May 3/2014
በጎንደር መተማ አቅራቢያ ልዩ ስሙ ሸዲ እና ገንዳ ውሃ በሚባሉ ቦታዎች የፌደራል ፖሊስ በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ በከፈተው ተኩስ አምስት ሲሞቱ ስድስት ክፉኛ ቆስለው ወደ ጎንደር ሆስፒታል መወሰዳቸውን የደረሰን ዜና ተቁሟል::
የግጭቱ መንስኤ አንድ የፌደራል ፖሊስ አባል አንድ የአካባቢውን ነዋሪ በህገ-ወጥ የኮንትሮባንድ ንግድ ሳቢያ በተፈጠረ ግርግር ይገድለዋል:: የአካባቢው ነዋሪዎችም በሰላማዊ ሰልፍ ገዳዩ የፖሊስ አባል ለህግ እንዲቀርብላቸው ለመጠየቅ ሲወጡ: ሌሎች ማህበረሰባዊና ፖለቲካዊ ጥያቄዎችንም አብረው ይዘው ወጡ:: ፌደራል ፖሊስም በወጣው ህዝብ ላይ ቶክስ በመክፈት አራት ተጨማሪ ሰዎችን ሲገድል ስድስት ክፉኛ ቆስለዋል::
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen