Netsanet: አቡጊዳ – በምእራብ ኦሮሚያ የዘር ማጥራት ወንጀል ተባብሷል

Mittwoch, 14. Mai 2014

አቡጊዳ – በምእራብ ኦሮሚያ የዘር ማጥራት ወንጀል ተባብሷል

May 14/2014
በወለጋ ከኦሮምኛ ተናጋሪዎች ዉጭ ያሉ ኢትዮጵያዉያን ላይ ከፍተኛ ጥቃት እየተደረገ እንደሆነ ከመኢአድ አካባቢ የደረሱን ምንጮች ገለጹ። «በወለጋ ክፍለ ሃገር ከፍተኛ የሆነ ችግር ተፈጥሮል፡፡ በተለይ በጊምቢ ከተማ ኗሪ የሆኑ ከኦሮሞኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ዉጭ ያሉ ይደበደባሉ ይሰደዳሉ፣ ይገደላሉ» ያሉት የመኢአድ መንጮቻችን ፣ አቶ ፍሬዉ አያሌዉ የተባሉ የከተማዋ ነዋሪ በአክራሪ ኦሮሞዎች እንደተገደሉም ይገልጻሉ።
ኦሮሞ ያልሆኑ ዜጎች ንብረትና ሱቅ በስፋት እየተቃጠለ ሲሆን ፣ ሰላማዊ ዜጎች ተደብቀው እንደሚገኙም ለማወቅ ተችሏል። ከጥቂት ቀናት በፊት ኢሳት በኦሮምያ ክልል በምእራብ ወለጋ በጊምቢ ከተማ ነዋሪ የሆኑ የአማራ ተወላጆች፣ ከአካባቢው እንዲወጡ በሚፈልጉ ወጣቶች ቤታቸው እየተደበደበ መሆኑንና ህይወታቸውም አደጋ ላይ መውደቁን መዘገቡ ይታወቃል።
በአዲስ አበባ ዙሪያ በአዳማ ፣ በሸኖና በሰበታ መስመር በኦሮሞዎች እና በሌሎች ኢትዮጵያዉይን ዘንድ ብዙ ችግር እንደሌለ የገለጹት በጉዳዩ ላይ ከአዲስ አበባ ያነጋገርናቸው ተንታኝ፣ ችግሩ የባሰው በቡራዩ መስመር በምእራብ ሸዋና ወለጋ እንደሆነ ያናገራሉ።

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen