Netsanet: ሰበር ዜና የአ.አ ከንቲባ ጽ/ቤት ጠባቂ ፖሊሶች ተታኮሱ_ ነገረ ኢትዮጵያ

Freitag, 24. Oktober 2014

ሰበር ዜና የአ.አ ከንቲባ ጽ/ቤት ጠባቂ ፖሊሶች ተታኮሱ_ ነገረ ኢትዮጵያ








የአዲስ አበባ መስተዳደር ማዘጋጃ ቤት (ከንቲባ ጽ/ቤት) ውስጥ የሚሰሩ ፖሊሶች ዛሬ በግምት ከቀኑ 6 ሰዓት አካባቢ እርስ በእርሳቸው መታኮሳቸውን አስተዳደሩ ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡
ፖሊሶቹ የተታኮሱት በከንቲባው ጽ/ቤት ውስጥ የሚሰሩ ፖሊሶች በነበራቸው ግምገማ በተፈጠረ አለመግባባት እንደሆነ ታውቋል፡፡ ፖሊሶቹ የተታኮሱት ከስብሰባው እንደወጡ እንደሆነም ምንጮቹ ገልጸዋል፡፡
በከንቲባ ጽ/ቤት ፖሊሶች በተታኮሱበት ወቅት የአትክልት ተራን ጨምሮ በአካባቢው የሚገኘው ማህበረሰብ በድንጋጤ ውስጥ እንደነበርና አብዛኛው ከተኩሱ በኋላ ወደ አስተዳደሩ ቢሮ በማቅናቱ በከንቲባው ጽ/ቤት አካባቢ በርከት ያለ ህዝብ እንደሚገኝ ምንጮቻችን ጠቅሰዋል፡፡

ፖሊሶቹ በተታኮሱበት ወቅት ገላጋዮች መሃላቸው በመግባታቸው በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለና ይህም በግምገማው ወቅት ለገላጋይ ያበቃ አጨቃጫቂ ጉዳይ እንደነበራቸው ያሳያል ተብሏል፡፡

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen