላ ላይ ብቻ አፍጥጦ ትኩረት አላደርግላት ሲል አይጥም እየባሳት መጣና አፍንጫውን ትልሰው ገባች፤ አንበሳው ምንም አላለም፡፡ ከዚያም ድኩላው አንበሳውን ስላላየው ቅጠሉን እየበጠሰ ጅራቱን እየቆላ አንበሳው አካባቢ ሲጠጋ አይጧ ጀርባው ላይ ወጥታ ስትቦርቅ ስለነበር ከመቅፅበት መትረፍ ብሎ ዘሎ ድኩላውን ሲያንቀው አይጧም ወደቀች ድኩላውም በአንበሳው ጥርስ ተቀረጠፈ፡፡

…የዚህን ታሪክ ሞራል ስናስብ አንበሳ አይጥዋን ለምን አልበላትም? ካልን ምክንያቱም አይጡዋን ሲያሯሩጥ ጊዜውን መግደል ሌላም ተላቱ እንዲነቃበትና አቅጣጫ እንዲቀይርበት አይሻም ምክንያቱም ይችን አይጥ ሲበላ #ሲጥ# ማለቷ አይቀርም፡፡ ስለዚህም አይጧ ምንም ብትሆን ምን ማድረግ ለእርሷና ምንም ለማታጠግበውና አላማው ውስጥ ያላስገባትን ሲል ትልቁን ዓላመውን እንደሚስት ያውቀዋል አያደርገውም፡፡

እናም እኛ የኢትዮጵያዊያን አሁን ታዳኛችን ይህ ስርዓት ያጣ ስርዓት የሌለው ስርዓት ነው፡፡ መንግስት ሳናደርገው መንግስት የሆነብንን አምባገነን ስርዓት ነው፡፡ አይጧ ደግሞ በመካከላችን ያለው ትርኪ ምርኪ ልዩነት የሚመስል ግን መሰረታዊ ችግርና የመለያያ መፍትሄ ሊሆን የማይችልና የማይገባው ክፍተት ተፈጥሯዊ እውነታዎች ናቸው፡፡

እነዚህን ተፈጥሯዊ እውነታዎች ደግሞ መቸም ቢሆን ልንፍቃቸው ልንክዳቸው አንችልም፡፡ መቼም ቢሆን እነዚህ ልዩነቶቻችንና ክፍተቶቻችን ማስወገድም አንችልም፡፡ ታዲያ እንዴት ነው ያውም ተፈጥሯዊ የሆኑ ሊወገዱ የማይችሉ ሲብስም ደግሞ መቼም ቢሆን ያለ ልዩኘት መኖር እንደማንችል ልባችን እያወቀው እነዚህ ምርጥና ውብ ልዩነቶቻችንን ልንለጥጣቸው እና ለኢህአዴግ እንዲመቹ ከማድረግ ውጭ ልናሰፋቸውና ልንቀዳቸው እንደማንችል እያወቅን ከኛ እና በኛ መካከል ያለድልድይ መኖር እንደማንችል እያወቅን የሞኝ ተራራ ግፊ ውስጥ ለምን ነው የምንገባው?
ይህንን ታሪካዊውም ሆነ ተፈጥሯዊ ልዩነቶቻችንንና ተፈጥሯዊ ክፍተቶችን እንደ አጋጣሚ በመጠቀም ሊለያየንና የትኩረት አቅጣጫችን እንድንቀይርለት የሚፈልገው አንድም ኢህአዴግና ካድሬዎቹ ሁለትም ሳያውቁ በስሜት የሚገፉ የሃገራችን ህልውና አደጋ ላይ መጣል የማይችሉ ብንረሳቸው መረሳት የሚችሉ ብናጠፋቸው መጥፋት የሚችሉ ትንሽ የወያኔና ሳይጣን መሳሪያ ሆነው የጋራ ትግላችን ላይ መሰናክል መፍጠር የሚፈልጉ አካላት ብቻ ናቸው፡፡

እነዚህን አካላት ደግሞ ታግሎ ለመሸናነፍ ማሰብና አሁንም በስሜት መነዳት ሌላው የጋራ ጠላታችን ለማስወገድ የምናደርገው መጋጋጥና መላላጥ ደንቃራ ነው፡፡ አንድ ጉዳይ ማወቅ ያለብን ማንም አለ ማን እነዚህን አካላት ቁጥር ውስጥ አስገብቶ ለመታገል ማሰብ ትልቅ የማይፈታ ሞኝነት ነው፡፡ አዎ የወገናችን ደም የኛ ደም ነው!!! ኢትዮጵያዊ የሆነ ከየትኛውም የኢትዮጵያ መሬት ይምጣ ሲሞተ ሲቆስል ሲታሰር ሲገረፍ ሲደማ ንብረቱ ሲዘረፍ ሲቃጠል ሲወድም ይህ ሃገርህ አደለም ከሃገራችን ውጡ ሲባሉ ማየት የየትኛውም አንድነትና ኢትዮጵያ የምትባል አባት እናቶቻችን ያስረከቡንን አጥንት ደማቸውን የከሰከሱላትን ምድር የሚፈልግ ሁሉ ያገባዋል ይህን በእጅጉ ያወግዛል ስዕተቱን ምንም ፈፀመው ማንም የኛ የኢትዮጵያዊያን አንድነት ናፋቂ ህዝቦችና አደራ ተቀባዮች የአንዱ መጎዳት የእኛ መጎዳት የሚሆንብን ኢትዮጵያዊያን ጉዳት ነው!!! የኛ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ጉዳት እስር እንግልት ሞት ቁስለት ግርፋት ነው፡፡ ነገር ግን #ዝም ማለታችን# ሳይሆን አንድነታችን በጠበቀ መልክ ትግላችን ለማጧጧፍና አንድ ላይ ወደ ምንፈልገው የድል ማማና ቦታ እና መስመር ውስጥ ለመግባት ነው፡፡

አማራውን ኦሮሞው ቢደግለው አማራውን ትግሬው ቢገድለው ትግሬውን ጉሙዙ ጉምዙ አማራው ቢገድለው ትግሬውን አፋሩ አፋሩን ትግሬው ኦሮሞውን ደቡብ ደቡቡን ኦሮሞ ቢገድለው አዲስ አበባውን ኦሮሞ ቢገድለው ኦሮሞውን አዲስ አበባው ቢገድለው ትግሬውን ኦሮሞው ቢገድለው ትግሬው ኦሮሞውን ቢገድለው ሶማሌውን አፋሩ አፋሩ ሶማሌውን ቢገድለው ለአንድነት ጠባቂና ናፋቂ ቁርጠኛ ታጋይ ጀግና ኢትዮጵያዊ ይህ ማለት ግን የሚያስበው አንድን ኢትዮጵያዊ ሌላ ኢትዮጵያዊ እንደገደለው እንጅ አንዱን ብሄር ሌላኛው ብሄር እንደገደለው ዘረኛና እጅግ የላሸቀ አስተሳሰብ አደለም መሆንም ለበትም እንዲህ ሚያስብ ቢኖር ግን እርሱ ወያኔ ኢህአዴግ አለቅላቂና ድስት ላሽ የኢትዮጵያዊነታችን አንድነታችን ተንቅ እሾህ ነው፡፡ እንዲሁም እንዲህ የሚያስብ አንድም ኢህዴግ ካድሬና አለቅላቂ ካልሆነም አላዋቂ ነው የሚሆነው፡፡

በቃ ደም በመቃባት ያለደምም አያለምንም ምክንያት የትኛውም ክልል ውስጥ አንዱ አንዱን በድንበር ልጅ እናቱን ወንድም ወንድሙ በቦታው ጎረቤት ሆነው አይገዳደሉም እንዴ!!! ልጅ አባቱን አባት ልጁን ገድሎ አያውቅም ወይ? እናት በልጇ ተቆራርጣ ሞታ እኮ በአይናችን አይተናል ስዎች፡፡ አባት ልጁን ቆራርጦ ገድሎት ደፍሯት ልጅ አባቱን ወንድም ወንድሙ በተለያየ ምክንያት አንዳልሆነ አድርጎ ገድሎ ማየት እኮ የተለመደ ጉዳይ ነው፡፡ ይህ ተለምዷል ብለን ግን ዝም የምንለው ሳይሆን ማንም ማንንም ሲበድል… አደለም መግደል፤ ብናይ ዝም እንላለን ለፍትህ አንታገልም ፍትህ እንዲሰፍን አናደርግም ማለት ግን አደለም ማንም ማንንም መግደል የለበትም!!! አለቀ ሰው ሰው በመሆኑ ብቻ መኖር በህይወት የትኛውም የኢትዮጵያ ክልል ተንቀሳቅሶ የመስራት ሃብት ማፍራት መብት ሊኖረውና ማንም ሊገስሰው የሚገባው ሊገስስና መብቱን የሚነካ ቢኖር ደግሞ የተሳሳተ እንደሆነ በሚማርበት መልክ ማስተማር አለያም አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወሰድበት ግፊት ከማድረግና መውሰድ ምንችል አካላትም ካለ፤ን ከመውሰድ ፍትህ ያለምንም ማዳላት እንዲሰፍን ከማድረግ ወደኋላ አንልም ኢትዮጵያዊነታችን የምንሻ አንድነታችን የምንናፍወቅ እስከሆንን ድረስ ይህ ነው ከአባቶቻችን የተረከብነው ይህ ነው ኢትዮጵያዊነት በቅንጭቡ ሲታይ፡፡

ማንም ምንንም መግደል ለበትም!! ይህን ቢያደርግ ለህግ ይቀርባል!! ፍትህ ይሰጠዋል ውሳኔውን ተሸክሞ እደማንኛውም እስረኛ ወህኒ ይወርዳል፡፡ መቼም ቢሆን ይህ ሰው የእጁንና የዋጋውን ያገኛል፡፡ ነገር ግን አማራው በኦሮሞው ስለተገደለ ዘረኛ በሆነ መንፈስ አማርኛ ተናጋሪውን ህዝብ ለማነሳሳትና ኢትዮጵያዊ አንድነቱን ረስቶ ከኦሮሞመ ወንድምና እህቶቹ ጋር እዲበላላና እንዲነካከስ የሚያደርግን ሁሉ እናወግዛለን፡፡ አንሰማም አናሰማም፡፡ በቃ ኦሮሞው ህሊና ከሌለው አማራ ወንድሙን ይግደለው ህሊና ከለለውና የኢትዮጵያዊነት ጠላትነቱ ለይቶለት እንዲወጣና የኢትዮጵያዊያን አስጊ ጥቁር ነጥብ ዝርዝር ውስጥ መግባት ከፈለገ፡፡ አንድ ባለማወቅም ሆነ በማወቅ ሆን ብሎ የዘር ክፍፍል እንዲመጣ በሚሻ የወያኔ ስርዓት ሴራ የገባ እና ስውር አገልጋይ የሚሆን ኢትዮጵያዊ ሌላውን በዘር በቋንቋ በቀለም በሃይማኖት በማንኛውም ልዩነት ክፍተት ምንም ዘላቂ ለውጥ ላያመጣ ነገር ቢደክም አንሶት የመግደል የማሳደድ የመዝረፍ የመቅጣት የመግረፍ ማንኛውም የሚታይም ሆነ የማይታይ አካላዊውም ሆነ ስነልቦናዊ ጉዳት ቢያደርስ መጀመሪያ እንደ አንድነት ናፋቂ ኢትዮጵያዊ እና ኢትዮጵያዊነትን አንደሚናፍቅ ምርጥ ዜጋ እና ዲሞክራቲክ በእኩልነት የሚያምን ዜጋ አንዱ ኢትዮጵያዊ በአንዱ ኢትዮጵያዊ እንደገደለ ብቻ እንወስደዋለን፡፡ ከዛም ይህን ስርዓት አልባ ኢትዮጵያዊ ስርዓት እንዲይዝና ከገባ በምክር እገባው ይሆናል አለበለዚያ ግን ይህና ሌሎች ዲሞክራቲክ አማራጮች ካልተሳኩ እርሱ ከወጣበት ብሄር ጋር ምንም ፀብ የሌለን ሲሆን ራሱ አደጋ አድራሹ አካል ላይ ግለሰብ ላይ ግን አስፈላጊውን እርምጃ እንወስዳለን፡፡

ህይወቱን እስከማጥፋት ብሎ መናገር ምናልባት አስፈላጊ ግን ላይሆን ይችላል ሆኖም እርሱ ኦርጅኔት ካደረገበት ብሄር ጋር የግለሰቡ ርካሽ ተግባር ግን ሚያገናኘው ነገር ባለመኖሩ አባሌ ሞተብኝ የሚለው የሟቹ ግለሰብ ወይም ቤተሰብ ቋንቋ ተናጋሪ ህብረተሰብ ክፍልም ለምን #የኛን# አባል የኛን ቋንቋ ተናጋሪ በደለብን ለምን አዋረደብን በማለት ብቻ ሌሎች የገዳዩ ቋንቋ ተናጋሪ፤ እምነት ተከታይ እንዲሁም ዘር ቀለም አባላት ላይ ጉዳት ለማድረስ ቢሞክሩ በህግ ፊት መፋረድና ተገቢ ዋጋቸውን መስጠት ነው ይህ ሲባል ምን ማለት ነው የትኛውም ዘርሯኗ እምነት ወዘተ ቀለም ልዩነት ላይ መሰረት አድርጎ ሌሎች መሰሎቻቸው ያለሆኑ አካላት ላይ መድልኦ በደል ሞት ግርፋት ዘረፋ ግድያ ወዘተ የሚፈፅሙ አካላት ይህ ተግባራቸው እጅግ የከረፋና የወረደ በመሆኑ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን የሚያዋርድ የሚያጎድፍ ተግባር በመሆኑበቶሎ መታረም ካልቻሉ አደገኛነታቸው እና አሉታዊ ተፅዕኗቸው መቶ በመቶ አስከፊና አሳፋሪ በመሆኑ ያለምንም ምክንያትና ማመንታት የምንዋጋውና የምንታገለው አካሄድ ነው፡፡ በዚህ አካሄድና ርዕዮት ላይ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የሚደረጉ አስተሳሰቦች ከወዲሁ አደገኛነታቸው ታስቦበት እንዲቆሙ በዚህ አጋጣሚ በኢትዮጵያ ስም ጥሪየን አቀርባለው፡፡

ህሊና የሌለው አማራ ኦሮሞውን ይግደለው እንበል በቃ ቀድሞ ነገር ለመግደል ማሰቡ ምንም ህሊና እንደሌለው እጅግ የሞተ አስተሳሰብ ደረጃ ላይ እንዳለ አውቆ ከማሳወቅ ውጭ እና ለቀጣይ ሌላ አደጋ እንዳያደርስ ሌላ ሞት እንዳይከተል ከመታገል ውጭ ማንም ለብቀላ ቢነሳ የበለጠ ስዕተት የሚሆነው ያኔ ነው፡፡ ይህ ማለት ባጭሩ አንድ ኦሮሞ ኢትዮጵያዊ ሌላውን ኦሮሞ ኢትዮጵያዊ እንደገደለው አድርጎ መውሰድ ብቻ በቂ ነው አማራው ትግሬውን ትግሬው ኦሮሞውን ጉሙዙ ጋምቤላውን ሶማሌው አፋሩንና እንዲሁም አንዱ አንዱን ገደለ ማለት ኢትዮጵያዊውን ሌላ ኢትዮጵያዊ ገደለው ማለት ነው እንጅ እንደ ኢትዮጵያዊነት እና እንደኢትዮጵያ መወሰድ ያለበት አንዱ ብሄር ሌላኛውን ብሄር ምንም አያመጡብኝም ብሎ ገደለው ወደሚል አዝማሚያ መወሰድ ለበትም፡፡ ይሕ ይህን ፅሁፍ የፃፈው የአብቢን አስተሳሰብ ቢሆንም ቅሉ ፍፁም ኢትዮጵያዊነትን የተላበሰ አንድነትና መሰረት አድርጎ ዘረኛነትን ሚነቅፍ ፅሁፍ በመሆኑ ፀሃፊው እነደዚህ ትንሽ መልዕክት ያላት ፅሁፍ መፃፍ የሚያስደስተው አይኖርም ታዳሚዎቹንም እጅግ አድርጎ ያመሰግናል አብቢን፡፡

አሁን ይህችን ሃገር ለዘራፊዎች ከወንበዴዎች ከገራፊዎች ከህዝብ ጠላቶች አድኖ የነፃነት ታጋዮችን በማስተባበር አንድነቷ ተጠብቆ ክብርና ሉአላዊነቷ ተከብሮ እንድትኖር ለማድረግና ጠላቶቿ አፍረውና አንገታቸውን ደፍተው እንዲሄዱ ለማድረግ ህዝባችን የተሻለ የኑሮ ደረጃ ላይ እንዲደርስ መስመሮችን ለማስተካከልና አስተካክለንም ተፋቅረን አንድ ሆነን የምንኖርበትን አየር ለመተንፈስና አለም ከደረሰበት ደርሰን ማየት የምንችልበትን አቅጣጫ መንደፍ ላይ ነው ትኩረቴ ማድረግ ያለብን፡፡

ይህች አገር አሁን አደጋ ላይ ነው ያለችው፡፡ መቼም ቢሆን ብዙዎች እደሚሉት የዘር ፍጅት ይመጣል ብለው እንደሚያስቡት እንዲህ በቀላሉና እንደምናስበው የሚባለው ዘር ፍጅት እንደ ሩዋንዳ እንተላለቃለን ገለመሌ የሚባለውን እንዳልቀበል የሚያደርጉኝ በርካታ እወቅነተኛና ወደር ሌላቸው እውነታዎች በመኖራቸው ለሌላ ጊዜ እንደምገልፅ ብቻ በይደር እተወውና ወደዛሬው ወደጀመርኩት አጄንዳየ ስገባ ይህ ፋሽሽታዊ ልቅ ስርዓት እና መንግስት ሳናደርገው መንገስት ነኝ ብሎ የሚያስብ የማፊያ ቡድን ህዝቦቿን ከፋፍሎ እና ለመግዛት ባሪያ ለማድረግ እንዲሁም የበለጠ የከፋፍለህ ግዛ መርህን ለመተግበር በሚያመቸው መልክ ከፈለገም የሚገነጠለው ተገንጥሎ የሚገዳደለው ተገዳድሎ ሚሊየን አመት እንደሚኖሩበት ሁሉ አላማቸውን ህዝቦቿን አጨራርሰው ህዝቦቿን እና አንድነቷን በታትነው የስልጣን አድሜያቸውን ለማራዘም ግብግብ ገጥመዋል፡፡ ማን ጋር ነው የገጠሙት ካልን ግን ከህዝቡ ጋር ከኢትዮጵያዊው ጋር ከኢትዮጵያዊነት ትልቅ መሰረት እንዳለው ካላወቁት የብረት ግንድ እና ዘር ጋር ነው፡፡ ሆኖም አውቆም ይሁን ሳያውቅ ኢትዮጵያዊ አደለሁም… የሚል አካልማ የእነርሱ ትልቅ መሰረት ነው የግብግባቸው ደጋፊና አቀብቃቢ ነው፡፡ ነገር ግን ይህንን ሁሉ ስርዓት አልበኛውን ስርዓት እንዲሁም አለቅላቂ የጎንዮሽ አካላትን በኢትዮጵያዊነትና በኢትዮጵያ ስም በአንድነት አፍር ድሜ ማብላት በጣም ቀላል ስራ ነው፡፡ ስዎች ምነው አባቶቻችን ማሰብ ማስታወስ አቃተንስ…ተውልዱ በሱስ እንዲተመድእድሉን ፈጥረውለት በርካታው መሽጎ ሲቅም ሲጠጣ ሲያጨስ ቢውል ቢያድርምኢትዮጵያዊነትን በተላበሰና ኢትዮጵያዊ አንድነትን መፈቃቀርን መሰረቱ ላደረገ ከዘረኝነት ለፀዳ ገን ያለው ከበቂ በላይ ነውና የሚያሳስብ ጉዳይ አይሆንም፡፡ ድል የኢትየጵያ የህዝቦቿ እንዲሁም ኢትዮጵያዊነት ይሆናል፡፡ዱሮም አንድነታችን እንጅ ያኖረን አንድ ያደረጉን እንጅ ያኖሩን ያለአንድነታችንማ አስቸጋሪ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ትልቁ ሚሳየል የጠላት ጦርና ጠላት ማጥፊያ መሳሪያ ኒውክሌራችን አንድነታችን ብቻ ነው ሌላው ምናልባትም ኪሳራ ሲደመር ድል ነው፡፡ አንድነታችን ካለ ግን ኪሳራው ድምሩ ዜሮ ነው፡፡ ድል በድል እንሆናለን፡፡ በመሰረቱ ፌደራል ፖሊስ መከላከያ ፖሊስ አጋዚ ልዩ ሃይል ገለመሌ ቢባሉ ከህዝብ ውጭ አደሉም አንድ የሚያደርገን ሃረግ አለን መበጠስ የማይችሉት ላመን እያደሩ እንደሆነ እየገባቸው ቴክኖሎጅ በፈጠረላቸው አጋጣሚ እየታገዙ የመብት ጥቄ ለቆሙለት እስካሁን ግን ለበደሉት ለስርዓቱ ብለው በስዕተት ለህዝብ ያገለገሉ መስሏቸው ግፍ ሲያደርሱ ቢቆዩም አሁን አሁነ ግን ተቃውሟቸውን አንድም በመክዳት አለያም በአደባባይ በመመስከርና በመቃወም የመረሸን ህጋቸውን ሳይፈሩ እንኳን ጥያቄን እያቀረቡ እየሞቱ ከህዝብ ጎን እየተሰለፉ ነው፡፡

በእርግጥ አሁን አሁን የመብት ጥያቄ ባሉበት አካባቢም ይሁን እነርሱ አካባባ ስላለው መገፋት በመቃወም ሚያቀርቡ መከላከያ ሰራዊት አባላት ይረሸናሉ ይረሸኑ የሚል ህግም በሚስጥር መተላለፉን ሰምተናል ነገር ግን ጓዶቻቸው ወይም አባሎቻቻው የት እንደገቡሲጠይቁ ወይ የጠየቁትም እንደ አስፈላጊነታቸው ይታሰራሉ ወይም ይረሸናሉ አለያም ሲቪሉ ጋር እንዲቀላቀሉና ከመከላከያው ምንም ድርሽ እንዳይሉ ይደረጋሉ የሚሰጣቸው መልስም ያ ጥያቄ ያነሳው አካል ወደ ሌላ የኢትዮጵያ ክፍል ለግዳጅ እነደሄደ ይነገራቸዋል፡፡ ስለዚህ እነዚህ አካላት የፀጥታው አካላት እንደህዝቡ ሁሉ እየቆሰሉ ውስጣቸው እያረረ ነው ያሉት፡፡ ነገር ግን ይህ ስርዓቱ ሰላማዊ ሰልፍም ሆነ የስብሰባ ጊዜ ፀጥታ ለማስከበር ብሎ የሚልካቸውና እንዲገድሉ እነድደበድቡ የሚልካቸው የወጣላቸው አረመኔ የወያኔ ኢህአዴግ በተለይ የህወሐት ፈፃሚዎች ናቸው…ስለዚህ ሲገድሉም ሲገርፉም ቶርች ሲያደርጉም ይህን ስላደረዱ ስለሚሸለሙት ሽልማት እንጅ ስለሚያደርሱት ስቃይና ግፍ በደል አደለም፡፡ እነዚህን በኢትዮጵያዊነታችን ድል ዋዜማ ለፍርድ እናቀርባቸዋለን፡፡ ይህ ግን ብቀላ አደለም ህ ፍትሃዊነት ነው አንጅ፡፡

ይህ ስርዓት ዓላማው ኢትዮጵያን እንድ አድርጎ ማቆየት ሳይሆን ማኖር ሳይሆን አንድ የሆነች ኢትዮጵያን ድራሷን አጥፍቶ አንድነትና እኩልነትን ፍትህን ከሃገሪቱ አጥፍቶ የሚፈልገውን በደከመ ማህበረሰብ ውስጥ አቅም ባጣ ህዝብና እውነት ውስጥ እየተሸለከለከ እንደ ምስጥ መብላትና ስጋና ደሙን መጥጦ ራሳቸውን በሃብት ማድለብና ህዝቦችን ለበቀል ማዘጋጀት እንዲሁም እንደ አይጧ የሚያሳሱ የሚመስሉና የሚያሳስቱ እውነታ መሳይ ታሪካዊ አወዛጋቢ ክስተቶችን በመጠቀም በሃገሪቱ መበታተን የእነርሱን ባደረሱት ግፍና በደል የማይጠየቁበትን ሁናቴ ማመቻቸት ነው ምክንያቱም ይህች ሃገር ተበታተነች ማለት እነርሱን ተጠያቂ የሚያደርግ ስርዓት አንድ ሆነ የተባበረ ክንድ አይኖርም ስለዚህ የሰበሰቡትን ሁሉ እንደ እርኩም ለመብላት ያመቻቻዋል እንዲሁም ሃገሪቱ ድራሷ የሚጠፋበትን በመቀመር አንዱ ኢትዮጵያዊ በሌላኛው ኢትዮጵያዊ ላይ እንዲነሳና ደካማና ለኢትዮጵያ የማይበጅ ህሊናውን በደካማ ጎኑ በመግባት ማስገደል ማጋጨት ማቆራቆስ ነው፡፡

ይህንን የማይባንን ከሁሉም ኢትዮጵያዊ ከሁሉም አካባቢ የኢትዮጵያ ምድር ላይ ያለማዳላት አለ፡፡ አማራ ሆኖ ኦሮሞ አማራውን ገደለ ቆራርጦ አንጠልጥሎ ዞረ ስለተባለ ብቻ ኦሮሞን መጉዳት የማይፈልግ አይኖርም ማለት አይቻልም ምንም እንኳን የአማራ ህዝብ ብዙ ጊዜ አብሮ መኖርን አንድነትን የሚናፍቅ መሆኑን የሚያሳዩ በርካታ ዋቢዎች ቢኖሩም ቅሉ፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያዊነትን አንድነትን ኢትዮጵያን ሃገራችንንን የምንሸዳ ከሆነ ይህ አይበጅም ነው፡፡ ቆራርጦ የገደለው ኢትዮጵዊ ወነድሙ ነው ኦሮምኛ ስለተናገረ አደለም ነው የምለው፡፡ አማራ ሶማሌ ኦሮሞ ትግሬ አፋር ደቡብ ጉሙዝ ገታምቤላ ወዘተ ሁሉ ኢትዮጵያዊ ናቸው፡፡ ያልታደልን ሆኖ እና በወያኔ ሴራ እንጅ እኮ ኢትዮጵያ ማ ሰፊ ነበረች እኮ…
ለነገሩ እነዚህና ሌሎች ታሪካዊ የይገባኛል ጥያቅዎች ሁሉ የሚነሱበትና ፍትህ የሚያገኙበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም ሁለቱ ዝሆኖች እስኪወገዱ ብቻ እንጅ…

ኦሮሞ ሆኖ ደግሞ አማራውን መበቀል የሚፈልግ ከሰፊው የኦሮሞኛ ቋንቋ ተናጋሪ ኅዝብ መካከል አንድነትን ከሚፈልገው ህዝብ መካከል እንደ ዶሮ ቅልጥም ጣል ጣል በለው ሴራቸውን የሚያስኬዱ ሞልተዋል፡፡ ለዚህም አደል በተለያዩ አካባቢ የሚኖሩ አማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ ኢትዮጵያዊያንን በሃገራቸው ኢትዮጵያ እየኖሩ እያለ እንደማንኛውም ህዝብ እኳን ሳይታዩ የሚገደሉት የሚዘረፉት ለዚህም አደል እንዴ ምንም ክብርና ሞገስ ሳይሰጣቸው እንደ ኢትዮጵያዊ ሳይታዩ አንገታቸው በነሙሃመድ ጃዋርና ደጋፊዎቹ አክራሪዎች የሚገደሉት፡፡ ሙሃመድ ጃዋር እዛ ጫቱን እንደመቃም መጨራረስ የሚጠቅም መስሎት የፍየል ድምፁን ሰምተው አንደሚያንቋርሩት ደጋፊዎቹ መስሎት እንዳለውም በቤንጫ የሌላውን ቋንቋ ተናጋሪ የሌላውን እምነት ተከታይ የሚቀሉት፡፡

ግን ይህን የሚሰራው ሁሉም የኦሮሞ ህዝብ ሳይሆን አንዳንድ አላዋቂ ሳያውቄ ያወቁ የሚመስላቸው የጃዋርና ደጋፊዎቹና የደጋፊ ደጋፊዎቹ ደጋፊዎችና አክራሪ ኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋራች ናቸው፡፡ በርካታ የኢትዮጵያዊነት ስሜት ያላቸው ኦሮመኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ኢትዮጵያዊያን አሉ ኢትዮጵያ ያለአማራው ያለትግሬው ያለሶማሌው ያለ አፋሩ ያለ ደቡቡ ያለ አዲስ አበባው ያለ ጉሙዙና ጋምቤላው መኖር አንደማትችል የሚለፍፉና የሚሰብኩ ምርጥ የኢትዮጵያዊ ስሜትና ክብረ ያላቸው ኦሮሞኛ ቋንቋ ተባጋሪዎችና የአካባቢው ተወላጆች እኮ እከአፍንጫው ሞልተዋል፡፡ ግን ከስንዴ መሃል እንክርዳድ አይጠፋምና ከዚህ ምርጥ ኦሮሞኛ ተናጋሪ ምርጥ ህዝብ መካከል ጣል ጣል ያሉ ከአንድም ሁለት ሶስት ዓላማ ያነገቡና ባለማወቅ ይህንን ስእተት የሚሰሩ ኢትዮጵያዊያን አሉ፡፡ ኢትዮጵያዊነትን አስገድዶ መጫን አይቻልም፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያ ምድር ላይ እስካሉ ድረስ ለቅቀው ከኢትዮጵያ ውጭ እስካልሄዱ ድረስ ኢትዮጵያዊ የሆኑ እና ብለንም የምንጠራቸው ራሳቸውን እንደ ኢትዮጵዊ ሳይሆን እንደ ኦሮሚያዊ የሚቆጥሩ የህሊና ጭንጋፎች አሉ፡፡

ይህን ችግር እንዲህ አይነት ችግርና ክፍተት እንደሚያመጣ እያወቀ ባያውቅ እንኳን ሊያውቅ እየተገባው ሆን ብሎ ይህ የጫካ ስርዓቱን እና ፅንስ ዘመኑን ያልጨረሰ ምንግስት ሳናደርገው መንግስታችሁ ነኝ የሚለን ስርዓት ሳይኖረው ስርዓት ነኝ የሚለንን የማፊያ ቡድን ሴራና የረዥም ጊዜ ልምምድ እቅድ ነው፡፡ ይህም ውጤቱ ነው፡፡

ስለዚህ እኛ ትግላችን መሆን ያለበት ትንቅንቃችን መሆን ያለበት ይህንን ክፍተት የፈጠረውና ይህን እልቂትና እርስ በእርስ እንድንጨራረስ ከሚመራን ማፊያ ቡድን ጋር ብቻ ነው፡፡ አማራው በማንም ቢገደል ከገዳዩ አያገባንም እርሱን እንደፍትህ እንደ እኩልነት እንደ ፀረ አንድነትና ከሃዲ ሃይል እንፋረደዋለን እንጅ ለምን ብለን ስለገደለ ብቻ ለብቀላ ኦሮምኛ ተናጋሪ ወገኖቻችን ለማጥፋትና እንደጠላት ቆጥረን የምንገጥምበት ምንም እውነት የለም ያሰበ ካለም ተሳሷል፡፡ ይህንን በደል ያደረሰ አካላ ግን በቻልነው ሁሉ ለፍርድ ማቅረብ አለብን፡፡ ይህንን የኢትዮጵያዊነት አስተሳሰብ ፀር የሆነ ተግባርንም ሆነ አላማ ይዞ የሚንቀሳቀስ አካል በቃህ ልንለው ይገባል ስዎቹን በዳዮችን ግን ለፍርድ ማቅረብና አስፈላጊ ከሆነም አስፈላጊውን ፀረ-ፀረ-ኢትዮጵያዊነት እርምጃ መውሰድ ስለኢትዮፕያና ኢትዮጵያዊነት የጠፈፀመ እንደሆነ አድርጌ እወስደዋለው፡፡ ለኔ ማንኛውንም አይነት እርምጃ ኢትዮጵያን ለማዳን ቢወሰድ ትክክል ነው፡፡ ምክንያቱም አላማየ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵዊነትን ማዳን ነው፡፡ ማንም አይሄድም የምንበቀለው ቢኖር ግን ፀረ-ኢትዮጵያዊነትን ፀረ-ኢትዮጵያና ፀረ-ህዝቦቿን ፀረ-አንድነቷን ፀረ-ሉአላዊነቷንና ይህን ማፊያ ቡድን ብቻ ነው ብሄርን ቋንቋን እምነትን ሃይማኖትን ቀለምን አካባቢን ተወላጅነትን በአጠቃላይ በኢትዮጵያዊነት ብቻ ያላመነን አስተሳሰብ መሰረት ያደረገ አስተሳሰብን ሆነ ግለሰብን ሆነ ፖለቲካዊ የተደራጄ አንቅስቃሴን ማውገዝ ለነገ የሚባል ጉዳይ አደለም፡፡
ቸር እንሰንብት
ኢትዮጵያ ኢትዮጵዊነትና ህዝቦቿ በምንም ላይ ያለተመሰረተ ልዩነት ሳይገባባቸው ለዘላላም ትኑር ይኑሩም
በአብቢን

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen