Netsanet: የማለዳ ወግ … እነሆ የጨለመው ነጋ ! … ነጻ ወጣሁ ! አመሰግናለሁ (ጋዜጣኛ ነብዪ ሲራክ)

Samstag, 3. Mai 2014

የማለዳ ወግ … እነሆ የጨለመው ነጋ ! … ነጻ ወጣሁ ! አመሰግናለሁ (ጋዜጣኛ ነብዪ ሲራክ)

May 2, 2014

እነሆ 60 ፈታኝ የመከራ ቀናቶች በትዕግስት ተገፍተው አለፉ ፣ ክፉውን ቀን ለማለፍ የትዕግስት ጽናት ብርታት ተስፋየ ምንጩ በመላ አለም የምትገኙ ወገን ወዳጆቸ ነበራችሁና ላደረጋችሁልኝ እና ላሳያችሁልኝ የሞራል ድጋፍ ልባዊ ምስጋና አቀርባለሁ ! አሰልችውን ቢሮክራሲ አልፈው ፣ በማይጨበጠው ቀጠሮ ሳይሰላቹ ሌት ተቀን እኔን ሀፐነው ታመው ጉዳዬን ለምስለኔ አቅርበው ድቅድቅ ጨለማው እነወዲገፈፍልኝ ያደረጉትን ለማመስገን ቃላት ያጥረኛል ! ለደህንነታቸው ስል በስም ለማንሳት የማይቻለኝ ወንድሞቸ ብርታት ፈጣሪ ታክሎበት ለዛሬው ንጋት ደርሻለሁ ! ተመስገን ! ነግቶም በአይኔ ሲንቀዋለሉ ከነበሩት ብላቴና ልጆቸና ከመላ ቤተስብ ዘመደ አዝማድ ጓደኛ አፍቃሪዎቸ ለመገናኘቴ ምክንያት እናነተ በአካል ከጎኔ የቆማችሁ ነበራችሁና በሁሉም ስም ምስጋና ወደር የለውም !Nebyu Sirak Ethiopian journalist in Saudi Arabia
ከማዕከላዊው የብሪማን እስር ቤት ወዳጆቸ …በብሪማን ያላፉ ኢትዮጵያውያን የህግ ታሳሪዎች መካከል በግፍ የታሰሩት አሰገራሚ ታሪኮችን ከእናንተው ጋር በአካል ተገኝቸ ” እህ ” ሰምቸ ተምሬባቸዋለሁ ። በእስር ቤቱ ታዛ እና ግድግዳዎች ላይ የጻፏቸው ማስታወሻና ጥቅሶችን ተመልክቸ ተጽናንቸባቸዋለሁ ። አንዷ ተደጋግማ የሰማኋት ጥቅስ ውስጥ እኔም በመከራው ሳልፍ ተስፋን ሰንቄ እዚህ ደርሻለሁ! ” እኔ መውጣት የምፈራው መውጣት ከማልችለው ከመቃብር እንጅ ፣ መውጣት ከምችለው የብሪማን ወህኒ አይደለም! ” ትላለች ! አዎ ያ ቤት መቃብር አይደለም … በተስፋ ኑሩ ! አካላችሁ እንጅ አዕምሯችሁን ማሰር የሚቻለው የለምና ብሩህ ተስፋን ሰንቁ ! ፍትህ ርትዕ የጎደለባችሁን ድምጽ ዛሬም እንደ ትናንቱ ለምሰለኔዎቻችን አሰማለሁ ! አይዟችሁ !
ለእነ እንቶኔ መረጃ ቅበላየን ጠልታችሁ ላሳደዳችሁኝና ላልተሳካላችሁ ! ” ወደ ገደል አፋፍ ገፋነው ! ” በትምክህት የታበያችሁ ፣ ህልማችሁ ያልተሳካ እኩዮችም ቢሆን ያለመታከት በመስራታችሁ በመንገላታቴ አልተጎዳችሁኝምና ደስ አይበላችሁ ! እግሬና እጆቸ በካቴና ታስረው ወደማላውቀው የወህኒ ህይወት ስወረወር የማላውቀውን አውቄ ፣ ተምሬና ኑሮ በመከራ እንዴት እንደሚገፋ እማር ዘንድ ምክንያት ስለሆናችሁኝ አመሰግናችኋለሁ ! አዎ ዛሬ ነጻ ወጥቻለሁ !
ያሳለፍኳቸው 60 የወህኒ ቀናት ራሴን አዙሬ እንዳይ አድርጎኛል። በቀረጣይ ቀናት አረፍ በፍጥነት ከሚስገመገመው የመረጃ ቅብብሎሽ አውድ ገለል ማለት ባይቻለኝም ለአፍታ አረፍ ማለትን መርጫለሁ! በቀጣይ እረፍት ቀናቶቸ ወደ ብላቴና ልጆቸና ቤተሰቦቸ ፣ያለፉ እና በውዝፍ የቀሩትን የቀሩ የአረብ ሃገር ስደቱኛ ህይወት ከጋዜጠኝነት ህይዎት ተሞክሮው ጋር አዙሬ እመለከተው ዘንድ ግድ ይለኛል!
ከአፍታ እረፍት በኋላ እስክንገናኝ ፣ ሁላችሁንም አመሰግናለሁ: )
ሰለም ለሁላችሁ !
ነቢዩ ሲራክ

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen