Netsanet: በኮልፌ ቤቱ የፈረሰበት አባወራ በጅብ ሲበላ አንዲት ወላድ በድንጋጤ ህይወቷ አለፈ

Freitag, 23. Mai 2014

በኮልፌ ቤቱ የፈረሰበት አባወራ በጅብ ሲበላ አንዲት ወላድ በድንጋጤ ህይወቷ አለፈ

May 23/2014
----------------------------------------------------------
‹‹ቪዛ ይሰጠንና ወደ ሱማሌያ ቢሆንም እንሂድ›› ቤታቸው የፈረሰባቸው
---------------------
ዳዊት ሰለሞን 
በኮልፌ ቀራኒዮ አለም ባንክ አካባቢ ህገ ወጥ የመሬት ወረራ በማድረግ ቤቶችን ሰርታችኋል የተባሉ ዜጎች ቤቶቻቸው በላያቸው ላይ በሀይል ፈርሶ ንብረታቸው መወረሱን አመለከቱ፡፡ ከ15.000 የሚልቁ ነዋሪዎች በሚገኙበት አለም ባንክ አካባቢ ሰዎቹ አነስተኛ መጠለያ ያረፉባቸውን ቤቶች ከገበሬዎች ላይ በመግዛት መኖር ከጀመሩ አመታት መቆጠሩን ያስረዳሉ፡፡ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት ልከውና ወደ ስራ በተሰማሩበት ቅጽበት ከጸጥታ ሰራተኞች ጋር አካባቢውን የወረሩት አፍራሽ ግብረ ሃይሎች መኖሪያ ቤቶቹን ማፍረሳቸውን በሀዘን ተውጠው ገልጸዋል፡፡ ቤቶቹ በድንገት መፍረሳቸውን በመቃወም ድምጻቸውን ያሰሙ የአካባቢው ነዋሪዎች በፖሊሶች ክፉኛ መደብደባቸውንና መወሰዳቸውን የአይን እማኞች አስረድተዋል፡፡ቤቷ ሲፈርስ የደነገጠች እመጫት ወዲያኑ ህይወቷ ሲያልፍ ቤቱ በመፍረሱ መሄጃ ያጣ አባወራ ላስቲክ ዘርግቶ በተኛበት ጅብ ጎትቶት ወስዶት በልቶታል፡፡በጅብ የተበላው አባወራ ስርዓተ ቀብርም ዛሬ መፈጸሙ ታውቋል፡፡ ቤታቸው ፈርሶ ለጎዳና እንደተዳረጉ የሚናገሩ ሰዎች‹‹ኢትዮጵያዊነታችን ተሰርዟል፣ቪዛ ይሰጠንና ሌላው ቢቀር ወደ ሶማሊያ እንድንሄድ ይደረግ ›› ብለዋል፡፡

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen