Netsanet: የኬንያው ፕሬዚደንት በፈቃዳቸው ሥልጣናቸውን ለቀቁ!!

Donnerstag, 9. Oktober 2014

የኬንያው ፕሬዚደንት በፈቃዳቸው ሥልጣናቸውን ለቀቁ!!

እንደዚህ የሚል እንደዚህም አይነት የሀገር መሪ አለ ለካ አፍሪካ ውስጥ???
“የ40ሚሊዮን ህዝብ ባለቤት የሆነችውን አገሬን በፍርድ ቤት ፊት አላቆማትም”
this is so astonishing national feeling and kenianism feeling!
I would be proud if i were keniyan!
የኬንያው ፕሬዚደንት በፈቃዳቸው ሥልጣናቸውን ለቀቁ!!
October 8, 2014
የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የቀረበባቸውን ክስ እንደፕሬዚደንት ሳይሆን እንደማንኛውም ተራ ዜጋ ለማድመጥና ለመከላከል ሲሉ ባልተለመደ ሁኔታ በድንገት ኃላፊነታቸውን ለቀው ለምክትላቸው ዊሊያም ሩቶ በትረ ሥልጣናቸውን በጊዜያዊነት አስረከቡ።
ፕሬዝዳንት ኬንያታ ውሳኔያቸውን ያስተላለፉት በትናንትናው ዕለት በአገሪቱ ፓርላማ ፊት በመገኘት ነው።“የ40ሚሊዮን ህዝብ ባለቤት የሆነችውን አገሬን በፍርድ ቤት ፊት አላቆማትም” በማለት በግለሰብ ደረጃ ፍርድ ቤት ለመቅረብ ለምን እንደፈለጉ ኬንያታ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ፕሬዝዳንት ኬንያታ ለፍርድ የሚቀርቡት እ.ኤ.አ በ2008 በአገሪቱ በተካሄደው ምርጫ ወቅት በተነሳው ግጭት በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በመሞታቸውና በዚህም ጉዳይ እጃቸው አለበት የሚል ክስ የተመሰረተባቸው በመሆኑ ነው።
ኬንያታ በፍርድ ቤቱ ነፃ ከወጡ ሥልጣናቸውን መልሰው ይረከባሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ክርክሩ ግን በምን ያህል ጊዜ እልባት ሊያገኝ እንደሚችል የታወቀ ነገር የለም።
ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በኩል በኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ላይ የቀረበውን ክስ በማውገዝ በግልጽ የተቃውሞ አቋም መያዛቸው የሚታወስ ነው።
ምንጭ፡ ሰንደቅ ጋዜጣ

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen