Netsanet: ሰበር ዜና- አሜሪካ ”በዋሽግተን ኢትዮጵያ ኤምባሲ የተኮሰው አቶ ሰለሞንን ለመክሰስ እየተዘጋጀሁ እያለ አመለጠኝ ከአሁን በኃላ ወደ አሜሪካ በማንኛውም ጊዜ መምጣት አይችልም ከመጣ ግን ክሱ ይጠብቀዋል” አለች

Freitag, 3. Oktober 2014

ሰበር ዜና- አሜሪካ ”በዋሽግተን ኢትዮጵያ ኤምባሲ የተኮሰው አቶ ሰለሞንን ለመክሰስ እየተዘጋጀሁ እያለ አመለጠኝ ከአሁን በኃላ ወደ አሜሪካ በማንኛውም ጊዜ መምጣት አይችልም ከመጣ ግን ክሱ ይጠብቀዋል” አለች

የጉዳያችን አጭር ዘገባ

ዘሂል” (The Hil) የተሰኘው እ አ አቆጣጠር ከ1994 ዓም ጀምሮ በአሜሪካ የምክርቤት እና የዋይት ሃውስ ጉዳይ ላይ በማተኮር የሚዘግበው ጋዜጣ ዛሬ መስከረም 22/2007ዓም (ኦክቶበር 02/2014) ”Ethiopian diplomat flees US to dodge prosecution” ”ኢትዮጵያዊው ዲፕሎማት ከአሜሪካ ፍትህ ፊት ሸሽቶ አመለጠ” በሚል ርዕስ ስር ባወጣው ዘገባ በኤምባሲው ውስጥ የተኮሰው ሰው የዲፕሎማሲ ከለላ እንዲነሳ እና አሜሪካ ፍርድ ቤት እንዲቀርብ የኢትዮጵያን መንግስት ጠይቆ እንደነበር ይገልፃል።
the hillዘገባውም አያይዞ ”የስቴት ዲፓርትመንት”ቃል አቀባይ ጄን ሳኪ ”ጥያቄያችንን በግልፅ አቅርበናል።ነገር ግን ግለሰቡ ሀገር ጥሎ ጠፋ” ማለታቸውን ያብራራል።ጄን ሳኪ አያይዘውም ”ከሀገር ከወጣ በኃላ ተመልሶ ወደ አሜሪካ የመምጣት ዕድል የለውም ከመጣም ሕግ ፊት መቅረብ ብቻ ነው ዕድሉ” በለዋል።
በእዚህ ዘገባ መሰረት የኢትዮጵያ መንግስት ጉዳዩን በዲፕሎማሲ መፍታት ሲገባው ህገ ወጥ በሆነ መንገድ ግለሰቡ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሀገር ቤት እንዲገባ አደረገ ማለት ነው።
ከዋሽግተኑ ክስተት ወዲህ የኢህአዲግ ደጋፊዎች በማኅበራዊ ድረ ገፆች ላይ በአሜሪካ ላይ የዛቻ ፅሁፎችን እያወጡ ሲሆን አቶ ግርማ ብሩ ግን አንድ አሜሪካን ሀገር ለሚተላለፍ ራድዮ በሰጡት መግለጫ ተቃዋሚዎችን ከመሳደባቸውም በላይ ከአሜሪካን ጋር ያላቸውንግንኙነት እንዳይበላሽ ”ሁሉም ሊንከባከበው ይገባል” ቀረሽ ንግግር ሲማፀኑ ተሰምተዋል።ነገሩ እያመራ ያለው ግን እርሳቸው እንዳሰቡት አይመስልም።አሁን የሚጠበቀው ከሁለቱ አካላት አንዳቸው የሚሰጡት ጠንከር ያለ የቃላት ልውውጥ ብቻ ነው።ብዙዎች አሜሪካ ከፍተኛ ትዕግስት ማሳየቷ እና ከእዚህ በኃላ ግን ልትታገጽ እንደማይገባት ያሰምሩበታል።

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen