May 15/2014
የኢትዮጵያ አየር ሃይል አብራሪ ከድቶ ለኤርትራ እጁን #Ethiopia #EPRDF #AirForce #Ginbot7 #Eritrea #MinilikSalsawi
ሰጠ።
የኤርትራ መንግስት ቃል አቀባይን ጠቅሶ ማዶት ( madote.com )የተባለ ድህረገጽ እንዳለው የኢትዮጵያ አየር ሃይል አብራሪ ከነ አይሮፕላኑ ለኤርትራ መንግስት እጁን መስጠቱን ጠቁሟል።
የሚግ 23 አብራሪ የሆነው ካፒቴን ዳንኤል የሺዋስ በኤርትራ ከሚገኙ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ሃይሎች ጋር መቀላቀሉን ቃላቀባዩ አክለው ገልጸዋል። ፓይለቱ ወደ ኤርትራ አመጣጡን በተመለከተ ዝርዝር መግለጫ አልተሰጠም። የወያኔ ባለከፍተኛ ማእረግ መኮንኖች በተለያየ ጊዜ ከድተው ወደ ኤርትራ ገብተዋል፡፤ ባለፈው መስከረም አክሊሉ መዘነ ጥላሁን ቱፋ ጊቱው ወርቁ ቢኒይም ግዛው የተባሉ የሂሊኮፕተር አብራሪዎች መክዳታቸው የሚታወስ ነው።
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen