May 24/2014
ታሪኩ አፈ ታሪክ ነው፤ በደንብ ሊጠና ይገባዋል ተብሏል
በአፄ ምኒሊክ ዘመን ተፈጽሟል የሚባለውን ኢ-ሠብአዊ ድርጊት ለማሳየት በኦሮሚያ አርሲ ዞን አኖሌ በተባለ ስፍራ የተገነባው ሃውልት፤ የታሪክ ምሁራንን እና ፖለቲከኞችን እያወዛገበ ሲሆን፤ የታሪኩ እውነተኛነትና የሃውልቱ አስፈላጊነት አከራካሪ ሆኗል፡፡
ተቃራኒ አስተያየቶችን ለአዲስ አድማስ የሰጡ ፖለቲከኞች፤ ታሪኩ እውነተኛ ነው ወይስ አይደለም በሚለው ጥያቄ አልተስማሙም፡፡ በአኖሌ ተፈጽሟል የተባለው ጡት እና እጅ የመቁረጥ ድርጊት በታሪክ ሰነዶች ያልተመዘገበና ያልተረጋገጠ አፈታሪክ ነው የሚሉ ፖለቲከኞች፤ ሃውልቱ ጥላቻና ቂም በቀልን የሚሰብክ ስለሆነ ተገቢ አይደለም ብለዋል፡፡ በአኖሌ ኢሰብአዊ ድርጊት መፈፀሙ እውነተኛ ታሪክ መሆኑን የሚያምኑ ፖለቲከኞች በበኩላቸው፤ ሃውልቱ መገንባቱ ተገቢ የሚሆነው ድርጊቱ እንዳይደገም መማሪያ ስለሚሆን ነው ብለዋል፡፡
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የታሪክ መምህር አቶ አበባው አያሌው፤ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ሴት ልጅ በጦርነት ጊዜ የተለየ ጥበቃ እንደሚደረግላት ጠቅሰው፤ በአኖሌ ጡት ተቆርጧል ለሚለው ማረጋገጫ የሚሆን የታሪክ ሰነድ የለም ብለዋል፡፡ አፈታሪኩ ከብሔርተኝነት ጋር ተያይዞ የተፈጠረ ነው ያሉት አቶ አበባው፤ አፈታሪክን መነሻ አድርጐ ሃውልት መገንባት አይገባም፤ ከዚህ በተጨማሪ ሃውልቱ ጥላቻና ቂም በቀልን ከማንፀባረቅ የዘለለ ፋ....

Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen