Netsanet: ኢትዮጵያ - ምእራባውያን - አንዳርጋቸው - የወደፊት እጣ - ለትግል መነሳት

Samstag, 25. Oktober 2014

ኢትዮጵያ - ምእራባውያን - አንዳርጋቸው - የወደፊት እጣ - ለትግል መነሳት

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)
በአሸባሪው መንግስታዊ ዘራፊ እና አፋኝ ቡድን የታፈነው አቶ አንዳርጋቸው ጸጌ ወያኔ ለመፍታትም ሆነ ለመግደል ዝግጁ አይደለም ። ግደሉት አሊያም ስቀሉት ቢባሉ እንኳን በፍጹም አያደርጉትም። ምእራባውያኑ ከአፍ ወሬ ውጪ ምንም የሚተገብሩት ነገር የለም ፡ እስክንድር ነጋ በቂ ምሳሌ ሊሆን ይችላል ከሰብአዊ መብት ድርጅቶች ጀምሮ እስከ አሜሪካው የውጪ ጉዳይ አናት ኬሪ ድረስ ድምጻቸውን ቢያሰሙም ለይስሙላ እና ለብሄራዊ ጥቅማቸው እንዲሁም ነገ ሌላ መንግስት ቢተካ እንዲህ ብለው ነበር እንዲባልላቸው እና እዳ ማውረጃ ንግግራቸው ለትግሉ ምንም የሚያበረክተው አሊያም ለአንዳርጋቸው የሚፈይደው ነገር የለም ።

ለአንዳርጋቸው ይሁን በእስር ለሚማቅቁት ወገኖቻችን የሚፈይደው ዋናውና አንዱ ጉዳይ የኛ ጠንክረን መታገል እና አንድ እርምጃ መጓዝ ሲሆን የዛን ሰአት የኛን መጠናከር እና መታገል የተመለከቱ ም እራባውያን ምን እንርዳችሁ ከምን ደረሳችሁ ምናምን ማለታቸው እና መጠየቃቸው ግድ የሚልበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም ፡፤ አሁን የሚፈለገው የኛ መታገል እና መታገል ብቻ ነው። የነጮቹ የከንፈር ልብላቤ ከብሄራዊ ጥቅም ሚዛን ሂደት ምስረታ ላይ ስለተመረኮዘ ከንግግር ውጪ ምንም አይፈይድም:

ልብ ማድረግ ያለብን ከማ እከላዊ አፍሪካ እስከ አፍጋኒስታ ከሊብያ እስከ ኢራቅ በተለያዩ የአፍሪካ እና የመካከለኛው እንዲሁም የኢስያ ሃገራት ም እራባውያኑ የሚያካሂዱት የፕሮክሲ ጦርነት የተነሳ ሌላ ዙር ቀውስ በምስራቅ አፍሪካ እና ውጥረት እንዲከሰት ስለማይፈልጉ ከወያኔ ጋር እጅና ጓንት ሆነው ለመስራት አለመቦዘናቸው የሚያመለክተው እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሃገራት ላይ በአሁኑ ሰአት ሊፈጠር የሚችለውን አመጽ እና ችግር መቆጣጠር ይዞ የሚመጣውን ውጤት እርግጠኛ ሆነው ለማወቅ አለመቻላቸው ከወያኔ ጋር እንዲተሳሰሩ አድርጓቸዋል።ምንሊክሳልሳዊ

እንዲሁም ደቡብ ሶማሊያ ላይ ነዳጅ መኖሩን ስካን አድርገው ስላረጋገጡ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ25 አመት በኋላ እንግሊዝ ኤምባሲዋን ሞቃዲሾ የከፈተች ሲሆን ይህን ተከትሎ ከ100 በላይ የብሪታንያ ካምፓኒዎች ካልተረጋጋችው ሶማሊያ ፍቃድ እንደተሰጣቸው ለማረጋገጥ ተችሏል። ይህንን ከሶማሊያ ሊያገኙትን ብሄራዊ ጥቅም ሊያስጠብቅ የሚችለው አገር ቢኖር ወታደሮቹን ለሞት እየገበረ የሚተባበራቸው የወያኔው መንግስት ብቻ ስለሆነ ያላቸውን ሃይል ሁሉ በመጠቀም ሕዝብን በዲፕሎማሲያዊ ቋንቋ በመደለል የአምባገነኖች እድሜ እንዲረዝም ሚናቸውን ይጫወታሉ።

ብቸኛው እና ዋናው ጉዳይ ትግሉ/ጦርነቱ በመሃል እና በዳር አገር ከተፋፋመ ፣ ሕወሓት እና አመራሩ አደጋ ውስጥ መግባት ሲጀምሩ የዛን ወቅት ም እራባውያኑ በሌላው አለም እንደለመዱት ይመጡና አንዳርጋቸውን እንደ ጆከር ካርድ ለመጠቅም ይሞክራሉ። በቃ ወያኔ አንዳርጋቸውን እንዲፈታ እና የተኩስ አቁም ተደርጎ ድርድር እንዲጀመር ያደርጋሉ ከዚህ ውጭ ግን የሃይል ሚዛኑ በወያኔ እጅ ባለበት የመንግስትን ወንበር ተቃዋሚዎች ባላዩበት ሁኔታ ምእራባውያኑ የሚያሰሉት ከወያኔ ጋር ያላቸውን ቁርኝት ነው። ይህንን ለመበጠስ ደሞ የግዴታ የተኩስ ትግል መጀመር አለበት ። ወያኔም ቢሆን የትጥቅ ትግሉ በመሃል አገር እና በዳር አገር ሲስፋፋበት ጭንቀት ውስጥ ስለሚገባ ከአጣብቂኙ ለመውጣት ሲል ያለውን አማራጭ ለመጠቀም ይሞክራል። ወያኔ ደጋፊዎቹን እና ካድሬዎቹን ብእጥቅም ስለገዛቸው ጦርነት ከተስፋፋበት ያለውን ሃይል ሁሉ ወደ ዛው ስለሚያጋድለው ለካድሪዎቹ ጥቅሞች ጊዜ ስለማይኖረው አብዮታዊ መበላላት በፓርቲው ውስት ስለሚፈጠር እድሜውን ማቀጨጭ ከዛም መጣል ይቻላል። መታገል ካልቻልን ባሁኑ አካሄዳችን ወያኔን እንድማንጥለው ማወቅ አለብን።

አንዳርጋቸው የት እንዳለ ባልታወቀበት ሁኔታ ቶርቸሩ ባልቆመበት ሁኔታ ላይ 500 ሚሊዮን እነ ብሪታንያ እየሰጡ ባለበት ሁኔታ ወያኔ እና የየመን መንግስት የሚፈልጉትን ነገር እንዲያደርጉ ቀድመው ላይሰንስ አድርገዋቸውል ለማለት መገመት ብቻ ሳይሆን ያስደፍራል።አስር ጊዜ ወያኔዎችን የሚያጥላላ ነገር ከመጻፍ በየመንገዱ ሰልፍ ከመውታት በጋራ ተሰባስበን ሳንናናቅ እና ከኛ በላይ አዋቂ የለም ብለን ሳናስብ አንዱ ለ አንዱ ዝቅ ብሎ የወያኔን ስልጣን አደጋ ውስጥ የሚከት ከባባድ እንቅስቃሴ ማድረግ ከቻልን በትግላችን ስኬት ምእራብያውያኑን ማሳመን እንደምንችል ማወቅ አለብን። ህዝባችንንም ነጻ ማውጣት እንደምንችል መረዳት ግድ ይላል።#ምንሊክሳልሳዊ

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen