Netsanet: ኢትዮጵያዊነት ክፍል አንድ (ሄኖክ የሺጥላ)

Sonntag, 11. Mai 2014

ኢትዮጵያዊነት ክፍል አንድ (ሄኖክ የሺጥላ)

May 11, 2014

ኢትዮጵያዊነት በተቃርኖ የተሞላ የግሳንግስ ስብስብ አይደለም። ኢትዮጵያዊነት የወጪት ሰባሪዎች ትግል፣ ለኔ በገሌ ነው ባዮች ምክር አይደለም። ኢትዮጵያዊነት በበግ ጸጉር ቡክርናውን እንደቀውማው ያዕቆብም ( ” አታላይ ማለት ነው”) አይነትም አይደለም። በጎሳ አሽክላ ተተብትበን፣ በቂም ቆመን፣ ጭረት አመርቅዘን ቁስል አርገን ፣ የዛሬ ውድቀታችንን ፣ የዘምን ምክነት አስመስለን፣ ላለመቻላችን መወጣጫ፣ ላለመቆማችን የ ምክንያት መቆናጠጫ ብንፈልግ ፣ ካለፈ ጥፋትም ሆነ ሕዝብ ካለፈለት እውነት ጀርባ መዶለታችንን እስካልተውን ፣ የድርሻችንን ለመወጣት ታጥቀን እስካልተነሳን ድረስ ፣ ትግላችን እንደ እስከ ዛሬው ” ለ አፈ ግም አፍንጫ ድፍን ያዝለታል” ሆኖ ስለመቀጠሉ አዋቂ መሆን አይጠይቅም።henok yeshitla

የፕለቲካ ድርጅቶች መግለጫና ትርጉም
የ-ወያኔው ስርዓት እንደ ወየነ 40 ዓመት ሞላው። እኛም የዚህ ስርዓት አድማቂዎች መሆን ከጀመርን እንዲሁ። የተላዩ ያልተቀናጁ፣ በማይረባ የትግል ቅርጽ የተጠረቡ ድርጅቶችም ይሄንን ስርዓት እሱን በሚመቸው መልኩ እየታገሉት (በጩኸት እያጫፈሩት) ተጉዘዋል፣ ብዙዎቹ መሰረት አልባ፣ የማይጨበጥ፣ የማይያዝ ትግል አድርገዋል። ባንጻሩ ደሞ ጥቂቶች ደማቸውን አፍስሰዋል፣ ጥቂቶች ራሳቸውን ባደባባይ ገብረዋል፣ ጥቂቶች ተሰውተዋል። እና በዚህ በማይረባ የትግል መስመር ውስጥ ባሉትና በቆራት አቁዋም ራሳቸውን በሰዉት መሃከል ግን በሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ ይህ ነው የማይባል በደል ( እስር ፣እንግልት፣ ግድያ፣ አፈና ፣ስደት እና ወዘተ ) ደርሶበታል እየደረሰበትም ነው፣ ገና ወደፊትም ይደርስበታል። ታጋዮቻችን ለአመታት ከማሳሰቢያ ያለፈ ነገር ሲያደርጉ አይስተዋሉም ” የ ወያኔ መንግስ በንጹሃን ኢትዮጵያውያኖች ላይ እያደረሰ ያለውን ነገር ባስቸኩዋይ እንዲያቆም አከሌ የተባለው ድርጅት አበክሮ አሳሰበ “። እኔ እምለው እንዲህ አይነት ማስጠንቀቂያ ስትጽፉ ነው የኖራችሁት፣ በማስጠንቀቂያ ቢሆን ኖሮ ወያኔ አዲስ አበባም አይገባ ነበር። እስኪ ማስተንቀቂያችሁ አልሰማ ሲል አጸፋ መመለስ የምትችሉ እስክትሆኑ ድረስ እባካችሁ ማስጠንቀቁን ተዉት። ይሄ ጭፍን እና መሰረት አልባ ጀብደንነት ነው አርባ ዓመት አጫፋሪ ያደረገን። እስኪ አሁን ማን ይሙት ዛሬም ( በ 2006) ማስጠንቀቂያ የምንጽፍ ሰዎች መሆን ነበርን ? “ብልህነት እንጂ ብልጠት ባከተመለት ዘመን ተፈጥረን ” ማንን ለማሞኘት ነው። ወይስ አንድን ድርጅት ድርጅት የሚያስብለው እንዲህ ነገሮች ሲጦዙ እመር እያለ በማስጠንቀቂያ ቀለም መጨረሱ ነው። አይግባኝም። እዚህ በምኖርበት ሀገር አማሪካ አንድ ሰው የቤት ክራዩን ወይም የስልክ አገልግሎት ክፍያውን በአግባቡ መፈጸም ካልቻለ ማስጠንቀቂያ ወረቀት ይደርሰዋል፣ ሰውየው/ሰትይቱ በተባለው ግዜ ክፍያውን ካልፈጸመ/መች አገልግሎት ሰጪው ድርጅት የአገልግሎት ተጠቃሚነቱዋን ይሰርዛል። ማስጠንቀቂያ ማለት እንዲህ ነው። እኛ ግን ወያኔ አርባ ዓመት ሲረብሽ፣ አርባ ዓመት ማስጠንቀቂያ የምንጽፍ ተራ ጀብደኞች ነን። በምክንያት የታጠርን፣ የማናታግል፣ የማንታገል፣ ስለ አንድነት የምንሰብክ ግለኞች ፣ በጠባብ ተሰፍረን ስለ ሆደ ሰፊነት የምናወራ። አረ እንደውም ይሄ ሆዴ ሰፊነት ስለሚባለው ነገር እናውራ። በአዲስ መስመር ይጀመር።
ሆዴ ሰፊነት ማለት ምን ማለት ነው? ጭቆናን መቀበል? በኢትዮጵያዊነት ጉዳዮች ላይ የጋራ ዝንባሌም ብቻ ሳይሆን ፍጹም ተቃራኒ በሆነ መልኩ ከሚሄዱት ጋ ፣ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር የለችም ከሚሉት ጋም’ እስከ መተባበር ድረስ ነው? ሆዴ ሰፊነት እና ሆደ ቡቡነት እኮ የተለያዩ ነገሮች ናቸው። እንደውም ታጋዮቻችንን የምጠይቀው ነገር አለኝ። በእውነት መታገል ትፈልጋላችሁ ? በእውነት ለውጥ ማምጣት ትፈልጋላችሁ ? በእውነት እየሆነ ያለው ነገር ይገባችሁዋል ? ቢሆን ኖሮ ዘንድሮም ወረቀት በተንን ብላችሁ ባላወራችሁ፣ ቢሆን ኖሮ እንደ ትልቅ ነገር በየ ድህረ ገጾቻችሁ የማስጠንቀቂያ ሐተታ ባላወጣችሁ። የምታደርጉት ነገር ልክ አይደልም እያልኩ አይደለም፣ ግን ከዚያ አንድ ጋት ፈቀቅ ማለት አልቻላችሁም፣ ግብራችሁ ከአንደበታችሁ ( ከምታወሩልን ነገር ጋ) ይጣረሳል። ከስብሰባና ዓመት እየጠበቁ የምስረታ በአላችሁን ከማክበር ያለፈ አንድም ነገር ስታረጉ አላየናቹም። አለን ትላላችሁ እንጂ የላችሁም። መነሳት አልቻላችሁም፣ ወጣቶች እንዲነሱ መንገድ ማሳየት አትፈልጉም፣ ከስር ሆኖ ጉልበት የሚስም እንጂ የናንተን ጉልበት ይዞ የሚነሳ ልጅ አልወላዳቹም፣ ስመቻችሁ ትውልዱን ጫታም፣ ሴሰኛ፣ ራስ ወዳድ ፣ ምናምን ብላችሁ ጥረግሙታላችሁ። ትውልዱ በማን ይውጣ፣ ማንን ይከተል፣ ምን አስተማራችሁት። ከናንተ የተማራው እምብ ማለትን ሳይሆን፣ ከእሳት መሸሽን ነው። መስእዋትነትን የምታውቁት ከናንተ ጋ ቆመው በተሰዉት ሰዎች እንጂ በራሳችሁ አይደልም። በሰው ደም ለመንገስ ፣ በሰው ደም ለመኮፈስ፣ በሰው ደም አናት ለመሆን ከመዳዳት ውጪ ፣ ጉልበታቹም ውኔያችሁም፣ እምቢታቹም በራሳችሁ ገድል ላይ የተመሰረተ አይደለም።
መጋደልንም ሆነ መሞትን ማወቅ አትፈልጉም፣ የኢትዮጵያ ጉዳይ ያሳስባችሁ ይሆናል ግን እንቅልፍ አይነሳችሁም፣ ነገሮች መስመር ሲለቁና የህዝቡ እሪታ ሰማይ ሲደርስ፣ ባፋጣኝ ድርጅት ትመሰርታላችሁ፣ የሚገርመው ከሚያልቀው ሰው ይልቅ አብልጣችሁ የምትጨነቁት ስለድርጅታችሁ ስም እና አባላት ነው። እያንዳንዱ የኢትዮጵያ መከራ ለናንተ የገንዘብ መሰብሰቢያን ዕድል ይፈጥራል፣ ይህንንም ያለ ሀፍረት ባደባባይ ታደርጉታላችሁ። ባጭሩ ትግል ምን እንደሆነ አታውቁም። እናንተን የሚያታግላችሁ በየጊዜው የሚፈነዳው የህዝብ ብሶት እንጂ አላማችሁ አይደለም። አጀንዳም፣ የትግል መዋቅርም፣ ሕልምም የላችሁም። በተገኘው አጋጣሚ ትግሉ እንዲፋፋም ትፈልጋላችሁ፣ ስለዚህ አልተሳካላችሁም፣ ምክንያቱም እያንዳንዱ አጋጣሚ የራሱ የሆኑ ውድቀቶች አሉትና።
ሙህርነታችሁ ፋና ወጊ ከመሆን ይልቅ መመጻደቂያ ስታደርጉት ነው ያየነው። በሁለት ሃሳቦች መሃከል ያለውን ልዩነት ለመፍታት የምታደርጉት ውይይት የምሁርነታችን ልክ ሳይሆን የጥላቻችሁን ቁመት ነው የሚያሳየን። ባልነበርንበት፣ በማናውቀው፣ ፍጹም ልክ የሚባል መረጃ በሌለበት ሆኔታ እንኩዋ ፍጹም ልክ የሆነ ተበዳይ እንሆናለን።
እስኪ ትንሽ ምሳሌዎች ላንሳ
ዶር መራራ ጉድና ከኢሳት ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ጋ ባደረገው ቃለ ምልልስ። ” አያቴም በሚኒልክ መሬታቸው ተወርሶዋል ይህም የሆነው አድዋ አልዘምትም በማለታቸው ነው ” ይላል። እንዴ ጋሼ መራራ ለካ የእርሶም አያት አድዋ አልዘምትም ብለው ነበር። እኔ ይሄ የሰሜን ባንዳዎች ታሪክ ብቻ ይመስለኝ ነበር። እንግዲህ እግዚአብሔር ይግለጥላችሁ ምንሊክ ምክንያታቸው አደዋ ዝመት ነው። አይ አድዋ አልዘምትም ! እንግዲያውስ አንተ ኢትዮጵያዊ አይደለክም ስለዚህ የኢትዮጵያውያኖች መብት ሁሉ ያንተ መብት አይደለም ይመስለኛል የምንሊክ ሃሳብ። ይሄን ውሳኔ የሚቃረኑ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ ግን እስኪ ደሞ ዘንድሮ እየተደረገ ያለውን እንመልከት። መሬትትህን ሽጥ ወይም ልቀቅ ? ገበሬ ” ወይ መራራ ራሳቸው ” ለምን የህንድ ገበሬ እንዲያርስበት። አዩ ያባቶት አለመዝመት ያመጣብዎ ጣጣ ?
ይቀጥላል

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen