Netsanet: የዚህ አምባገነን መንግስት አሁንም ብሎገርስና የፌስቡክ ማነቃቃትንና መነቃቃትን እንደ ስጋት እና በቀላሉ መፍትሄ የሚያገኙለት መስሎ ስላልተሰማው አሁንም የተለያዩ ፀሃፊና ጦማሪያንና ፀሃፊዎችን ወደ ማጎሪያቸው ለማስገባት ሳይታክቱ በመድከም ላይ ናቸው

Freitag, 23. Mai 2014

የዚህ አምባገነን መንግስት አሁንም ብሎገርስና የፌስቡክ ማነቃቃትንና መነቃቃትን እንደ ስጋት እና በቀላሉ መፍትሄ የሚያገኙለት መስሎ ስላልተሰማው አሁንም የተለያዩ ፀሃፊና ጦማሪያንና ፀሃፊዎችን ወደ ማጎሪያቸው ለማስገባት ሳይታክቱ በመድከም ላይ ናቸው

የዚህ አምባገነን መንግስት አሁንም ብሎገርስና የፌስቡክ ማነቃቃትንና መነቃቃትን እንደ ስጋት እና በቀላሉ መፍትሄ የሚያገኙለት መስሎ ስላልተሰማው አሁንም የተለያዩ ፀሃፊና ጦማሪያንና ፀሃፊዎችን ወደ ማጎሪያቸው ለማስገባት ሳይታክቱ በመድከም ላይ ናቸው/አሁን ምናለበት ለመልካም ተግባር ለመልካም ስራ ይህንን ድካማቸውን ቢያውሉት/…እናም ትላንት በ13/09/2006 ከምሽቱ 12፡00 ላይ እኔ ወደ ስራ ሄጄ የማስተምረውን ክላስ ጨርሼ ስመለስ መኖሪያ ቤቴ ዙሪያ ወደ አምስት የሚደርሱ ሲቪል ለባሾችና አንድ ፓትሮል የፌደራል ፖሊስ ሙሉ ትጥቅ አድርገው እኔን የፌስቡክ አሸባሪውን ለመያዝ ላይ ታች ሲሉ ያየ ጓደኛየ ደውሎልኝ እኔም አካባቢየን ለቅቄ ራቅ ወዳለ ስፍራ ምናልባትም ላለመመለስ ሄጃለው፡፡


በምንም መንገድ ግን እጄን ለፖሊስ መስጠት እንደማልፈልግ ላረጋግጥላችሁ እወዳለው፡፡ ጉዳዩ ለበርካታ ምሁራንና ፀሃፍት የሚያሰጋና በጅብ መንጋጋ ያለ ሙዳ ስጋ ያክል እንደሆኑ አውቀውት ራሳቸውን በጥንቃቄ ማታገልና መታገል እንዳለባቸው ላሳውቃቸው እወዳለው፡፡ እኔ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በአንዱ ውስጥ የማስተምር ሲሆን የማስተምረውን የኢኮኖሚክስ ትምህርት የምወደውን ሞያየን ሳይሆን ቅድሚያ መስጠት የምፈልገው ነፃነቴን ነው፡፡


ነፃነቱን ያገኘ ማህበረሰብ መፍጠር ነው የመጀመሪያው አላማየ ስለዚህ ሌሎች ፀሃፊያንና ጦማሪያን ትግላችሁ ለሰኮንድም መቋረጥ እንደሌለበት እያስገነዘብኩኝ ሁላችንም ታስረን ሞተን እስክናልቅ /ምናልባት ከጨረሱን/ አቢዮት ልቿን ትበላለች የሚለውን ነፃነትና ለውጥ ፍለጋ ልጆቿን ትበላለች ነውና ተበልተን እስክናልቅ /ምናልባት ካለቅን/ ትግላችን ያለምንም ፍራቻ መቀጠል አለበት፡፡


አፈላልገው ሊያገኙኝ ይችላሉ ሆኖም እስከዛች ቅፅበት ድረስ መፃፌን አላቆምም፡፡ ነፃነቴን በፍርሃት ክምር አላጠፋውም፡፡ ሲጀመር ፈርቼም አላውቅም ጥንቃቄ ግን ሁልጊዜም አደርጋለው፡፡


ጦማያን እና ፀሃፊያን ይህንን ሸር በማድረግ ላልሰሙት እናሰማ፡፡ በመሆኑም https://www.facebook.com/pages/Ethiopian-Politics/623214127716880 ይህንን የፌስቡክ ገፅ ስፅፍ የሚመጣውን ሁሉ አደጋ ለመቀበል በመሆኑ ዝግጁ መሆኔን ላሳውቃችሁ እወዳለው ሆነም ቀረም ምናልባት ከተሳካላቸው ይህንን ፔጅ ታስቀጥሉት ዘንድ በቅርቡ ለአንድ የማምነው ትግሉን ሊያስቀጥል ይችላል ለምለው ምርጥ ጓደኛየ ፓስወርዱን የማስረክብ ይመስለኛል፡፡ ካልነኩኝም ገና መረጃና ሚስጥራቸውን በማውጣት አፈዳያቸዋለው፡፡ ለዚህ ምስኪን የተገፋ ህዝብ ስል የመጣውን ሁሉ ለመቀበል ዝግጁ ነኝ፡፡


እስቲ ዘጠኙን ጦማሪያንና ጋዜጠኞች ምንግስት ከያዘ በኋላ ያለውን የጦማሪያን መበራከት አስቡት እጅግ በሚገርም ሁኔታ ምንም ስለፖለቲካ ሁናቴ ያስባሉ የማልላቸው የራሱ የመንግስት ነኝ ባዩ አካል አባላትና ካድሬዎችም ሳይቀሩ በቅርብ የማውቃቸው ማለቴ ነው ተያይዘውታል ባለ በሌለ አቅማቸው፡፡ ይህም እኔን ቢያስር የሚረከቡኝ በርካቶች መኖራቸው ያኮራኛል፡፡

ኢህአዴግ ወያኔ አሁን መግቢያው እንደጠፋው አሳማ እያጣጣረ እንዳበደ ውሻ ያገኘውን እየተናከሰ ነው፡፡ ይህ የመውደቂያው ቀን ስለመድረሱ የመጀመሪያ ደረጃ ምልክት ነው፡፡ የራሱ ካድሬዎችም አፍ አውጥተው የኢህአዴግን ሴራ በማውጣት ላይ ናቸው፡፡ አሁን የቀረው ጉዳይ ቢኖር የተቃዋሚው ጎራ አንድ ሆኖ ለወደፊት ስጋት የሚሆኑ ጉዳዮችን መቀናነስና ወደ አንድ መስመር መምጣት አለመቻል ነው ይህንን ለማሳካትም የጦማሪያንና የፀሃፍት ትግል እና ልፊያ ወሳኝ ነው፡፡


አሁን የመጨረሻ አማራጩ የነበረውን ዘርን ከዘር ማፋጀት ሴራው ስለተነቃበትና በትንሹም ቢሆን ለዚህ ሴራው መጠቀሚያ ሆኖ የነበረው የኦሮሞ አንዳንድ አካባቢ ህዝብ ፊቱን አዙሮ ጦሩን ሰብቆ የመንግስት ነኝ ባዩ ማፊያ ቡድን አለቅላቂና አድሃሪዎች ላይ ማዞሩ እንዲሁም ኢህአዴግ እንዳሰበው ተባሉ ብሎ ፈንጅ የጠመደባቸው አካላትም አንድ ላይ ሆነው ኢህአዴግን ማጥፋት መፍትሄ ነው ብለው መጀመራቸው በተለይ ለዚህ ደግሞ የአማራው ህዝብና የኦሮሞው ህዝብ ወደ ቀናው እና ትዕግስትን ወደተላበሰው ፍቅር መስመር ያለምንም ቅድመ ሁናቴ ስዕተታቸውን አርመው መምጣታቸውን ይህንን ማፊያ ቡድን ከአሁኑ እየናደው እንዳለ በርካታ ማሳያዎች አሉ፡፡

አሁን መንግስት እንደዱሮው እንዲህ ልሰራ ነው እንዲህ ላደርግላችሁ ነው እና በሰልፍ ወጥታችሁ ደግፉኝ ገለመሌ ብሎ የህዝብን አቴንሽን የሚያጥፍበት ዳይቨርት የሚያደርግበት ምንም አዲስ ነገር የለውም ዱሮም የደርግና የኃ/ስላሴ ምንግስታት ያቀዳቸውን ስራዎች ነበር ሲተገብር የቆየውና አሁን እነዛ ሲያልቁበት ሊሆን ባይችልም ከዚህ በላይ ማድረግ ስለማይችል እኛ መግፋት አቅቶን እንጅ ሁሉም ባለስልጣናቱ ቆመው እየለመኑን ነው፡፡ ግፉና ጣሉን እያሉን ነው፡፡ አንድነት ያስፈልገናል፡፡


የኢህአዴግን ውድቀት የምናራዝምለት እኛ ነን ስዎች፡፡ ልክ እፊታችን ላይ ራስ ዳሸንን የሚያህል ዳቦ ተቆልሎ ኑ ብሎ እየተባልን እርስ በራሳችን በመመቀኛኘት ባለመፈቃቀር ቀደ ዳቦው ተደጋግፈን ባለመሄድ ዳቦን ላንበላው እዛው ስንላፋ እንዲበላሽ እንደማድረግ ነው አንድነት ማጣታችን ያመጣብን ነፃነት ማጣት በመሆኑም አንድነት ማጣታችን የነፃነት ማጣታችን የምንፈልገውን ስርዓት መምረጥ አለመቻላችን ማክተም አለበት፡፡


ለማንኛውም በቅርብ ማንነቴን የሚገልፅ ፎቶ የምለጥፍ መሆኔን ስገልፅ በደስታ ነው፡፡ ሳልለጥፍ ከቀደሙኝ ግን እኔን የምታውቁኝ አላችሁና ፎቶየን በማውጣት እና ትግሉን በጧጧፍ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጎን ትሰለፉ ዘንድ በነፃነት ናፋቂ ኢትዮጵያዊያን ህዝብ ስም እጠይቃለው፡፡ በአጠቃላይ አሁን ኢህአዴግን የሚቃወም ብቻ የኢትዮጵያን አንድነት አብሮነታችን አንዲሁም ለውጥን የሚናፍቅ ነው ተብሎ ተወስዷል፡፡ አሁን ኢህአዴግን መደገፍ የፋራ ነው!!! ሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃ…


በደማችንም ቢሆን በአጥንታችንም በሞታችንም በእስርና ግርፋታችንም ቢሆን የህዝባችን ነፃነት ያለምንም ማዳላትና ያለምንም ልዩነት ነፃነቱን እናጎናፅፈዋለን ከሌሎች የውጭና የውስጥ የትኛውም ታጋይ ጋር በመሆን!!!
ድል ለሰፊው ነፃነት ናፋቂ!!!
አብቢን ነኝ!!!

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen