Netsanet: የጥሎ ማለፍ ቦለቲካ

Mittwoch, 28. Mai 2014

የጥሎ ማለፍ ቦለቲካ

May 28/2014
#ሳምቮድሶን #አብቢንኢትዮጵያ ሃገራችን ውስጥ ያለውን የፖለቲካ ጨዋታ በትክክልም የጥሎ ማለፍ ጨዋታ የሚያስመስሉት የሚስተዋሉ እውነታዎች አሉ፡፡ የማህበራዊ ድረገፆች ተፅዕኖ የፖለቲካ ፓርቲዎች ህብረተሰባችን ላይ ከፈጠሩት ጫና በላይ ለሃገሪቱ የለውጥ ጎዳና ጥርጊያ ሲፈጥሩ መታየቱ እሰየው የሚያስብል ተቃዋሚ ነን የሚሉ የፖለቲካ ድርጅቶችንም ያስናቀ እደጉ ተመንደጉ የሚያስብል ንቅናቄ ነው፡፡

የአረብ ባህረሰላጤውን ለአብዮታዊ ምንቅስቃስ ያበቃው ፖለቲካ ፓርቲዎች መዥጎድጎድ የፖለቲካ ፓርቲዎች ያላሳለሰ ጥረትና መንግስት የሚሉት አካል ላይ በሚያደርሱት ተፅዕኖ አደለም ነገር ግን ያን ያልል ህዝብ መስዋዕት ተከፍሎበት ድል ለህዝብ ሊሆን የቻለበት እውነት የተቀናጄና በማዕበራዊ ድረገፆች ቅብብሎሽ በሚካሄዱ አብዮታዊ እንቅስቃሴዎች አማካኝነት ነው፡፡

እነዚህ አብዮታዊ ለውጥን ማጎናፀፍና የሚችሉና የሰፊውን ህዝብ ጩኸት ሊያሰሙ ከዚያም ወደ ሙሉ ትግል ሊያስገቡ የሚችሉ ህዝቡን ምንም ያህል ተፈጥሯዊ ልዩነት ሊኖር ቢችልም እንኳን ሃገራዊ በሆነ ጉዳይ ላይ አገርን እና ህዝብን ከማዳን አንግል አንድነታቸውን አንድ አድርገው ተፋቅረውና ተሳስበው እንዲታገሉ ተፅዕኖ መፍጠር የሚችሉ የአረቡ ክፍለዓለም አብዮት ቀስቃሾችና ለውጥ አራማጆች በዚህም ስኬታማ ነበሩ ምንም እንኳን አብዮታዊ እንቅስቃሴው በተሳሳተም መንገድ በመሄድም ይሁን በትክክለኛ ብቸኛ አማራጭ ሄዶ የብዙ ህዝብን እና ንብረትን መስዋዕትነት ጠይቆ መንግስት ነኝ ባዩን አምባገነን ስርዓት ሁሉ አፈር ድሜ ቢያበላም፡፡

የሆነው ሁሉ ትክክለኛ የለውጥ መስመር ላይሆን ይችላል ነገር ግን የትኛውም የለውጥ መስመር ይሰመር ዋናው ጉዳይ ብሄራዊ እና ሃገራዊ እዲሁም ህዝባዊ ጉዳይ ላይ አንድ መስመር ብቻ መያዙ ላይ ነው፡፡ ይህም ደሞ አንድ መስመር መያዙ ግዴታ ነው፡፡ ይህ ባልሆነበት አግባብ ትግሉ ከሚፈልገው ደረጃ በሚፈልገው ሰዓትና ወቅት ለድል ይበቃል ማለት ላም አለኝ በሰማይ ነው… ምክንያቱም ድል የብዙዎች ኋላ ደጀንነትንና የብዙዎችን ፊታውራሪነት የሚጠይቅ ምናልባትም ከፊት ለፊት ብቻ ግጭት የሚሻ በጎን ከኋላ ግጭትን መጋጋጥን የማይፈልግ ሊሆን እንደሚችልም መገመት አስፈላጊ ነው፡፡

ይህ ሲባል ግጭትና መላላጥ መጋጋጥ አይኖርም ለማለት ሳይሆን መላላጥና ግጭቱ ከፊት ለፊት ከአንድ አካል ማለትም ልንለውጠው ከሚገባው ከምንታገለው አካል ብቻ መሆን አለበት፤ እርስ በራሳችን ሽህ መስመሮችን በልዩነቶቻችን ልክ እና በግለሰቦች ግላዊ ዓላማ መሳካት ልክ ተለያይተን ለትግል የተለያዩ መስመሮችን ግንባሮችን የምፈጥር ከሆነ አንድም ደጋፊ ሃይላችን ስንከፋፍልና ስንበታትነው በአንድነት የሚኖረውን ጥንካሬና አብሮነት መንፈስ አንድነታችን እየበታተንነው መሆኑን መዘንጋት የለብንም ኢህአዴግ ወያኔም ይህንን ክፍተታችን ነው እየተጠቀመበት ዕድሜውን እያራዘመበት ያለው፡፡

ስዎች ኢህአዴግ አንድነታችን ወዶ አደለም የሚፈራው መመከት ማይችለው ናዳ እንደሆነ ያውቃል አንድነታችን አንድ ብቸ ጠንካራ ብቻ አደለም የሚያደርገን አንድነታችን በሁሉም አቅጣጫ ያሉ የውጭም ይሑን የውስጥ አካላት ትኩረታቸውን አንድ ማንነታችን ላይ ሲያሳርፉ ትኩረታቸው ሁሉ ያለንን ጫና የመቀበል እንጅ ያለመቀበል ማቅማማት አያሳዩም፡፡ ይህም ሌላው ጥቅም ነው አንድ በሆንን ቁጥር፡፡

ኢህአዴግ ወያኔ አረመኔና አስከፊ የአደገኛ ቦዘኔ ስብስብ አምባገነን ስርዓት መሆኑን ማንም አደለም ህዝቡ ራሱ አህአዴግም ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ ይህ ችግር እንደማያመጣበትም ጠፍቶት ሳይሆን ይህንን ችግሩን በዚህ ባህሪው ምክያት የሚመጣበትን ፈተና እንዴት መወጣት እንደሚችል ስለሚያውቅ እንጅ፡፡ ይህ የሚያውቀው የፈተናው የህዛባዊ አመፅ ማስታገሻ ብቸኛና ያለ የሌለው መፍትሄና ማሻሪያው ግን አንድና አንድ የሆነ በመካከላችን እንደ ጎርፍ እየሰረሰረ በመግባት ልዩነቶቻችን በመካከላችን በመርጨት እኛ ስንናቆርለት እርሱ የሰራውን ቢሰራም ያለ አንድነታችን ምንም እንደማናመጣ ያውቃልና በእርስ በእርስ ልፊያችን እንደ ሳይጣን ሳናየው ይስቅብናል፡፡ ይህንን ስለማድረጉ ደግሞ ከአመታት በፊት በድብቅ ሲያደርገው ነበረውን አሁን አሁንማ በግላጭ በጠራራ ፀሃይ ሃውልት እስከ መስራትም ደረሰልን እኮ የእኛ ጀግና ስርዓት አልባ መንግስታችን፡፡

ይህች ብቸኛ አማራጭ ብቻ እንዳለቸውም ያውቃል ለዚህም ነው ወገቡን አስሮ ያፋጀን ያሰበው፡፡ ይህንን ነው መታገል ያለብን በመካከላችን ኢህአዴግ እየሰረገ እየገባ መከፋፈሉን ተገንዝበን እኛም እየተከፋፈልንለት መሆኑን አውቀን ይህም የኢህአዴግን የስልጣን ዘምን ሲያራዝም የኛን ነፃነት ትግል እንደሚያቆረቁዘው አስበን ራሳችን ከተኛንበት ምቹ የስንፍና አልጋ ላይ ነቅተን ማውረድ አለብን፡፡ ይህች ብቸኛ አማራጭ ማለትም "…ታሪካዊ ክፍተትን መጠቀም…" መንግስት እንደትልቅ እድል ቆጥሮ አጋጣሚዋን ህዝብ ሳያውቅበት ማስፋፋት ይፈልጋል ሆኖም እድሜ ለነፃነት ታጋይ አጋሮቻችን በተለያዩ ሚዲያዎች

…ኢህአዴግ አቁም ነቅተንብሃል እኛ አንድ ነን በአንተ ሴራ አንከፋፈልም ኢትዮጵያ አንድ ናት ህዝቦቿም አንድ ናቸው…፡፡

እያሉ በመለፈፍ አሁን አሁን ህዝቡ በመጠኑም ቢሆን በመንቃት ላይ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ እዚህ ላይ የመብት ጥያቄ የይገባኛል ጥያቄ የብሄራዊ አንድነትና ክብር ጥያቄ ያነሳል ኢህአዴግ ለመልሶቻችን ምንም አይነት ደንታ የለውም፡፡ ያችን ቁልፍ ታሪካዊ ክፍተትና ልዩነቶቻቸን ብቻ ዞር ማድረግ ነው መፍትሄው ብሎ ስርዓት አልባው መንግስትም "ከፈሱም አይጥፈን"፡፡ ለምን ስንል ደግሞ በእጁ የተፃፉትን መፅኀፍት አንብቦ ምሁር የሆነ የሚመስላቸውን ጅልና የስርዓቱ መሃይም አቀንቃኞችን በመጠቀም የታሪክ ክፍተቶችን በአንድ ሌሊት ቁጭ ብለው ያነቡና ያንን ክፍተት የሚሉትን የታሪክ ሽንቁር ካለ እንኳን ተምረንበት ልናልፍ የሚገባውን ሊደገሙ የማይገባቸውን ስዕተቶችን /ምናልባት ካሉ/ራሳቸውን ለህዝብ ባላደረጉ በስርዓቱ ልሳናት አንድም ቀን ህዝብን ከማደንቆር ውጭ አንድም ፋይዳ የሌላቸውን ልሳናት በመጠቀም ለሚዲያ ያበቁታል፡፡

ይህንን ሽንቁር አነበብኩ ለካስ እንደዚህ ነበር ብሎ ራሱን እሳት ውስጥ መክተቱን ያላወቀውና ለስርዓቱ መጠቀሚያ ማሽን እየሆነ እንዳለ ያላወቀው ምስኪን የየትኛውም ቋንቋ ተናጋሪ ኢትዮጵያዊ ደግሞ ያራግበዋል፡፡ ካነበበው ላይ በራሱ የወግ ማጣፈጫ ሲጨምር እንኳን ሌላ ቃል ሲጨምር አሁንም ሌላ ሲጨምር… ቆልሎ ቆልሎ ስርዓቱ ሊጠቀምበት ካሰበው በላይ በማድረግ ለሚቀርቧቸው ሁሉ ይነዙታል፡፡ ያኔ ኢህአዴግየ በክፍተቶች ስፋት በተፈጠሩት ልዩነቶች እየጨፈረ ዳንስ ቤት ለዳንስ ቤት በየፖለቲካ ዳንስ ቤቶች እና ሙዚቃዊ ዳንስ ቤቶች ሁሉ እየዞረ ሲዘልል እንደ እንቦሳ ሲቦርቅ ያድራል… ያኔም ሌላ ሴራ ይሸርባል፡፡

በጣም የሚገርመኝ ሁለት ነገር ውስጥ የኢህአዴግ ደካማ ጎናችን ወይም ኳርታችን ማወቅ መቻሉና እኛ ደግሞ ያለብንን ያላረጋገጥነውን ከየትም ያገኘነውን ወሬ የመንዛት አባዜ እውነቶች ናቸው፡፡ ህዝቡ በተለይ ሳያውቁም ሆነ እያወቁ አንዳንድ ለስርዓቱ መሳሪያ የሚሆኑ አካላት በልዩነቶቻችን የሚገቡ ጋሬጣዎችን ስንጥሮችን ያለ የሌለ ሃይላቸውን በመጨመር ግንድ ያህል ያሳድጓቸዋል፡፡ እነዚህን ግንዶችም ወደ ድልድይ ያሳድጓቸዋል… ድልድዮችንም ይሰብሩና ያለያዩትና ዓለማትን ይፈጥራሉ ሃገራትን ይመሰርታሉ ከዛም እናንተ ሌላ እነዚህ ሌላ ምን አገናኝቷችሁና አንድነትን ትሻላችሁ የሚል አስተሳሰብን ይጭኑብናል፡፡

ይህን የሚያደርጉት ኢትዮጵያዊነታቸውን ረስተው ጎጠኛና ራሳቸውን ለሚያዩትና ሚሰሙት ብቻ የሚያጠቡ ከእንሰሳ ያልተሸለ አስተሳሰብን ይዘው በአንድ በኩል ኢህአዴግን የሚታገሉ የሚመስላቸው በሌላ በኩል ደግሞ ሳያውቁትም ሆነ አውቀውት ለዚሁ ሳይጣናዊ ስርዓት የሌለው ስርዓት መሳሪያ ሆነው የሚያገለግሉ እነዚህ ልዩነቶቻችን በመፈጠራቸው ለሚደሰተው የስልጣን እድሜውን ማራዘም ለሚፈልገው መንግስት ትልቅ የምስራች እየፈጠሩለት እንደሆነ አለማወቃቸው ያሳብዳል፡፡

ታዲያ ይህ የእቅልፋሞችና አንድም ሳያውቁ ያወቁ የሚመስላቸው አካላትና የስርዓቱ አገብጋቢዎች ባይኖሩማ መች ይሕን ያህል ልዩነነት ይኖር ነበር፡፡ መች ያለፉት ስርዓቶች የተባለውን ያህል ግፍ ሰሩና… መች ያለፉት ስርዓቶች የሚነገርላቸው መልካምና አስተማሪ ተግባራትበን መስራታቸው አደለም ኢትዮጵያዊውን አለምን ማስተማር የሚችሉ ተግባራትና ስኬቶችን አጡና… መች ከስዕተቶቻቸው መማርና አለመድገም ሲገባን መች ከስዕተቶቻቸው ሌላ የከፋ ስዕተት እንማር ነበርና…

ይህን ሁሉ ሴራ ማን ሸረበውና…ይህንን ሁሉ ቂም እና ሳል ማን አቋረሰንና ኢህአዴግም አደል እንዴ…ይህን ሃቅ የሚክድ በምንም መስፈርት ጤነኛ አዕምሮ አለው ማለት አይቻልም፡፡ ይህንን ሃቅ ክዶ ሊያስተባብል የሚፈልግ ጤነኛ አዕምሮ የለውም ካልን ደግሞ የምንመራው ምንም ጤነኛ አዕምሮ አላቸው በማንላቸው አካላት ነው ማለት ነው፡፡

እጅግ በጣም የሚያሳዝነኝ እኮ ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ ስንትና ስንት መስራት እየቻለና እየሰራ ይህንን ሴራቸውን አውቀው ከሚደግፉት ልበ ስውራን ይባስ ማወቅ አለመቻልና ኢህአዴግን አውቄብሃለው ኢትዮጰያ የምትባል ሃገር እንዳትኖር ካለህ የቆየ ህልም ነው ብሎ አንኳን በአደባባይ ወጥቶ የተከፋውን ያህል መታገል አለመቻሉ እና ለመታገልም ለሆዱ ሲል ብቻ እና ከኔ እስኪደርስ በሚል ራስ ወዳድ ድድብና መነሳት አለመቻሉ የአንዱ ኢትዮጵያዊ መበደል በቡድንም ሆነ በግለሰብ የራሱ መበደል የራሱ መለገፋት መሆኑን ለዛች ቅፅበታው ጥቅሙና ሰላም አብሮት እንደሚኖረው ሁሉ ለሃብት እና ሆዱ ሲል ሰላምና የሰፈነባት የዜጎች መብት የተከበረባት ሃገር ከሌለች ሃብቱን አብሮት እንደሚቀበረው ሁሉ ድምጥማጡን አጥፍቶ መተኛቱ ነው፡፡

ስለዚህ መጀመሪያ ይህንን ሃይልም ማንቃትና ለሌሎች በደል መነሳትን ማሳየት አለብን፡፡ በመሰረቱ አንዱ ሲበደል ዝም ብሎ ማለፍን እንደመብት የሚቆጥር ሰው መብቱ እንደሆነ አድርጎ የሚያስብ ከሆነ ትልቅ ስዕተት እየሰራ እንደሆነ ሊያውቀው ይገባል፡፡ ዝምታ ዝም ማለት ከሚገባው ቦታ ላይ እንጅ የብቃት መለኪያ የአዋቂነት የሃብት የስብዕና መለኪያ አወንታዊ ምላሽ አደለም፡፡ ዝም ማለት ሳያስፈልግ ዝም ማለት ጤና መጉደል እንጅ ጤነኛነት አደለም፡፡

የራበው ህዝብ መብላት የሚጀምረው መሪውን ከዛም የተመሪ መሪዎችን ነው፡፡ እያለ ይቀጥላል፡፡ የተራበ ህዝብ የራቡን ጥማት ሁሉ ይወጣል፡፡ የሚርበው ምግብ ብቻ ላይሆን ይችላል፡፡ ስንት እራብ አለ ስዎች እንንቃ እንጅ፡፡ የዲሞክራሲ ርሃብ አለ፤ የየትኛም ነፃነት እራብ አለ፤ የምግብ ረሃብ አለ፤ የልብስ ረሃብ አለ፤ የመሰረታዊ ፍላጎት ምሟላትና አለመቻል ረሃብ አለ፤ እጅግ ብዙ ምናልባትም የህዝቡን ቁጥር ያህል የተለያየ ረሃብ አለ፡፡ እኛ ሃገር ላይ ሁሉም አይኘት ረሃቦች አሉ፡፡ ታዲያ ይህ ህዝብ የራበውን ያህል መልስ ባልተሰጠው ቁጥር ረሃቡም በጣም እየራበው ረሃቡን ማርኪያ ፍላጎቱም በጣም እየናረ ነውና የሚሄድ ይህንን በሁሉም አቅጣጫ የራበው ህዝብ ማርካት ግድ ይላል፡፡ ለረሃብ አምጭና ለርሃብ ተባባሪ መሆንና ረሃብ በበር ሲያልፍ ዝም ብሎ ማሳለፍ በራበው ከመበላት አያድንም ብያለው፡፡

ኢህአዴግ ብልጥ ነው ማለትም ይቻላል፡፡ አንዱን የህዝብ ጥያቄ በሌላ ህዝብ ጥያቄ ነው እንዲረሳ የሚያደርገው በደልና ግፎችን ሲደራርባቸው መነሳት የሚገባው ሳይነሳ መነሳትና መዘብዘብ የሌለበት ላይ ህዝብ ጊዜውን ያጠፋል፡፡ ይህም ኢህአዴግን ይጠቅመዋል፡፡ ህዝቡ ቀልቡን ሰብስቦ አንድ ጥያቄ ይዞ ምላሽ ፍለጋ ወደ እሱ እንዲሄድበት አይፈልግም፡፡ ለዚህም ነው ህዝብ አንድ ጉዳይ ላይ ጥያቄ ሲያነሳ ሌላየህዝብ ጥያቄ ሊሆን የሚችል ጉዳይ እያወቁ ያመጣሉ ያጠፋሉ፡፡ ያኔ እንደለመድነው ጯጩኸን ዝም እንላለን፡፡ አስቡት እስቲ ስንት ጉዳዮች አስጩኸውን ስንቶችን ረሳናቸው፡፡

ይህ በትግል አንድነታችን እያመጣን እያለ ሌላው ደንቃራችን ነው፡፡ የሃሳቦች መበታተን ገጥሞናል፡፡ ይህን ጉዳይ ማሰሪያ ለማበጀት ደግሞ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ትልቅ ሚና አላቸው ሃላፊነትም አለባቸው ጥቅልል ያለ ፖሊቲካዊ ጥያቄ እንድናነሳ መሪ ልትሆኑን ይገባል እስከመፍትሄው ድረስ እስከመጨረሻው መታገል ያስፈልጋል መፍትሄ ካልተገኘ ደግሞ መጮህ የሙስሊሙ እንቅስቃሴ ምርጥ ምሳሌ ነው ለዚህ፡፡

በትርኪ ምርኪው ሁሉ ከምታስጮኹን ይልቅ ጥቅልል ያለ ሃሳብና ጥያቄ ይዛችሁ ጥያቄያችን ጥቅልል አድርጋችሁ አታግሉን መፍትሄውን እስክናገኝ ድረስ አስቀጥሉን፡፡ እኛ እስከመጨረሻው አብረናችሁ ነን ልንላቸውም ይገባል አለያ ይህ የጥያቄ ፖሊቲካ ጥሎ ማለፍ የትም አያደርሰንም፡፡ ጥያቄያችን ተቀጣጣይና የብዙሃኑን ነፃነት ናፋቂ ሃሳብ የያዘ እና እስከመፍትሄው ልንሄድለት የምንችለው እጅ መሆን ያለበት እንዲያው ለይስሙላ ምን ያህል ህዝብ ኢህአዴግን ይጠላዋል እስቲ ምን ያህል ህዝብ ለሰላማዊ ሰልፉ ይወጣል ገለመሌ ብሎ ዘላቂ ያልሆነ አላማ ይዞና እንዲያው ለከንቱ የሚዲያ ውዳሴ ብለን ከወጣንና ሰላማዊ ሰልፍ ምናምን ከጠራን ስዕተቱን የሰራችሁት እናንተ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ናችሁ፡፡ በእርግጥ የፋይናንስ ምንጭ ችግር ሊኖር እንደሚችል ጠፍቶኝ አደለም፡፡ ብዙ ጊዜ ወጣን እኮ፡፡

ነገር ግን ያነሳናቸው ምን ያህል ጥያቄዎች ናቸው ምን ያህሉስ ምላሽ አገኙ? ምን ያህሉንስ እስከምላሻቸው ድረስ ልንሄድባቸው አስበናል? በበነጋታው ለምንረሳቸው ጥያቄዎቻችን ከሆነ የምንጮኸው ከዚች ዕለት ጀምሮ ማንም ሰላማዊ ሰልፍ ብሎ ባይወጣ የሚኖረውን ያህል ዋጋ ብቻ ነው የሚኖረው ባይ ሆኘ እንዳላርፍ የውጭ ተፅዕኖ መንግስት እንዲያርፍበት ስለሚያደርግ ሃሳቤን በዚህ አልቋጨውም ሆኖም ግን ትግላችን እስከ እስርና አስከ ቃሊቲ እስኪያበቃን ሳይሆን መሆን ያለበት አስከ ምላሽ ማግኘትና እስከ የሚታይ ለውጥ ድረስ መሆን አለበት፡፡

ጥያቀዎቻችን ካለተመለሱ አሁንም ያንኑ ጥያቄና አዳድስ ጥያቄዎቻችንን የመብት ጩኸታችንን ማቅለጥ ምላሽ እስኪያገኙና ለውጥ እስኪመጣ አለያ ግን ውሃን ቢወቅጡት እምቦጭ ነው ሚሆነው፡፡ እስቲ ሁላችንም ልብ ይስጠን፡፡

ቀጣይነት ያለው ያላሰለሰ ትግል ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ አለያ ጠየፖሊቲካ ጥሎ ማለፍ ስልጣን ላይ ላለው ሲጠቅም ለነፃነት ናፋቂው ግን ክስረትና የከፋ ግፍን ያስከትላል

#አብቢን ነኝ

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen