Netsanet: ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለመብቱ መታገሉ ለነፃነቱ ጥያቄ ማንሳቱ ሰለማዊ በሆነ መንገድ መጠየቁ የገረመው መንግስት ይህ ነፃነት የጠማው የራበው የቸገረው ህዝብ የከፋ እርምጃ ሊወስድ እንደሚችል ኢህአዴግ ጠፍቶት አደለም ብላችሁ እንዳታስቡ ተሸውዷል፡፡

Mittwoch, 7. Mai 2014

ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለመብቱ መታገሉ ለነፃነቱ ጥያቄ ማንሳቱ ሰለማዊ በሆነ መንገድ መጠየቁ የገረመው መንግስት ይህ ነፃነት የጠማው የራበው የቸገረው ህዝብ የከፋ እርምጃ ሊወስድ እንደሚችል ኢህአዴግ ጠፍቶት አደለም ብላችሁ እንዳታስቡ ተሸውዷል፡፡

May 7/2014
ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለመብቱ መታገሉ ለነፃነቱ ጥያቄ ማንሳቱ ሰለማዊ በሆነ መንገድ መጠየቁ የገረመው መንግስት ይህ ነፃነት የጠማው የራበው የቸገረው ህዝብ የከፋ እርምጃ ሊወስድ እንደሚችል ኢህአዴግ ጠፍቶት አደለም ብላችሁ እንዳታስቡ ተሸውዷል፡፡ ኢህአዴግ አሁን የኢትዮጵያን ህዝብ በሁሉም ተለዋዋጭና መስመር ሁሉ የከፋፈለው የበታተናት ሃገር እንዳለች ነው የሚያውቀው፡፡ ሲጀመርም ገና ወደ ስልጣን መስመር ከመምጣቱ በፊት በጦርነት ከደርግ የሚረከባቸውን ቦታዎች ጎጠጦች ዳገትና ቀበሌዎች ሁሉ በቤተሰብ ሳይቀር እየከፋፈለ በተለያየ ጥቅማጥቅም እያሰረ ልዩነታቸውን ብቻ እያሳየ ሌላ አማራጭ ያልነበረው ህዝብ ሲቀበለው ቆይቶ አሁን በክልል በዞን በወረዳ በቀበሌ እና ሰፈር ድረስ ከፋፍሎ እኛ ህዝቦቹም በተከፋፈልንበት ሁናቴ ሁሉ አንድነት አንድነት ተመሳሳይነት እንዳለን አድርገን ወሰድንለትና በየሰፈሩ አሁን የእንትን ሰፈር ልጅ ከእንትን ሰፈር ልጅ ጋር በጩቤ በድንጋይ ሲፈነካከት ሲተራረድ ማየት ምንም አዲስ አደለም፡፡ የአንዱ ወረዳ ነዋሪ ከሌላኛው ወረዳ ነዋሪ ጋር በሆነ ባልሆነው ሲኮራረፍ ሲገዳደል ሲቀጣቀጥ ማየት ምንም አዲስ አደለም፡፡ አንዱ ዞን ከሌላኛው ዞን ጋር በስራቸው በሚያስተዳድሩት ህዝብ ስም ጥቅም እየነገዱ አንዱን ከአንዱ አባትን ከልጁ እናትን ከልጇ ወንድምን ከወንድሙ ምን አለፋችሁ በቃ እንደምታዩት ሆነን ስንጨራራስ ስተራረድ እንገኛለን፡፡ ሰው ከሰው ጋር ለምን ይጋጫል ለምን ይገዳደላል የሚለው እውነተ ውስጥ አልገባሁም እርሱ ራሱን የቻለ ተፈጥሯዊ ክስተት ስለሆነ፡፡ እኔ እያልኩ ያለውት ግን አሁን እስቲ ታዘቡት በየአካባቢው የመገዳደያ ምክንያቶች ምንድን ናቸው? ግድያው መኮራረፉ መከፋፋቱ እንዲባባሱ የሚያደርጉ እውነታዎችን እስቲ ታዘቡ፡፡ በዛም አለ በዚህ የመከፋፈላችን የመጨረሻ ውጤትና ምክንያት ፍጅት ነው፡፡ ሆኖም ፍጅት ሲባል ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ሊነሳ የሚችለው ፍጅት እንደሁቱና ቱትሲ ይሆናል ብላችሁ ግን አታስቡት፡፡ መቸም ቢሆን ይሕ ጉዳይ ሊከሰት አይችልም፡፡ በብሄር ግጭት ተነስቶ ኢትዮጵያ ሃገራችን ትጠፋለች አንድ ዘር ይጠፋል ማለት አይቻልም፡፡ ለዚህ ራሱን የቻሉ እውነተኛ ምክንያቶች አሉ፡፡ ሌላው ዓለም ላይ የሌሉ ሃገራችን ውስጥ ግን እንደ ዕድል ብቻ ሆኖ ያሉ ሳይማር ተፈጥሮ አስተምራ ያኞረችው ተውልድና ትስስር በመሆኑ ብቻ አብረውን የሚኖሩ እውቶች አሉ፡፡ ኢህአዴግ ግን ከዞን እና ቀበሌ ብሶ የመጨረሻ ሴራውን በክልል በቋንቋ ዘር ቀለም ወዘተ እያለ በባህል በእምነት እያለ የሚታዩና የማይታንን ልዩነቶች እየፈጠረ በመካከላችን ምንም አይነት ስንጥቅ ሳይኖር የኖረን ሆነን ሳለ በራሱ ሴራ እና በአሜሪካና በሶሪያ እንዲሁም ፍልስጤም ሴራ ተጎንጉኖ በወያኔ የተተገበረውን የመሰነጣጠቅ እና ለአስተዳደር ለማመቻቸት በመሰለ ሴራና ተንኮል ህዝባችን አንድነቱ ፍርሶ ጉልበቱ ፈሶ አሞቱ እንዲደርቅ በማድረግ ለራሳቸውየሚጠቅማቸውን ለህዝባችን እና ሃገራችን ግን ትልቅ የአንድነት ነቀርሳን ተከሉብን፡ በምንም መንገድ ከታሪካዊ አመጣጡም ቢሆን እንደተረዳነው ወያኔ ኢህአዴግ ለኢትዮጵያ አንድነት ሳይሆን የታገለው አሁንም የሚሮጠው ለሁለት አላማዎች ብቻ ነው፡፡ አንድም ታላቋ ትግራይን መመስረትና የአማራውን እና ኦርቶዶክስን ተሰሚነት አኮላሽቶ መቅበር ነው፡፡ ይህንን የሚያረጋግጡም በርካታ የምስልና የድምፅ ቅጅዎች በተለያዩ ነፃነት ናፋቂ የየትኛውም ብሄር ታጋዮች እጅ ይገኛል፡፡ ጠ/ሚ መለስ ነፍሳቸውን ከሚያስቀምጥበት ያስቀምጠውና "…እንኳን እዚህ ወርቅ ህዝብ ተወለድኩ…እንኳን ከዚህ ምርጥ ተጋዳላይ ህዝብ ተወለድኩ…እንኳንም የሌላ አልሆንኩ…" ገለመሌ እያለ ሚቀባጥርበት የድምፅና ምስል ቅጅ ያዩአል፡፡ ዋናው ያለውን ልጥቀስ ብየ እንጅ ስንቶች ስንት ብለዋል፡፡ ለዚህም እኮ ነው ኢህአፓ ለኢትዮጵያ አንድነት ቆሞ ለህዝብ መብት እንደ አንድ ህዝብ ለማንም ሳያደሉ የቆሙ ሆነው ሳለ ከዚህ እርጉም ስርዓት ጋር መንትያ ሆነው በአንድ ወቅት ተፈጠሩና ወያኔ ኢህአፓ በገባበት እየገባ ያን ያህል ኢትዮጵያን መቀየር ኢትዮጵያ ሃገራችን ህዝቦቿን አንድ አድርጎ ማኖር ማበልፀግና አሁን እጅግ ከበለፀጉት ሃገራት ተርታ ማሰለፍ የሚችለውን የሰፊውን ህዝብ ድጋፍ ያገኘውን ኢህአፓን ድራሹን አጥፍተው በበረሃ ለወጡለት የተመቻቸ ነሯቸውን ትተው በረሃ የገቡለትን ወር የቀረው የትምህርት ውጤታቸውን ሳይመረቁበት የሄዱለትን ዓላማ መጨረሻ ሳያዩ በየበረሃው አሞራና ጅብ ራት ሆነው የቀሩት፡፡ ወያኔ እና ሻብያ የመከፋፈል ተልዕኮ/ሳይጣናዊ ተልዕኮ/ ኢህአፓ ደግሞ የአንድነት እና ብሄራዊ ክብሯን የጠበቀች ኢትዮጵያን እያለሙ ኢህአፓም/በርካታ አስተዳደራዊ ችግሮች ቢኖሩበትም ቅሉ/ በአጭሩ ተቀጨ፡፡ ኢህአፓዎች የጨረሱትን ትግል ጫፍ ሳያደርሱ በወያኔ አሜሪካ ፍልስጠየም ግብፅ ሱዳንና ሶሪያ ሴራ አፈር ዱሜ በላ፡፡/በዚህ ጉዳይ ላይ ነገርን ነገር እያመጣው ገባሁ እንጅ ዛሬ የማወራበት ርዕስ ሌላ ስለሆነ ልለፈው እና ወደ ዋናው ጉዳየ ልግባ/ …ህዝብ ጭራሽ ከኢትዮጵያዊነቱ ውጭ ምንም በማያውቅበት ሰዓት ህዝቡ ኢህአዴጋዊ የረከሰ የሰፈር ፍልስፍናና መደባዊ ርዕዮት ይዞ እንዲያድግ ለማድረግ ከልጅነት ጀምሮ ደርግ የጀመራቸውን መልካም ተግባራት እንዲህ ዘግይተው ሊሞክሩት ያኔ ግን ማስቀጠል ሳይሆን ያሰቡት ምድማዱን አጥፍተው መልካም ጅማሬዎችን በማጥፋት ደርግ አንድም መልካም ቅርስ እንዳይኖረው እና ለመጥፎ ተግባራቶቹ ብቻ ማስታወሻ ይሆኑ ዘንድ በቦታው የሰማዕታት ሃውልት ገለመሌ እያሉ ሰሩ… ይህንን ስል ብቻ አንተ የደርግ ደጋፊ የቆየው ስርዓት አራማጅ እንዳትሉኝ እኔ ገና የ28 ዓመት ወጣት ነኝ!! ስለደርግ ራሳችሁ የፃፋችሁትን ሁሉ በማገላበጥ እንጅ... ይህን የደርግ ስም ማጥፋት ዘመቻ ሴራው ደርግ ክፉ ስለሆነ ብቻ አደለም…እነርሱ እንደ ፃፉትና ከኢህአፓ ታሪክ በመነሳት ደርግ ክፉ ነገሮችን በሃይል ሚዛን ብቻ መምታት መፍታት የሚፈልግ ድርጅት እንደነበረ የወያኔን ታሪክ ሳይሆን የኢህአፓን ታሪክ በማየት ብቻ መገመት አያቅትም፡፡ በዛ ላይም ደርግ ወያኔ ላይ ይወስደው የነበረው እርምጃ ያለምንም ማቅማማት ትክክል እንደነበረ መመስከር ይቻላል፡፡ ምክንያቱም ታሪካዊ የደርግ ስብሰባዎችን በምናይበት ጊዜና በምናነብበት ሰዓት እንዲሁም የፕሬዘዳንቱን የመንግስቱ ኃ/ማሪያምን ንግግሮች ስንሰማ እስከመጨረሻው ወያኔ ይህችን ሃገር ሊካፋፍላት እየመጣ ነው ሊያስገነጥሉና ሊገነጠሉ ነው ኢትዮጵየ በወያኔ ትከፋፈላለች ስለዚህ ከወዲሁ ይህንን ወንበዴ ሃይል እንምታው ነበር የሚሉት፡፡ በዚህም ጥርጣሬያቸው እጅግ ስለወያኔ ሴራ ጠንቅቀው እንደሚያውቁና በሳል መሪ ግን ግልፍተኛ እንደነበሩ ማወቅ ይቻላል፡፡/መንግስቱ አምባገነን አልነበረም ያለ የለም!!/ እናም ኢህአዴግ /ወያኔዎች/ ደርግን የሚጠሉበት መልካም ቅርሶቹ እንዲጠፉ የሚሹበት ዋናው ምክንያት ደርግ የሃገራችንንን ደህንነትና አንድነት የሚጎዳ ጉዳይ እና እንቅስቃሴ ላይ ሁሉ ምንም የማያዳግም እርምጃ የሚወስድ በኢትዮጵያ አንድነት ላይ የነበረው አቋም አሜሪካ ለአሜሪካ ካላት አቋም እጅግ የጠነከረ ስለነበረ የደርግ ቅርስ ተከበረ ማለት የኢትዮጵያ አንድነት ጥያቄ ታወሰ ማለት ስለሆነ በብቻ ነው፡፡ ለዚህም ነው የትኛውም አሁን ላይ የሚጎበኙ ቤተ-መዘክሮች ብትገቡ የኃ/ስላሴ ሊኖር ይችላል የደርግ ግን አንድም የለም፡፡ ቢኖሩ እንኳን ከመልካም መገለጫቸው ይልቅ የደርግን ክፉነት የደርግን ገዳይነት የሚያጎሉ ቅርሶች ብቻ ቀርተዋል፡፡ በመሰረቱ የአባይ ድልድይንም የማያፈርሱት ነገር ገጥሟቸው ነው፡፡ ያም ሆነ ይህ ኢህአዴግ ፀቡ የሃገራችን አንድነት ጋር የተያያዘ የኦሮሞና አማራ ህዝብ ጋር የተያያዘ ኤርትራና ትግራይን ገንጥሎ አንድ ከማድረግ ቅዠት ጋር የተያያዘ የኦርቶዶክስ ሃይማኖትን ማጥፋት እዲሁም ክርስትናው ዕምነት ጋር እጅና ጓንት ሆኖ ለዘመናት በፍቅር የኖረውን ሙስሊም ማህበረሰብ ድራሽ ከማጥፋት ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ይህን ያግዙት ዘንድ ደግሞ ከጫካ አረቦችና አሜሪካ የሃገራችን መጠንከርና አንድነት ከማይፈልጉት ሃይሎች ሁሉ የቀሰመው ልምድ ስላለው በህዝቡ መሃል እንደ እንክርዳድ ጠብ ጠብ ብለው አሉ፡፡ እነዚህ በተለምዶም ሲቪል ደህንነት የሚባሉ አካላት የነጋዴ ደህንነት ተማሪ ደህንነት የሸማች ደህንነት የመንግሰስት ሰራተኛ ኦዲተር ደህንነት ወዘተ እያለ በሚስጥር ሰግስጓል፡፡ በመሰረቱ ይህ ስለተበላበት አሁን በኋላ ወደ ሃይል እርምጃ የሚገባውም ለዚህ ነው፡፡ ህዝቡ እነዚህ ራሳቸውን የገዥው መደብ ከፍተኛ አድራጊ ፈጣሪ አድርገው የሚያስቡ ደህንነቶችን ጠንቅቆ ያውቃቸዋል፡፡ ይህ ደግሞ ለመንግሰስት ትልቅ ኪሳራ ነው፡፡ ምክንያቱም የመበታተን ሴራውን እና እቅዱን እጅግ እንደሚጎዳበት ያውቃል ስለዚህም ነቅቶ የሚገኘው ህብረተሰብ በተለይ የሶሻል ሚዲያ ታጋዩን ያለምንም ማስረጃና መረጃ ወደ ወህኒ የሚወረውሩት የሚገድሉትም ለዚህ ነው፡፡ በደርግ ሰዓት በደርግ ሰዓት ምናምን በአፄው ዘምን ገለመሌ እያለ ራሱን ያኔ ብላክ ኤንድ ዋይት ስክሪን ቴሌቪዥን ብቻ በነበረበት ሰዓት የነበሩ ስርዓቶችን እያመጣ ይህን ሰራሁ ይህን ሰራሁ እያለ…እኔ ካለፉት መንግስታት እሻላለው እያለ ጀሮአችን ማግማቱ ሲነቃበትና ህዝብ ተወን እኛ የምንፈልገው የብልፅግና ደረጃ ላይ ስላልሆንን እኛ የምንሻው የነፃነት ደረጃ ላይ ስላልሆንን አንፈልግህም ልቀቀን ስላልነው ብቻ እጅ ከፍንጅ እንደተያዘ ሌባ የሚለፈልፍ ለብቻው በተቆጣጠረው ሚዲያ የሚዘበዝበው የነቃውን ህዝብ ላልነቃው ባሰማው ገተት አድርጎ ለመምታት እንዲያመቸው ነው፡፡ አስቡት አሁን በየቦታው ያሉ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊ እና ባህላዊ እምነታዊ እና ሃይማኖታዊ ልዩነቶችና ጥያቄዎች በደርግ ዘምን አልነበሩም እኮ… በደርግ ዘመን የነበረው ችግር ምንድን ነው ስልጣኑን የሚቀሙት የመሰለውን ያውም መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከሆነ የሃገሪቱን አንድነት አላማቸው ይነካል ኢትዮጵያን የሚበታትን ስርዓት ለመመስረትና አላማቸው ለመገንጠልና ለማስገንጠል ነው እንዲሁም ይሕችን ሃገር ከነበረችበት አሮንቃ እና አሃዳዊ ስርዓት ለማውጣት ሶማሌ እና የሻብያ ተገንጣይኛ ወራሪ ሃይላት ልመክት መጀመሪያ አሁን የፖለቲካ ጥያቄ አላስተናግድም ሲል ይህንን አልቀበል ያሉ ስርዓቶችንና እነዚህን በኢትዮጵያ ላይ ጦርነት ያወጁ አካላትን የሚደግፉትን ነው ለቅሞ የፈጀው ከዛም በኋላ በመረጃ ስዕተት ኢህአፓዎችን እንደጨረሰ ነው መረጃዎች የሚያሳዩት እንጅ ለምን አማራጭ አመጣችሁ ለምን ይህንን ርዕዮተ ዓለም ተከተላችሁ ብሎ አልገደለም፡፡ እንዲያውም ደርግ በጣም በሳል የሆነበት የመሪነት ሚና ተቃዋሚዎች በተለይ መኢሶንና ኢህአፓ የሚያመጧቸውን አማራጮች በመተግበርና በመቀበል የራሱ በማስመሰል በርካታ ጥሩ እና አስተማሪ ተግባራትን ተግብሯል፡፡ እውነት ነው ደርግ ሌባ አይወድም ዘራፊ አይወድም ገንጣይ አስገንጣይ አይወድም፡፡ ሽፍታ አይወድም ህዝብን የሚበዘብዝ ከበርቴ ጭቃ ሹም ገለመሌ አይወድም፡፡ ድሃ እንዲበደል አይፈልግም፡፡ ድሃ እንዳይበደል ሲፈልግ ግን ሃብታም ሊኖረው ሊያፈራው ከሚፈልገው ጋር የሚጣጣም ህግ አላወጣም ነበር፡፡ በዚህ እንዳይፈረድበት ደግሞ በዚያ ወቅት ትልቅ እና ተቀባይነት ከነበራቸው ርዕዮት ዓለሞችና ድሃን እንደዜጋ እንደ ሌሎች እኩል ትሪት ከሚያደርጉ ውስጥ የማርክሲዝም ዝና ሌኒኒዝም አስተሳሰቦች የተሻለ ስላልነበረ በዚያ ወቅት በርካታ የተማረ ሃይል የነበረበት ኢህአፓም የሚከተለው ርዕዮት ዐለም ስለነበረ /በሚስጥር ቢያዝም/ ደርግም ይመራ የነበር በዚህ ግራ ክንፍ መደባዊ ያልሆነ ስርዓት ነው፡፡ ደርግ በርካታ አንቱ የሚያስብሉት ትግባራትን ፈፅሟል፡፡ በኋላም ለውድቀት የዳረገው በትክክል ደርግን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ጠልቶት ሳይሆን በመካከላቸው በነበረው ተራ የስልጣን ሽኩቻ ምክንያት በተፈረካከሱ ግለሰቦች የድጋፍ አቅጣጫ መለያየትና ውስጣዊ ሴራ እና አማራጭ በማጣት አንድን የደርግ ወታደር በሁለት ብር ሂሳብ ለወያኔ በሰጡ ባስጨረሱ ጀኔራሎች ሴራ እንጅ በወያኔ ጥኝካሬ እንዳልሆ እሙን ነው፡፡ ያውም ከወያኜ ይልቅ ለዚህ ትግል መስዋዕትነት በመክፈል ድንቅ አሻራቸውን ያኖሩት የሰፊውና የብዙሃኑ ህዝብ ድጋፍ የነበራቸው ኢህአፓዎች ናቸው፡፡ /ሌላ ተመልሰን እንመጣበታልን/፡፡ …ወያኔ ስልጣን እንደያዘ የጀመረው የደርግን ጅማሮዎች በሙሉ ከምድረ ኢትዮጵያ ማጥፋት እና ማቃጠል ወድ የኢትዮጵያ አካል ፊያሜታ የሆነችውን እህታችን አካላችን መለየትና መገንጠል ወደባችን ጭራሽ ጭንቅላቷ ከተቆረጠው ኢትዮጵያችን መለየት ወዘተ ዘግናኝ የታሪክ ጠባሳዎችን ነው፡፡ በመሰረቱ ያኔ ወያኔ ራሱን የትግራይ ሪፐብሊክን መስርቶ ሊገነጠል ያልቻለበት ምክያት የያዘውን ጦር ለማስተዳደር እጅግ ስለከበደውና የሁሉም ብሄሮች ተዋፅኦ ሳይፈልግ ለድል ሲል ብቻ ከሰበሰበው ሃይል በመኖሩ ነው፡፡ ደርግ እያየለና እጅግ ዘመናዊ ጦር መሳሪያ እያስገባ ምንም እንኳን በሁሉም የሃገሪቱ አቅጣጫ የተወጠረ ቢሆንም ወያኜ ግን ሊቋቋመው የማይችለው ሆኖ ስላልተሰማው ከሁሉም ብሄሮች የተውጣጣ ማለትም /ከምርኮኞች፣ ከተቀናቃኞች፣ ከኢህአፓም፣ ከኦነግ፣ ከኢህዴን ወዘተ…/ አዲስ ጦር ሰብስቦ ነው ትግሉን የቀጠለው፡፡ ከዚያም በቀላሉ አንድ የሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ከትግሉ ላይም ተቀላቅሎ በመቻቻል አንድነቱን በማሳየት ሻብያን ለመገንጠል ስለመሆኑ እውቅና በመስጠት እንደ ድርጅት አንድ ላይ በመሆን ደርግን ወጉ ታዲያ ያኔ ትግራይ ሪፐብሊክን እንዳይገነጥል ይህንን ሃይል እንዴት ይበትን የት ይልቀቀው? ቢለቀው ከትግራይ ውጡ ቢል እዛው ሚጨርሱት ሆነና አንዲያው ተቀብሎ ተግሉን በማስቀጠል ደርግን ለውድቀት ዳረጉት፡፡/ሌሎች ምክንያቶችም አሉት/ ወያኔ ኢህአዴግ አሁን የያዘው ስትራቴጅ ደግሞ የማይመጣው ማጥ ውስጥ ስለከተተው የሚከተለው እንደ ትግሉ በግልፅ ራሱን በመገንጠል አላማ ማለትም የመሄድ ዓላማ ሳይሆን ተቃራኒውን ነው፡፡ ይህም ማለት አሁን በምኑም በምኑም ምንያት የከፋፈለውን ህዝብ የበለጠ በመከፋፈልና የመለያያ ታሪኮችን እንደመልካም አስተማሪ ታሪክ በመምዘዝ እና አደባባይ በማውጣት /ሆኑ አልሆኑ የሚለው ባይታወቅም ምንጭ ባይኖረውም/ አንዱን ከአንዱ በማፋጀት እራሱ መሄዱን ሳይጀምር ሌሎች በየአቅጣጫው እንዲሄዱ በማድረግ የተዳከመች ኢትዮጵያ የተፈረካከሰች ኢትዮጵያ ስትቀር…በሉ እኔም የድርሻየን እናንተ ከሄዳችሁማ…ብሎ ለመነሳት ነው ያሰበ፡፡ ይህ አላማውን ለማሳካት ሲያጠናና ሲያንሰላስል ደግሞ የዚህ አላማ አቅጣጫ ወደ ኦሮሞው ህዝብና የትኛውም አይነት ክፍተቶቹ እንዲሁም የሙስሊሙ ህብረተሰብና ክፍተቶቹ እንዲሁም በራሱ የራሱን ቂላዊ አስተሳሰብና እሳቤ በጫነባቸው ብሄረሰቦችና ብሄሮች በማዞር ነው፡፡ አሁን ኢተዮጵያ ውስጥ በየላይብራሪው ሚገኙ የታሪክ መፅሃፍት በብዛት አንዳችን ከአንዳችን የሚያባሉ አንዳችን ከአንዳችን የሚለያዩ በብዛት ከ99 ፐርሰንት በላይ ደግሞ በዚህ ደደብ ከፋፋይና ገንጣይ አስገንጣይ ስርዓት ዘምን የተፃፉ እና በትግራይ ፀሃፍት እና ተበደልኩ በሚሉ የተከበረው የኦሮሞ ህዝብ ቁንፅል አስተሳሰብ ያላቸው የወያኔ መጠቀሚያ እንደሆኑ እንኳን ማወቅና መለየት ባልቻሉ አካላት የተፃፉ ናቸው፡፡ በመሆኑም ራሱ በሚቆጣጠረውና ቤሰኮንዱ ሳንሱር በሚያደርገው የግሉ ፕሬስ ቀን ከሌት እየተቆጣጠረ እና የኢትዮጵያን አንድነት ሚሰብኩ ብሄራዊ ክብራችን በየስርዓቱ የየስርዓቱን ያለፉትን መልካምና በጎ ያልሆኑ እውነተኛ ታሪኮች የሚያሳዩ መፅሃፍት እንዳይታተሙ በማድረግና ዱሮ የተፃፉትንና በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እና ዳር ድንበር ወሰን ላይ የተፃፉ መፅሃፍትን ታሪካዊ እና አለማቀፋዊ ይዘት ያላቸውን መፅሃፍት በማቃጠል ድራሻቸው እንዲጠፋ ከማድረግ ብሶም ባለፈው የአዲስ አበባው የታሪክ ትምህርት ክፍል ከናካቴው እንዲጠፋ እየተደረገ መሆኑን ሰምተናል፡፡ ዞሮ ዞሮ መዝጊያው ጭራሮ እንደሚባለው ምንም ቢዞሩ ቢዞሩ የተሳካላቸው የማይመስሉ ኢህአዴግና ሴረኞቹ አሁን ደግሞ አማራውን ከኦሮሞው አፋሩን ከሶማሌው ቀበሌን ከቀበሌ ዞንን ከዞን ወረዳን ከወረዳ ቋንቋን ከቋንቋ ሃይማኖትን ከሃይማኖት እምነትን ከእምነት ፓርቲን ከፓርቲ በማንኛውም ልዩነት አድርገው በወሰዱት መለያያ ሁሉ ለማፋጀት ቆርጠው ተነስተዋል፡፡ ለዚህም በትንሹም ቢሆን የተሳካላቸው ይመስላሉ ዘላቂ አደለም እንጅ፡፡ ለዚህ ማሳያም አማራው ከቀየው እየተፈናቀለ ብት ንብረቱ በየሜዳው እየተቃጠለ እየተዘረፈ እየተገደለ፤ አንዱ ብሄር ከሌላው ብሄር በእሳትና ሃሩር እየነደደ ንዌቁን ከወንድም እና እህቱ እያባላ…አማራውን ክትግራዩ…ትግራዩን ከአፋሩ ሙስሊሙን ከክርስትያኑ እያባላ ይገኛል፡፡ አንድ እውነት ግን ልንገራችሁ ይህች ሃገር ልትበታተን እደማትችል ይሕ ስርዓት አለማወቁ ተፈጥሯዊ ማወቅ ምክንያትና ሚስጥራዊ አፈጣጠር አለማወቅ እንኳን አለመሌቱ የስርዓቱን መንበሳበስ ያሳያል፡፡ ይህ ህዝብ አንድ ሆኗል በራሳቸው ሴራ ምክንያት ትንሽም የሚያስቸግሩ ይህ እውነታና ሚስጥር ያልገባቸው አንዳንድ የወያኔ ኢህአዴግ መጠቀሚያ መሆናቸውን ያላወቁ በስሜት የሚነዱ ኢትዮጵያዊያን ብቻ ናቸው፡፡ እነዚህ የወያኔ አባሪ መሆናቸው ያልገባቸው አካላት ሶስት ባህሪያቶች አሏቸው፡፡ 1. ዘረኛና በማንነታቸው ራሳቸውን አጥብበው የሚዘቡ፤ ከራሳቸው ቋንቋ እምነት ተመሳሳይ እና አካባቢ ውጭ ሌላው ምንም እንዳልሆነ ማየት የጀመሩና ወደፊትም የሚያስቡ ናቸው፡፡ 2. በኢትዮጵያ አንድነት ካለማመናቸው ብሶ የመግንጠል ህልምና ሌላውን ቋንቋ ተናጋሪ መበቀል ሚፈልጉ ከአካባቢያቸው እንዳይኖር የሚፈልጉ፤ የሌሎችን ሃብት ንብረት የሚዘርፉ፤ የቋንቋቸውን ልዩነት ብቻ በማየት የእነርሱን ቋንቋ ለሚናገሩት የእነርሱን እምነት ለሚከተሉት ብቻ አድልኦ ሚያደርጉ ናቸው፤ ጎጠኞች ናቸው፡፡ 3. ስለአንድነት ስለብሄራዊ እርቅ ስለልዩነት ውበትነት ከመናቆሪያነት ይልቅ ስለብሄራዊ ጥቅሙ የሚያወሩ የሚሰብኩ ሳይሆኑ ስለመለያየት አንዱን በማንኳሰስ ሌላውን በማሞገስ ይኖራሉ፤ አንዱን የበላይ አንዱን የበታች በማድረግ ራሳቸውን ይቆልላሉ፡፡ መደባዊ ስርዓትን ይከተላሉ ይደግፋሉ፡፡ ተገንጣይና አስገንጣይ አስተሳሰብ የተፀናዎታቸው ናቸው፡፡ አንድ ኢትዮጵያን ሳይሆን ኢትዮጵያ ማለት የአንድ ብሄር ብቻ እንደሆነች አድርገው ሚያስቡ ናቸው፡፡ ለማንኛውም ራሳችሁን ከነዚህ ምድቦች ውስጥ ያላችሁ ሁሉ ቆም ብላችሁ ማሰብ አለባችሁ፡፡ ይህ ተግባራችሁም ከተንኮለኛና ሴረኛው ኢህአዴግ ጋር የሚያስፈርጃችሁ ነው ሚሆነው ይህ ማለት ደግሞ ሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላት ናችሁ፡፡ አሁን አማራ ክልል ውስጥ በመቶ ሽህዎች ሚገመቱ ትግሬዎች ኦሮሞዎች ሶማሌዎች ደቡቦች አፋሮች እንዲሁም ሌሎች ይኖራሉ በአተቃላይ ቢያንስ ከሁለት ሚሊዮን በላይ አማራ ያልሆኑ ብሄር አባላት ይኖራሉ በሰላም ወጥተው በሰላም ይገባሉ፡፡ ዛሬ ኦሮሚያ ክልል ውስጥ በርካታ ሚሊዮን አማሮች በርካታ መቶ ሽህ ትግሬዎች ሶማሌዎች አፋሮች ደቡቦች ጉሙዞች ጋምቤላዎች ይኖራሉ ግን የነፃነታቸው ጉዳይ አጠያያቂ ነው፡፡ ኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሚኖሩ አማሮች ችግር ውስጥ ላይ ናቸው ኢህአዴግ ወደስልጣን ከገባ ጀምሮ ይገደላሉ ይታሰራሉ ንብረታቸው ይዘረፋል ይቃጠላል…ወዘተ ይህ ደግሞ የኦሮሚያ ህዝብ ለኢህአዴግ ሴራ ተገዥና ተጠቂ መሆኑ ነው፡፡ ነገር ግን የኦሮሚያ ህዝብ ኢህአዴግን ለመደገፍ ፈልጎ እንዳልሆነ ግልፅ ጉዳይ ነው ሆኖም ግን አንድ የሰፊው ህዝብ ስንት በርካታ ምሁራንን ያፈራው የኦሮሚያ ህዝብ ያላወቀው እና ለፀረ-ኢትዮጵያዊያን ተዘዋዋሪ አጋዥ ሆኗል፡፡ ለምሳሌ፡- የአኖሌ ሃውልት ታሪኩ እውነት ሆነም አልሆነም ለወደፊቷ ብሄራዊ አንድነቷ ለተከበረችው ኢትዮጵያ ምንድን ነው ፋይዳው አዲስ ህፃን ሲወለድ …ይህ ሃውልት በሚኒሊክ ዘመነ መንገስት ጊዜ እናቶቻችን ጡቶቻቸው እየተቆረጡ የተጣለበትን…ገዜ ይህ እጅ ደግሞ ተቆረጠውን የሚኒሊካዊያን እጅ ነው የሚያስታውሰን ለማለት ነው¡?... ሃሃሃሃ…ይሄ ቀልድ መሆን አለበት ቀልድ መሆን አለበት!!!! ታዲያ …አባየ ታድያ ምንድን ነው ለእኛ ትውልድ የሚጠቅመን? ያበላናል ሲጠማን ያጠጣናል? ሲያርዘን ያለብሰናል?...ምንድን ነው ከዚህ የምማረውና የኔ የምለው መልዕክት?... ብሎ ልጁ ቢጠይቅ አባባው ምን መልስ አለው፡፡ ታዲያ የማይጠቅም አንድም በጎ ራዕይ ያልሆነ የመከራና ሃዝን ጊዜን የሚያስታውስ ታሪክ ለምን እናኖራለን፡፡ ያውም እኮ ምንም ማስረጃ ለሌለው ነገር ለዚህም ራሳቸው ዶ/ር ነጋሶ ኪዳዳ "…የአኖሌ ታሪክ ስለመፈፀሙ የሚናገር አንድም ማስረጃ የለም!! " ሲሉ ተሰምተዋል፡፡ እንዲያው እስቲ ለሃገር አንድነት ለሃገር ህልውና ብሄራዊ ጥንካሬና ስሟ የገነነ ለመብቱ ጠያቂ ማህበረሰብ መፍጠር የሚፈልግ ትክክለኛና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ቢሆንማ ኢህአዴግ ለምኔ ብሎ በገነባው ነበር ይህንን ዲንጋይ ሃውልት ያውም 20 ሚሊዮንን ያህል ገንዘብ አፍስሶ፡፡ ሞኝ!! ሞኝ ነው መንግስተ ነኝ ባዩ ወንበዴ ማፊያ ቡድን፡፡ እኛም አውቀናል…ጉድጓድ ምሰናል አለች አይጥ ይህንን ሴራውን ሞኞች ለአጭር ጊዜ ቢሸወዱም እንኳን 80 90 ፐርሰንቱ የኦሮሞ ህዝብ ሴራቸውን እንዳወቀባቸውና የሴራቸው ማዳፈኛ ጉድጓድም እንደማሰባቸው ባወቁ ነበር ደደቦች፡፡ መብሸቅ ነው ወገኖቼ…አስቲ ለማንኛውም የጀመርኩትን ልጨርስ የዛሬን ብቻ ታገሱኝ… ኢህአዴግ እውነት የኢትፕያን አንድነት ቢፈልግማ አንድ ህዝብ ያልተከፋፈለ ያልተለያየ ህዝብ ቢፈልግማ አኖሌን ከሚያሰራ ያኔ የወሎ ህዝብ ሲራብ የኦሮሞ ህዝብ ማስተናገዱን የደቡብ ህዝብ ማስተናገዱን የጎንደር ህዝብ ማስተናገዱን፤ ያኔ የነብዩ ሙሃመድ ተከታዮች ወደ ሰላሚቱ ምድር ወደ ክርስቲያኗ ምድር ኢትዮጵያ ሂዱ እዛም ሰላማችሁን ታገኛላችሁ ብሎ የላካቸውን ሙስሊም ወንድምና እህቶቻችን ስንቀበላቸው የሚያሳይ ሃውልት፤ ያኔ የትግራይ ህዝብ በተለይ ወያኔያዊያን ሲታገሉ ብቻቸውን ሳይሆን ከሌሎች ወንድሞቻቸው ጋር በመሆን በወቅቱ አምባገነን የሚሉትን ስርዓት ለመጣል ያደረጉትን ትብብርና ያለትብበራቸው መውደቁ ዘበት ሊሆን የሚችልበትን እውነት የሚያሳይ ሃውልት ለምን አያስገነባም፡፡ ለምን ታዲያ የአጼ ዮሃንስን የራስ ቅል ከደርቡሾች ተቀብሎም ሆነ ቀምቶ አምጥቶ ሃገራችን ውስጥ በክብር አላስቀመጠም ለምን ደርቡሾች ሱዳኖች አጼ ዮሃንስን አንገቱን ሲቆርጡ የሚያሳይ ሃውልት አልሰራም፡፡ ለምን ሃገር ውስጥ እንኳን የአማራው ህዝብ ለኢትዮጵያ ህልውና ሲል ሌሎች ወንድሞቹና እህቶቹ ጋር በመሆና በመተባበር በአንድነት የጠላትን ክንድ ሲሰባብር የሚያሳይ ከሃዲዎችም ሲክዱ የሚያሳይ ሃውልት አልሰራም፡፡ ለምን በቅኝ ግዛት ሙከራ ወቅት የኢትዮጵያኝ ንብረትና ጥሬ ሃብት ጣሊያን ስትመዘብር የሚያሳይ ሃውልት አልሰራም፡፡ ለምን መልካም ያለፉ መንግስታትን ተግባራት የሚያሳዩ ሃውልቶችን አልሰራም…?!!!! ኧረ ስንቱ ወገን….!!! እህህህህህ ነው ብቻ እህህህ… ለማንኛውም እስቲ የዛሬውን እዚህ ይብቃኝና የዕለቱ መልዕክቴን አንካችሁ… ኢትዮጵያ ውስጥ ኦሮሞ የሌለበት ቦታ አለ? ሶማሌ የሌለበት አለ? ትግሬ የሌለበት አለ? አፋር ጉሙዝ ጋምቤላ ደቡብ የትኛውም ቋንቋ ተናጋሪ እምነት ተከታይ ሃይማኖት ተከታይ የሌለበት የኢትዮጵያ ግዛት አለ? እስቲ አማራ የሌለበት ክልል ካለ ይጠቀስ ኦሮሞ ሆኖ አማራ ክልል ውስጥ ሃብታም ሆኖ ለበርካታ አማራዎች ትግሬዎች ደቡቦች ሶማሌዎች ወዘተ የስራ ዕድል የፈጠረ የለም እንዴ? አማራ ሆኖ ለበርካታ አማራዎች ኦሮሞዎች ትግሬዎች ሶማሌዎች አፋሮች ወዘተ…የስራ ዕድል የፈጠረ የለም? እስቲ እውነቱን እናውራ ኦሮምኛ ብቻ የሚናገሩ እናታቸው አማራ ወይ አባታቸው አማራ እናታቸው ወይም ደግሞ አባታቸው አሮሞ ግማሽ ሌላ ግማሽ ሌላ ሆኑ አማራ ውስጥ ትግራይ ውስጥ ኦሮሚያ ውስይ የሉም፡፡ ቆይ እስቲ ኦሮሚያዎች ትግራይ ውስጥ የሉም እንዴ…ደቡቦች አማራ ውስጥ የሉም እንዴ…የሞቀ ኑሮ እየመሩ አደለም እንዴ ያሉት? ታዲያ አንዱን ከአንዱ በምን ነው ሊለያዩን የሚፈልጉት?!!!!!... ጉድ እኮ ነው!! አማራውን ሄዳችሁ ክልልህ ውስጥ ያሉ ኦሮሞዎችን ደብድብ ብትሉት ምንም ቢሆን እንደእኔ ኢትዮጵያዊ ናቸው ማን ነው በላቸው የሚል ብሎ አፈሙዙን ወደ መንግስት ነው የሚያዞር…አማራ ክልል ውስጥ በብዙ መቶ ሽህ የሚገኙትንት ትግሬዎች ደብድብ ቢባል ወይ ፍንክች ወንድምና እህቶቼ ናቸው ነው የሚል አማራው ትግሬዎችም እንደዛው… ይህ ነው ብልጠት ይህ ነው ኢትዮጵያዊነት!!! ይህ ነው አንድነቷ የጠጠበቀች ኢትዮጵያን መሻት ማለት፡፡ ለምን አማራ ስለሆነ አማርኛ ተናጋሪ ስለሆነ ብቻ አማራው ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ይገደል እሽ ምላሽ ምን ይሁን…? አማራውም እንዲበቀል ትግራዩም እንዲበቀል ሶማሌውም እንዲበቀል ነው ኢህአዴጎች የሚፈልጉት….ይህንን ነው እነርሱ የሚፈልጉት፡፡ ለዚህ ምላሹ ግን ብቀላ አደልም በፍቅር ማሸነፍ ነው አሁን ትኩረታችን ነፃነታችን ከነሳን መንግስት ሳናደርገው ካስገደደን ኢህአዴግ ገንጣይና አስገንጣዩ ጋር ነው፡፡ አንድ ላይ መዝመት ያለብን እዚህ ስርዓት ጋር ነው፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ሁሉም ለአማራ ወይም ለትግሬው ጥላቻ አለው ወይም ለደቡቡ ጥላቻ አለው ማለት አይቻልም፡፡ የሚጠላ ካለም ጉዳቱ ለራሱ ነው፡፡ ለራሱ ቀረበት፡፡ አንድ ብንሆን ለራሳችን ነው ለኢትዮጵያማ ምን ይበጃት ኢትዮጵያማ መሬት ናት መሬት!!! ይህንን ጥላቻ እያስፋፉ አማራውን ከኦሮሞው ትግሬውን ከአፋርና ኦሮሞው አፋን ከሶማሌው የሚያናክሱት ኢህአዴጋዊያን ስውር ተንቀሳቃሾችና ሴረኛ ዘረኞች ደደቦች ናቸው፡፡ ስለዚህ የየትኛውም ብሄር አባል የሌላኛውን ብሄር አባል ሆነ ሌላ እምነትና ቋንቋ ተከታይና ተናጋሪ ህዝብ የሚጠላ ለጎሪጥ የሚያይ አልፎም ይህንን መሰረት በማድረግ ወደ ትውልድ ቦታህ ሂድ ልቀቀን በማለት የሚደበድብ የሚገድል ሁሉ የወያኔ አሽከር መሆኑን ተገንዝበን ከተግባሩ እንዲቆጠብ ጥሪ እናቀርባለን፡፡ ይህንን ለመፈፀምም በአንድነትና ኢትዮጵያዊ መንፈስ መዋጀት አለብን ራሳችን በዚህ ኢትዮጵያዊነት ብሄራዊ ክብራችን መቃኘትና መንቀሳቀስ አለብን፡፡ ያለዚያ ግን የኢህአዴግ ፈፃሚና አስፈፃሚ በመሆናችሁ ፍርዳችሁን ታገኛላችሁ፡፡ አመሰግናለው ክብር እና ዘላለማዊ ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen