May 2/2014
አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) እሁድ ሚያዝያ 26 ቀን 2006 ዓ.ም ለሚያደርገው ሰላማዊ ሰልፍ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ድርጅት አላስተናግድም ማለቱን የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው ገለጹ፡፡ የህ/ግ ኃላፊው እንደገለጹት ከሆነ ማንኛውንም ህጋዊ አካል ወይንም ዜጋ በእኩልነት ማስተናገድ የሚገባው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ምንም አይነት ህጋዊ ምክንያት ሳያቀርብ አናስተናግድም ማለቱ አንድ የሕዝብ አገልጋይ ነኝ ከሚል ተቋም የማይጠበቅ እና ተቋሙ በእርግጥም የህዝብ አገልጋይ አለመሆኑን በድጋሚ በተግባር ያረጋገጠበት ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡ እንደ ህዝብ ግንኙነቱ ገለፃ ፓርቲው ጉዳዩን በቸልታ እንደማያየው እና ወደ ፍርድ ቤት እንደሚወስደውም ታውቋል፡፡ የኢትዮጵያ ቴሌቪዢን የማስታወቂያ ክፍል ኃላፊ አቶ ሰይፉ አለምሰገድና ወ/ት ሸዋዬ የማስታወቂያ ክፍል ኤክስፐርት በእጅ ስልካቸው ደውለን ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው የነሱን ሀሳብ ልናካትት አልቻልንም፡፡

Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen