Netsanet: በአምቦ 47 ሰዎች መገደላቸውን የአይን እማኞችን ጠቅሶ ቢቢሲ ዘገበ።

Freitag, 2. Mai 2014

በአምቦ 47 ሰዎች መገደላቸውን የአይን እማኞችን ጠቅሶ ቢቢሲ ዘገበ።

የኢሕአዴግ መራሹ መንግሥት በአምቦ የተገደሉት 9 ሰዎች ብቻ ናቸው ቢልም በከተማዋ የሚኖሩ የአይን እማኞች ግን 47 ሬሳ መቁጠራቸውን መስክረዋል። ከአዲስ አበባ 125 ኪሎሜትር ከምትርቀው የአምቦ ከተማ ባለፈው አርብ በተነሳው አመጽ ምክንያቱ ኦሮምያ ተብሎ ከሚጠራው ክልላዊ መስተዳደር መሬት ቆርሶ ዋና ክተማውን ለማስፋት የተነደፈውን ፕላን በመቃወም ተማሪዎች ያነሱት ትቃውሞ እስከዛሬ ትኩሳቱ አልበረደም። ለዜጎች እና ለመንግስት ሃይሎች ግጭት የፈጠረው ይህ ተቃውሞ በአገሪቱ ተስፋፍቷል፡፤
አንዲት የአይን ምስክርን በ እማኝነት የጠቀሰው ቢቢሲ ሴትየዋ ከመንገድ ዳር የተዘረጉ 20 አስከሬኖችን መቁጠሯን ስትናገር የአምቦ ነዋሪዎች እንዳሉት አራቱ የተገድሉት ሰኞ ቀን ሲሆን ማክሰኞ ቀን ደሞ ተማሪዎችን በመደገፍ ሰልፍ የወጡት የከተማው ነዋሪዎች ላይ የመንግስት ሃይሎች አነጣጥረው 43 ነዋሪዎችን መግደላቸውን የአይን እማኞች ለቢቢሲ ተናግረዋል። @ ምንሊክ ሳልሳዊ
የበለጠ ዝርዝሩን እዚህ ላይ ያገኙታል፦ http://mereja.com/forum/viewtopic.php?f=2&t=78086

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen