Netsanet: ከወያኔ መከላከያ ሠራዊት በመኮብለል የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርን የሚቀላቀሉ አባላት አሁንም እንደቀጠለ ነው። ሰሞኑን ግንባሩን ከተቀላቀሉ የሠራዊቱ አባላት መካከል የአየር ኃይል ባልደረባ ይገኝበታል።

Mittwoch, 1. Oktober 2014

ከወያኔ መከላከያ ሠራዊት በመኮብለል የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርን የሚቀላቀሉ አባላት አሁንም እንደቀጠለ ነው። ሰሞኑን ግንባሩን ከተቀላቀሉ የሠራዊቱ አባላት መካከል የአየር ኃይል ባልደረባ ይገኝበታል።


ከወያኔ መከላከያ ሠራዊት በመኮብለል የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርን የሚቀላቀሉ አባላት አሁንም እንደቀጠለ ነው። ሰሞኑን ግንባሩን ከተቀላቀሉ የሠራዊቱ አባላት መካከል የአየር ኃይል ባልደረባ ይገኝበታል።
በወያኔ መከላከያ ሰራዊት ውስጥ ያለውን የአንድ ቡድን የበላይነትን እና ሠራዊቱ የሀገርና ሕዝብ አገልጋይ መሆኑ ቀርቶ የወያኔ ቅጥረኛነትን በመቃወም በተለያዩ የሠራዊቱ ክፍል ሲሰሩ የነበሩ ግለሰቦች የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርን በተለያዩ ጊዜያት መቀላቀላቸው ይታወሳል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሰሞኑን የደብረዘይት አየር ኃይል ባልደረባ ምክትል መቶ አለቃ ጣይብ ቃዲ የተባለ የተዋጊ ጦር ሄሊኮፕተር አብራሪ የሀገራችን ኢትዮጵያን የግፍና የመከራ ጊዜን ለማብቃት እየተደረገ ያለውን ትግል ለመደገፍ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርን ተቀላቅሏል።ምክትል መቶ አለቃ ጣይብ ቃዲ ለአርበኞች ድምጽ ሬዲዮ እንደገለጸው ከሆነ "የአየር ኃይሉ ቁልፍ ቁልፍ ቦታዎች በሕ.ወ.ሓ.ት ሰዎች የተያዘ ሲሆን እንኳንስ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ሊያስከብር ቀርቶ እንደተቋም በሁለት እግሩ መቆም ተስኖት በውጪ ቅጥረኞች ትከሻ ላይ የተመሰረተ" መሆኑን ገልጿል።

የወያኔን አምባገነናዊ አገዛዝን በትጥቅ ትግል ለመፋለም በተለያዩ ጊዜያት የወያኔ አየር ኃይል አባላት የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርን የተቀላቀሉ ሲሆን ከወራት በፊት ምክትል መቶ አለቃ ዳንኤል የሺዋስ የተባለ የተዋጊ ጦር ጀት አብራሪ ግንባሩን መቀላቀሉ የሚታወስ ነው።

ሰሞኑን ግንባሩን ስለተቀላቀለው የአየር ኃይል ባልደረባ ምክትል መቶ አለቃ ጣይብ ቃዲ ሰፊ ዘገባ ይዘን እንደምንመለስ ከወዲሁ እናስታውቃለን።
http://www.arbegnochginbar.org/index.php?option=com_content&view=article&id=799:2014-09-25-16-31-41&catid=41:news&Itemid=50

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen