Netsanet: የአዲስ አበባ እና ጊዶሌ ሰልፍ – LIVE UPDATE

Sonntag, 4. Mai 2014

የአዲስ አበባ እና ጊዶሌ ሰልፍ – LIVE UPDATE

ከጠዋቱ  4:50 ሰዓት  / 3:50 PM DC  Time /
ሰልፈኞቹ አሁን አዋሬ አካባቢ ናቸው። ፖሊሲ ከአራት ኪሎ ና ከመገናኛ ሕዝቡ እንዳይቀላቀ ዋና መንገዶችን ዘግቷል። ፍቃደ ሰጥቶ  ህዝቡ ወደ ሰልፉ እንዳይመጣ መንገድ መዝጋት ምን ያህል አገዛዙ ለሕግ ድነታ እንደሌለዉን ሕዝብን የሚንቅ መሆኑን የሚያሳየውልል። እንደዚያም ሆኖ ግን አቋራጭ መንገዶችን እየያዘ፣ ህዝቡ ሰልፉ እየተቀላቀለ ነው።
እስከአሁን ድረስ ሰልፉ ፍጹም ሰላማዊ ነበር።፡ምንም አይነት ችግር እስከአሁን አልተፈጠረም።
ggg3
ከጠዋቱ  4:45 ሰዓት  / 3:45  PM DC  Time /
መፈክሮች ፡
ማዕከላዊ ጓንታናሞ ! ጨለማ ዋጠን ! ውሃ የለም ! ኔትወርክ የለም !
በአበባዩሽ ዜማ ሰልፈኞቹ በአንድነት እየተቀባበሉ እየዘመሩ ይገኛሉ
“ታስሯል ወገኔ ! ታስሯል ወገኔ “ እያሉ ሁለት እጆቻቸውን ሳቀሉ ዜጎች ወገኖቻቸው በእስር ቤት እንደሚገኙ እየመሰከሩ ነው::
gk1gk2


ከጠዋቱ  4:30 ሰዓት  / 3:30  PM DC  Time /
ሰልፈኞቹ አቧሬ አደባባይ ደርሰዋል::  ‹‹ተከብረሽ የኖርሽው የአባቶችችን ደም››የሚለውን ተወዳጅ መዝሙር ተሰላፊዎቹ ሲያዜሙት ማድመጥ ልዩ ስሜትን ይፈጥራል
አደባባዩች የህዝብ ናቸው  !  አንድ ናት አገራችን ! ኦሆሆ ኢትዮጵያችን !
ከጠዋቱ  4:15 ሰዓት  / 3:15  PM DC  Time /
አስደናቂና ሰላማዊ ሰልፍ ነው። ከሚሰሙ መፈክሮች መካከል !
የፈሪ ዱላ ጀግና ማሰር ነው ! ልማት እያሉ ሙስና  ሰሩ !  ድል የህዝብ ነው ! ድምጻችን ይሰማ ! ዛሚ ሌባ ! ተማረዎችን የገደሉና ያቆሰሉ ለፍርድ ይቅረቡ ! ስድስቱ ጦማሪዎችና ጋዜጠኞች ይፈቱ ! መግደል ይቁም ! እየገደሉ ገደሉ አሉ ! ራሱ ገዳይ ራሱ ከሳሽ !
ከጠዋቱ  4:05 ሰዓት  / 3:05  PM DC  Time /
ሰልፉ እጅግ በጣም ደምቋል። አስገራሚ ሰልፍ ነው !በጥይት በዱላ አይገዛም አገር !በጥፊ በርግጫ አይገዛም አገር !ፖሊሲ የሕዝብ ነው !መብትን መጠየቅ ሽብር አይደለም !አትነሳም ወይ አትነሳም ይሄ ባንዲራ ያነታ አይደለም ወይ !ሕገ መንግስቱ ወረቀት ብቻ !
ggg1ggg2
ከጠዋቱ  4;00  ሰዓት  / 3:00  PM DC  Time /
ውሸት ሰለቸን ኢቴቪ ሌባ ህዝቡ በአንድነት ሰልፍ ካስደመጣቸው መፈክሮች ይመደባሉ :
መብትን መጠየቅ ሽብር አይደለም !ውሃ ፣መብራት፣ኔት ወርክ ፣ትራንስፖር ! ፍትህ እያሉ ቃሊቲ ገቡ !ፍራቻው ይቅር ተቀላቀሉ ! ለፍትህ ብለው ቃሊት ገቡ ! በመግደል በማሰር አይገባም አገር !
ggg1
ከጠዋቱ  3፡ 30  ሰዓት  / 2፡30 PM DC  Time /
ተከበረሽ የኖርሽው ባባቶቻችን ደም ፣ እናት ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይዉደም ! እያለ ህዝቡ እየዘመረ ነው።  ሰልፉ ተጀምሯል።  መፈክሩ ደምቋል። እስክድነር፣ ርዮት ፣ አንድዋለም …እያሉ የሕሊና እስረኞቹን እየጠሩ ነው። «አሸባሪ አይደለንም !» እያሉ ነው።
«ኢትዮጵያ ካድሬዎች እንደፈለጉ የሚፈነጩባት አገር አትሂንም»፣ « አንድ ሕዝብ ነን።  በቋን ቋ፣  በባህል፣ በሃይማኖት ሊከፋፍሉን ሞከር። አልተሳካም»   …የመሳሰሉ መፈክሮች እየተሰሙ ነው።
girma3girma2girma1
ከጠዋቱ  3፡ 30  ሰዓት  / 2፡30 PM DC  Time /
ሰልፉ ጉዞ ገና አልተጀመረም። ከመገናኛ እና ከራት ኪሎ ወደ ቀበና የሚመጡ ዋና መንገዶች ፖሊሲ ዘግቶ፣ ህዝቡ አቋራጭ እየፈለገ ነው እየመጣ ያለው። ከተጠበቀዉ በላይ ሕዝብ በአንድነት አካባቢ መጥቷል። ሰልፉ ገና አልተጀመረም ግን ወደ አስልፋልቱ እየተሻገሩ ነው። ከትንሽ ጊዜ  በኋላ ስለፉ ይጀመራል። መፈክሮች እየተሰሙ ነው። የአመራር አባላቱ ንግግር አድርገው ሰልፉ ሰላማዊ እንደሆነ በመግልጽ የሰልፉን ስነ-ስርዓት እያሰረዱ ነው።
udj444

ከጠዋቱ  2፡55  ሰዓት  / 1፡55 PM DC  Time /
አንድነት ጽ/ቤት አካባቢ
udj1
ከጠዋቱ  2:15  ሰዓት  / 1:30 PM DC  Time /
ከቀበና መድኃኒዓለም ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት ከሚገኘው የፓርቲው ቅጥር ግቤ በመነሳት በቤልኤር፣ሲግናል አደባባይ፣አድዋ ድልድይ፣የካ ሚካኤል ወረዳ 8 ታቦት ማደሪያ መዳረሻው ይሆናል፡፡
አቶ አስራት አብርሃ ፣ በቅርቡ የአንድነት ፓርቲ ተቀላቅለዋል። በቃሊ ክፍል ቀርበው ትንሽ ቃለ መጠይቅ አደርገዋል። «ሰልፉ ገና ሳይጀመር ዉጤት አስመዝግቧል» ያሉት አቶ አስራት፣ የሚኖሩበት ሰፈር የሰልክ መስመር ኖሮ እንደማያውቅ የገለጹት አቶ አሥራት ፣ በዚህ ሳምንት ዉስጥ ግን የሰፈር ስልካቸው እንደሰራ ገልጸዋል፡
ሚያዚያ 26 ቀን 2006 ዓ.ም  ከጠዋቱ  2:15  ሰዓት  / May  4  2014 :  1:15 PM DC  Time /
የአንድነት ዋና ጸሃፊ አቶ ስዩም መንገሻ ለቃሌ ፓልቶክ ክፍል ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ ላለፉት ጥቂት ቀናቶች የተደረጉ ቅስቀሳዎች በጣም አስገራሚአን አስደሳች እንደነበሩ ገልጸዉ ብዙ ህዝቡ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
በተያያዘ ዜና የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶችም የአንድነት ሰልፍን እንደሚቀላቀሉ አሳወቁ። የወጣቶች ክፍል ሃላፊ ፣ ወጣት ዮናታን፣ ወጣቶቹ ለምን ወደዚህ ዉሳኔ እንደደረሱ ለረክንታ አፌር ክፍል፣ አብራርቷል። ወጣቶቹ ትላንት ተሰብስበው ባደረጉት ዉይይት ፣ የአንድነት ሰልፍን መቀላቀል አስፈላጊ እንደሆነ፣ አንድነት ያነሳቸውን አጀንዳዎች እንደሚደገፉ ገልጸዋል።
«የእናንት ፓርቲ፣ በፓርቲ ደረጃ በኦፊሴል አባላቱን ደጋፊዎች ለሰልፉ እንዲወጡ ጥሪ ቢያደርግ ኖሮ፣ ለሕዝቡ ትልቅ ትልቅ ትርጉም ያለው መልእክት በሆነ ነበር። ከዚህ አንጻር ፓርቲው በኦፌሴል፣ በግልጽ በጋዜጣዊ መግለጫ፣ ወይም ማስ ሜዲያ  አባልቶቹ  ድጋፍ ሰልፉ እንዲወጡ ጥሪ ያላቀረበበት ምክንይታ ምንድ ነው? » ለሚል ጥያቄ፣  የመለሰው ወጣት ዮናታን፣ 22 አባላትና አራት አመራሮች ታስረው ስለነበረ፣  እነርሱን ለማስፈታት ሲሯሯጡ እንደነበረ የገለጸ ዮናት «ከአሁን በኋላ ግን ፣ ከዚህ በኋላ የሚጠብቀን ፈተና ከባድ በመሆኑ፣  በጋራ ነገሮች ላይ አብሮ ለመስራት አስፈላጊ ነው» ሲል ከሰማያዊዎ አካባቢ ያልተለመደ፣ ግን ማስተዋል የሞላበትና ብዙዎችን ያስደሰተ ንግግር ተናግሯል።
«ሰማያዊ ስለሆንን አንድነት ያነሳውን አጀንዳ አይመለከተንም የለብም። ከድርጅት አጥር ወጥተን የሕዝብ ጥያቄ ማስቀደም ያስፈልጋል» ያለው ወጣት ዮናት፣  ዉሳኔው የወጣቶች እንጂ የሰማያዊ ፓርቲ አመራር እንዳልሆነ ገልጿል።  የድርጅቱን ሊቀመነብር አቶ ይልቃል ኤምባሲ ቀጠሮ ስላለው፣ በሰልፍ ላይገኙ እንደሚችሉም ጠቁሟል።
የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶች፣ የጣይቱ ልጆች.. በአንድነት ሰልፍ መቀላቀላቸው፣ ከአድንነት ጋር ለመተባበር መወሰናቸው የረፈደ ቢሆንም፣ በራሱ ትልቅ ድል ነው። አገዛዙ ለአንዱ እየፈቀደ፣ ለሌላው እየከለከለ በአንድነትና በሰማያዊ መካከል ልዩነት እንዲፈጠር ሲዶልት ነበር። ይህ የሰማያዊ ወጣቶች ዉሳኔ፣ የአገዛዙን ሴራ ያከሸፈ ነው። ከዚህ በኋላ የበለጠ ትብብር፣ የበለጠ አብሮ መስራት እናያለን ብለን እንገምታለን። አቶ ይላቃል እና የፓርቲው አመራር የወጣቶችን የትብብር መነሳሳት ላይ ቀዝቃዛ ዉሃ ወደፊት ባያፈሱበት ይሻላቸዋል።
ሚያዚያ 26 ቀን 2006 ዓ.ም  ከጠዋቱ  1:20  ሰዓት  / May  4  2014 :  12:20 PM DC  Time /
ከጠዋት 1 ሰዓት ነው።  ሰልፉን ከመጀመሩ ከሁለት ሰዓታት በፊት የአንድነት ፓርቲ በሰዎች እየተሞላ ነው። በጠዋቱ ወደ ሰልፉ ከመጡት መካከል ወ/ሮ ያዬሽ እና ወ/ሮ ፍቅርተ ሞገስ ይገኛሉ። ወ/ሮ ፍቅርተ  ሞገስ የአቶ ናትናኤል መኮንን ባላቤት ሲሆኑ፣  ወ/ሮ ያዬሽ ደግሞ የአቶ አንዱዋለም አያሌው። አቶ ናትናኤል መኮንን እና አቶ አንዱዋለም አያሌው በአሁኑ ጊዜ በዝዋይ እስር ቤት የሚገኙ ናቸው።
ከፍተኛ ፖሊስ እና ጥበቃ በአንድነት ጽ/ቤት አካባቢ እየታየ ነው። የአንድነት አመራር አባላትን ወደ ጽ/ቤታቸው እየገቡ ነው።
ሚያዚያ 26 ቀን 2006 ዓ.ም  ከጠዋቱ  11፡30  ሰዓት  / May  3  2014 :  10፡30 PM DC  Time /
ጊዶሌ በተለይም በትላልቅ ከተሞች የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ብዙ አያወቋትም። ጊድሌ በደቡብ ክልል ኦሞ ዞን ዉስጥ፣ በደራሼ ወረዳ የምትገኝ ከተማ ናት። በኣጠቃላይ የደራሼ ወረዳ የጋሞ እና የደራሼ ብሄረሰቦች የሞሉባት አገር ናት።
የደራሼ ሕዝብ ለብሄር ብሄረሰቦች መብት ቆመናል በሚለው ኢሕአዴግ ግፍ ደርሶበታል። የአገዛዙ ባለስልጣናት የግላቸው የሆኑ ፎቅችን በአዲስ አበባ በብዛት ሰርተዋል። የደራሼ ወረዳ ጊዶሌ ከተማ ግን ፒያሳዋ ምን እደሚመስል ተመልከቱ። መንገዶቹ ጠጠር እንኳን አይደለም፣ አቧራ !!!!  ኢሕአዴግ ለገጠሪቷ ኢትዮጵያ ለአርሶ አደሩ የቆምን እኛ ነን፣ ነበር ሲለን የነበረው። ነገር ግን እንሁ ገጠሪቷ ኢትዮጵያ !!!
gidole-300x217
ሚያዚያ 26 ቀን 2006 ዓ.ም  ከጠዋቱ  11  ሰዓት  / May  3  2014 :  10፡00 PM DC  Time /
የእሪታ ቀን ሰልፍ በአዲስ አበባ ሊጀምር አምስት ሰዓት ነው የቀረዉ። በተመሳሳይ ሁኔታ ጊዶሌ እንደዚሁ ሕዝቡ በነቂስ ይወጣል ተብሎ ይገመታል።
ከምርጫ ዘጠና ሰባት በኋላ እንደዚህ አይነት የሰልፍ እንቅስቅሴ ተደርጎ አያውቅም።  በመኪና በእግር ፣ በዋና ዋና ቦታዎች በየጉራንጎሮ፣  በራዲዮ ፣ ህዝቡ ስለ ሰልፉ እንዲያውቅ ተደርጓል። ኢቲቪ ስለሰልፉ እንዲናገር ጥያቄ ቢቀርብለትም፣ የአንድነት ማስታወቂያ (ያዉም ገንዘብ ተከፍሎ ) ለማስተናገድ ፍቃደኛ አልሆነም።
ነገር ግን ኢቲቪ ሳያስበው ፣ በነጻ የአንድነትን ሰልፍ ማስተዋወቁ ነው።፡ዳዊት ሰለሞን ከኢትዮጵያ እንዲህ ሲል ዘግቧል፡
=================
ኢቴቪ ለአንድነት ሰላማዊ ሰልፍ ቀሰቀሰ። የህትመት ዳሰሳ የሚሰኘው ሳምንታዊ የኢቴቪ ፕሮግራም አዘጋጆች አንድነት ለነገ የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ በማስመልከት አጠር ያለ ዳሰሳ በመስራት የሰላማዊ ሰልፉ አላማ አገሪቱ እየተጓዘችበት ከሚገኘው የልማት ጉዞ ተቃራኒ መሆኑን በመጥቀስ የባቡር መንገድ፣ማሳለጫው፣የኤሌክትሪክ አቅርቦት፣ትራንስፖርት፣የኢንተርኔት አገልግሎት መሻሻል ወዘተርፈ የመሳሰሉት እሪ እንበል የሚሉትን ባዶ እጃቸውን ያስቀራቸዋል፡፡ብለዋል፡፡
ኢቴቪ ትናንት የሰልፉን ማስታወቂያ በገንዘብ እንዲለቅ ተጠይቆ የነበረ ቢሆንም በህትመት ዳሰሳው አንድነት ሰላማዊ ሰልፍ ማዘጋጀቱን መናገሩን ብዙዎች ስለሰላማዊ ሰልፉ እንዲሰሙ ምክንያት እንደሆናቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡ኢቴቪን ገልብጦ የሚሰማው የአዲስ አበባ ህዝብም በነጻ የተለቀቀለትን ማስታወቂያ በመስማት ነገ ሰልፉን እንደሚያደምቀው ይጠበቃል፡፡የህትመት ዳሰሳ አዘጋጆቹን አንድነት ማመስገን አይኖርበትም ትላላችሁ።

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen