Netsanet: እኔ እኮ ከማይገባኝ ነገር ውስጥ የኢትዮጵያ ህዝብ እምቢ ካለ… አምባገነኖች ምን መብት ይኖራቸዋል፡፡

Montag, 26. Mai 2014

እኔ እኮ ከማይገባኝ ነገር ውስጥ የኢትዮጵያ ህዝብ እምቢ ካለ… አምባገነኖች ምን መብት ይኖራቸዋል፡፡

May 25/2014
‪#‎አብቢን‬ ‪#‎ሳምቮድሶን‬
እኔ እኮ ከማይገባኝ ነገር ውስጥ የኢትዮጵያ ህዝብ እምቢ ካለ… አምባገነኖች ምን መብት ይኖራቸዋል፡፡ የሶሊያና ቤት ተበረበረ እና ፍሪጁ ጀርባ ወይ ምናምን ስር የግንቦት ሰባትን መርህና ራዕይ የያዘ ወረቀት በማግኘታቸው በዚህ አሳብበው ሊከሷት አስበዋል ምናምን እያልን እንዘግባለን እንፅፋለን፡፡ በራሪ ወረቀቱን ያመጡት ራሳቸው ፖሊሶች መሆናቸውን ስለነቁ እናቷ አልፈርምም አሉ ምናምን አንላለን፡፡
እኔ ግን እዚህ ላይ መድረስ አልፈልግም፡፡ እውነታውና ስለስርዓቱ ስርዓት አልበኝነትና የሚሰራቸውን ሁሉ ላለመደገፍ ከዚህ በፊት ማንም ሰው የፈለገው ጉዳይ ላይ የሚያጠነጥን መፅሃፍ ይዞ ሲያነብ ቢገኝ ችግሩ ምንድን ነው ስለዚህ የነፃ ፕሬስ ህጉ ጋር የሚጣረስ ከነፃ የመናገር የመፃፍና የመናገር ህግና መብቱ ጋር የሚጋጭና የሚጣረስ መሆኑ ብቻ የመንግስትን ሴራ ልናወግዝ እንችላልን በቂ ነው፡፡
የኔ መከራከሪያ ሃሳብ ያለው እዚህ ላይ ነው፡፡ አንድ መንግስት ወይም ስርዓት የስልጣን ዘመኑን ለማራዘም የፈለገውን መንገድ ይጠቀማል፡፡ ይገድላል፡፡ ያስራል፡፡ ያደረሰበት ሳይታወቅ ብርቅየ የሃገር ልጆች ደመ ከላባት ሆነው ይቀራሉ ወዘተ…
የኔ ጥያቄ መንግስት ስለሚገድልበት ስለሚከስበት ስለሚያስርበት ስለሚያሰቃይበት ምክንያት ገለመሌ አደለም…የኔ ሃሳብ ህዝብ የፈለገውን በፈለገው ሰዓትና ቦታ የመስራት መብት ሊኖረው ይገባል፡፡ ማንም ላይ በተግባር የተገለፀ ጉዳት አድርሶ እስካልተያዘ ድረስና ጉዳት እስካላደረሰ ድረስ፡፡ አደለም ማንበብ፡፡ አደለም መፅሃፍትን ይዞ መገኘትና ማንበብ መፃፍ መግዛት ወንጀል ስለመባላቸው አስፈላጊነት ለመናገር ይቅርና ማንም ሰው ከፈለገ ለምን ከሳይጣን የባሰ አለ እንዴ ለምን የሳይጣንን መመሪያኛ ራዕይና የስራ መርህ ይዞ አይገኝም፡፡
ኧረ ስዎች ምንድን ነው እየሆንን ያለነው፡፡ አፍተር ኦል እኮ እኛ ስዎች ነን፡፡ ማን ነው እኛን ወክሎ ህጉን እያረቀቀና እያወጣ ያለው የሚለውንም ማየት ያሻናል እኮ…እኛ የመረጥናቸው ቢሆኑም እንኳን የመቃወም በተግባርም ሆነ በመርህ ደረጃ የመቃወም መብት አለን እኮ፡፡ አደለም እኛ ፈልገንና ፈቅደን በምርጫ ባሎት ያልወከልናቸው የሚያወጡትን ህግና ደንብ ማፍረስ ይቅርና…
ሮበርት ኤ. ሄንሌን እንደሚከተለው ያለ እኮ ወዶ አደለም ይህ ነው መርሃችንና ህጋችን መሆን ያለበት
…"እኔ ነፃ ነኝ፣ ምንም ያህል የህግ እና መመሪያ ጋጋታ ቢከበኝም ቅሉ የምታገሳቸው ከሆነ ብቻ እታገሳቸዋለው፤ እኔን ግጥም አድርገው የሚያስሩኝ እና ነፃ የማያደርጉኝ ከሆነ አላከብራቸውም እጥሳቸዋለው…ምክንያቱም ነፃ ነኝ!! ምክንያቱም እኔ ራሴ የህሊና እና ሞራል ሃላፊነት አለብኝ ለእያንዳንዱ ለምሰራው ሁሉ…"
ያለው እኮ ለዚህ ነው፡፡ ፀረ-ሽብር አዋጁን አምነን ተማምነን የመረጥናቸው አካላት አውጥተውት ተቀብለናል እንዴ…? ተቀብለናል? በቃ ካልተቀበልን ለምን ወረቀቱን ፖሊስ ነው ያመጣው ገለመሌ ወደሚል እንገባለን፡፡ ለምን ክፍተትና ቀዳዳ እንፈጥርላቸዋለን፡፡ ለምን እንደተቀበልነው ሁሉ ስለአፈፃፀሙ እንከራከራለን? ለምን ስለአተገባባር ክፍተቱ እናወራለን፡፡ የኛ ጥያቄ ያለው እኮ ገና ህጉን አለመቀበል ላይ ነው፡፡ ሶልያና ቤት ምንም ላይ የሚያጠነጥን ወረቀት ይገኝ ጥያቄያችን ግን መሆን ያለበት
ሶልያና ለምን በአርቲቡርቲ የፍርድ ቤት የስካር ደብዳቤ /እንዲያውም በፍ/ቤት ተፅፎ ከሆነ/ እንዳሻቸው ይፈትሻሉ? እሽ ይፈትሹም፡፡ ለምን የመናገር የመፃፍና የማንበብ መብቷ አይከብርላትም ነው መሆን ያለበት የዛሬዋ ገፈት ቀማሽ እርሷ የነገ ደግሞ እኛ ስለሆንን፡፡ ግራ አንጋባ እንጅ ስዎች!!!
…ሶልያና የፈለገችውን ምንበብ መብት አላት፡፡ ምንም እቤቷ ይገኝ ምን ሶልያና ወንጀለኛ ልትሆን የምትችለው አሸባሪ ሆና ጥፋት ካደረሰች ብቻ ነው… ፀረ-ሽብር ህጉን እኛ አልተቀበልነውም፡፡ ሶልያና አትቀበለውም /አስፈራርተው በዶክመንትሪ ብቻ እቀበላለው እንዳያስብሏት እንጅ/ ሁላችንንም ወህኒ ለማውረድ የተፈበረከ ዝክንትል ነው እንጅ ማን ይሁን አለና ህጉን ለመቀበል ኢቭን ባለስልጣናቱ ራሳቸው እኮ አይቀበሉትም እኮ… ለአፈና እንደሆነ ስለሚያውቁት ግን ለስጣናቸው ብቻ ሳይሆን ስልጣናቸውን ቢለቅቁ እና ሌላ ሃይል በምንም መንገድ ቢረከብ የሚደርስባቸውን ካጠፉት አንፃር ስለሚያስቡት ሁሉ ምንም በማድረግ ለህዝቡን /ለእነርሱ ለጠላታቸው/ ክፍተት ላለመክፈት እንጅ፡፡
እኛ በመረጥናቸው ስለዜጎች መብት /የእኩልነት ጉዳይ ገና ሳይነሳ እንኳን/ በቆሙ ተወካዮቻችን የወጣ ህግ ባለመሆኑ…አንቀበለውም፡፡ በመረጥናቸው ቢወጣ እንኳን ከመቃወም እስከ አለመቀበል መሄድ መብት አለን ምክንያቱም ዲሞክራሲያዊ እና ሰብአዊ/ተፈጥሯዊ/ መብቶቻችንን እስካላከበረ ድረስ ህግ እግሩን ይብላ አንቀበልም ማለት መብታችን ነው ዲሞክራሲያዊ ሳይሖን ሰው በመሆናችን ብቻ ያገኘነው መብት ነው፡፡ ከእንሰሳት የምንለይበት ዋናው ጉዳያችን እኮ ማማዛዘን ይህኛው መልካም ይህኛው ክፉ ብለን መፈረጅ መቻላችንስ አደል እንዴ፡፡
በምድረ ኢህአዴግ ካድሬ ፓርላማ ተወካይ የፀደቀና ለስልጣን ማራዘሚያ ዜጎች ስለመብታቸው እንዳይቆሙ ማሸማቀቂያና ከዛሬ ነገን ለመጠቀም ሲፈልጉ ብቻ ገዥ ሳናደርገው ገዥ የሆነብን፤ ስርዓት ሳይኖረው ስርዓት ነኝ እያለ ራሱን እንደ ነፃ አውጭ አድርጎ የሚጠራው የኛ መንግስት ሳንለው መንግስታችሁ ነኝ የሚለው ግፈኛ አገዛዝ የጫነን ዳውላ ነው እንጅ ማን ተቀበለውና እስቲ ይህንን ብጣሽ ፅሁፍ ከምታነቡት ውስጥ የሚቀበለው አለ? ይህንን ፀረ-ሽብር ህግ /ምናልባት ለነፃነት እና መብታችን መታገላችን ለጊዜው ሳያውቁ አውቀውም ለሆዳቸው ሲሉ ብቻ የሚቃወሙት ሆድ አደሮችና ፍርፋሪ ለቃሚዎች ሊቀበሉት ይችላሉ/ ነገር ግን ሲውል ሲያድር እንደ አቶ ኤርሚያስ ለገሰ አብረው ያወጡትን አንድ ወቅት አብረው የጨፈሩለትን ስንቶችን ከርቼሌ የከተቱበተን ህግ ቀን ሲጥላቸው እና ቀን ሲያነሳቸው ስርዓቱን ሲከዱ ዜጎችን ለማፈን የተጠቀመበት ዘዴ ነው ገለመሌ እያሉ ምንም እንኳን እኛ እና እውነቱ የሚሻውን ቢሉም እንኳን እነዚህ ስዎች ለፍርድ ከምቅረብ ውጭ እኛን ወክለው ስለ እኛ የመናገር ሞራል ሊኖራቸው አይገባም፡፡ ፀረ-ሽብር ህጉን ያብጠለጥላሉ ልክ እንደ እኛ ግን ያወጡት እነርሱ ናቸው እኮ /አይ ሰው ለሰው ሞት አነሰው አለች…/፡፡
ስለዚህ መሰረታዊ ጥያቄያችን ሶልያናን በምንም ያዛት በምን በምንም አሰራት አሰቃያት በምን… ለምን መታሰር አስፈለጋት የፈለገችውን ቤቷ ውስጥ ይዛ ብትገኝ እስካላሸበረች ድረስ ለምን ወደ ወህኒ ትሄዳለች ለምን ቤቷ ያለፈቃዷ ይፈተሸል /አንዲት የፍ/ቤት ትዕዛዝ ብቻ ስለተጣፈች/ ፍርድ ቤቱ የማን ነውና በማን ስር ነውና…ቀድሞ ነገር ለምን ስላነበበች /ያነበበችው ምንም ይሑን ምን ስለምንም ይሑን ስለምን ስለማንም ይሁን ስለማን/ ለምን ትታሰራለች ነው እንጅ መሆን ያለበት፡፡ ወረቀቱን ራሱ ፖሊስ አምጥቶ ሲያበቃ…ገለመሌ ለምን እንላለን፡፡
አሁንም የምለው የትግል መሰረታችን እጅግ ከስሩ መሆን አለበት፡፡ ይህን አልን ማለት እኮ ለፋሽሽቱ በር እየከፈትንለት ህጉን እንደተቀበልን ግን ስለሶልያና ስናወራ ስንጠይቅ ችግራችን ሶልያናነ ያልያዘችውን እንደያዘች ተደርጋ ወንጀለኛ ተባለች ባልን ቁጥር እርሷን ወደ ባሰ አዘቅት ውስጥ እየከተትናት መሆኑን መዘንጋት የለብንም ኦኬ…እርሷ ምንም ነገር በምንም ጉዳይ ላይ የማንበብ መብት አላት ነው ዋናው፡፡
የማንበብ የመፃፍ የመናገር መብት ሆኖ ዋናው ህግ ህገ መንግስቱ ላይ ከተጻፈ ምንም ስለማንበቧ ለምን ለማሰሪያ ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ ቀድሞ ነገር ይህ ፓርላማ የሚያወጣው የትኛውም ህግ የኢትዮጵያን ህግ ሊወክለን አይገባም!!! አለቀ፡፡ ኢቭን ለካድሬዎችና ለኢህአዴግ ደጋፊዎች እንኳን አይወክልም ምክንያቱም ኢትዮጵያዊ ናቸውና፡፡
ሶልያና ስላነበበች ታሰረች ለምን ነው ማለት ያለብን ስዎች!!
#አብቢን ነኝ
ኢትዮጵያኝ እ/ር ይባርክ

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen