Netsanet: ቅድመ ምርጫ 2007 እና የተቃውሚዎች እጣ ፋንታ

Dienstag, 24. Juni 2014

ቅድመ ምርጫ 2007 እና የተቃውሚዎች እጣ ፋንታ



መቼም የምርጫ ነገር ሲነሳ በኢትዮጵያ ታሪክ የጎላ ቀለም ያለው ምርጫ 97 ነው ምክንያቱም ከዚያ
በፊት የነበሩት ምርጫዎች በኢህአዲግም ሆነ በደርግ መንግስት የነበሩት የይስመላ ምርጫዎች ነበሩ
ምርጫ 97ም ቢሆን የዲሞክራሲ ጭላንጭል የታየበት በአዲስ አበባ እስከ ምርጫው እለት ሲሆን
በክልሎች ግን ምርጫው አንድ ወር እስኪቀረው ነበር በክልሎች ገዝው ኢህአዲግ ቀሪውን አንድ ወር
አፈናውን እናወከባውን አጠናክሮ ከመቀጠሉም በላይ አልፎ አልፎ ጠንካራ ተፎካካሪዎች ባሉበት ክልል
ግድያም ይፈፅም ነበር በአዲስ አበባም ቢሆን ከምርጫው ውጤት በዃላ የምርጫውን ውጤት
በመቀልበስ የዲሞክራሲ ጭላንጭሉን አጨልሞታል ከዚያም በዃላ የምርጫውን ውጤት ተከትሎ
በሃይል ገንፍሎ የወጣውን የህዝብ ቁጣ በሃይል ከመቀልበስ ውጭ አማራጭ ያጣው ኢህአዲግ
አፈናውን እና ግድያውን አጠናክሮ በመላ ሃገሪቱ ቀጠለ እናም ተቀዋሚ ጎራው እጣ ፋንታውግማሹ
እስር ቤት ግማሹም ኢህአዲግ ባሰመረለት መንገድ መሄድ ብቻ ሆነ እናም የምርጫ 97 ድራማ በዚህ
መልኩ ተጠናቀቀ
ቀሪው አምስት አመት ቀጣዩ ምርጫ እስኪመጣ ግምት ሰጥቶት የነበረውን የምክር ቤቱን
ከ540አካባቢ መቀመጫ አንድ አራተኛ ለተቀዋሚ በመስጠት ያለውን የውጭ ጫና በማቅለል የተዘጉትን
የእርዳታ ማእቀብ ለማስለቀቅ የሰራው የሂሳብ ስሌት ባለመሳካቱ እራሱን እንዲፈትሽ ምርጫው ትልቅ
ማሳያ ሆኖታል
በምርጫው ማግስት ኢህአዲግ ውጤቱን በሃይል መቀልበሱ በብዙዎች ቢታመንም ለኢህአዲግ ግን
ውጤቱ ያልጠበቀው እና ያልተዘጋጀበት በመሆኑ በቀጣዩ የምርጫ ጊዜ ኢህአዲግ ካለፈው ተምሮ ብዙ
ነገሮችን እንደሚያስተካክል የብዙዎች ግምት ቢሆንም ፓርቲው ግን ካለፈው ተምሬአለሁ የሚለውን
የምፀት አባባል በአደባባይ እየተናገረ ለቀጣዩ 2002 የምርጫ ዘመን የሚከተለውን መዋቅር ዘረጋ
ከምርጫ 97 በዃላ በዋነኛነት የተወሰዱ እርምጃዎች
1 በህትመት እና በህትመት ውጤቶች ላይ ጫና መፍጠር እና አፋኝ የሆኑ የፕሬስ ህግ አዋጆችን
መተግበር
2 በፀረ-ሽብር እንቅስቃሴ ከአሜሪካ ጋር በህብረት ፀረ-ሽብርተኝነትን መከላከል መርህ ሰበብ
በምስራቅ አፍሪካ የአሜሪካ ዋነኛ አጋር በመሆን ጠቀም ያለ ወታደራዊ የቁስ እና የገንዘብ ድጋፍ
ኢህአዲግ መራሹመንግስት እንደሚያገኝ ይታወቃል መንግስት ይሄንን የሽብር ጥቃት መከላከል
ሰበብ በመጠቀም በሃገርውስጥ የፀረ- ሽብር አዋጅ በማቋቋም ብሎም በመተግበር በሃገርውስጥ
በሰላማዊ ትግል የተደራጁትን ፓርቲዎችን እና የነፃነት እና ዲሞክራሲ እጦት ተቋውሞ
እንቅስቃሴዎችን በሽብርተኝነት በመፈረጅ አዋጁን በመጠቀም ብዙዎችን ለእስር በመዳረግ
የሰላማዊ ትግል እንቅስቃሴዎችን መድረክ ማጥበብ ማቀጨጭ እና ብሎም ማጥፋት
3 በምርጫ 97 ከታዩት ጉልህ የኢህአዲግ ስህተቶች ወጣቱን በተለይ ሰራአጥ ወጣቶችን በአደገኛ
ቦዘኔነት መፈረጅ እንዲሁም የተማረውን ሃይል ማግለል ስለነበር ይህንን እንደፓርቲው ስህተት
በመቁጠር የሙሁሩን ጎራ በከፊልም ቢሆን መተካካት በሚል መርህ ጥቂት ጥቅማጥቅሞችን
በማጋራት ብሎም ሙያዊ ሹመቶችን በመስጠት ልማታዊ ሙህር ልማታዊ ጋዜጠኛ ልማታዊ
ዶክተር ወ.ዘ.ተ እያለ ወደዱም ጠሉም የፓርቲው አባል ማድረግ
4 ስራ አጥ ወጣቶችን በየቀበሌው እንዲደራጁ በማድረግ ባቋቋማቸው የማታለያ ገንዘብ ብድር
ተቋማት ብድር በመፍቀድ እንዲደራጁ በመፍቀድ ሲደረግ ለዚህም የመጀመራያው መስፈርት
የድርጅቱ አባል መሆን ሲሆን ለዚህም ዋናው አላማ ለተቀዋሚው ጎራ አባል ለመሆን እየሄደ
የለውን ወጣት በጥቅማጥቅም ማስቀረት
5 ቀሪውን የህብረተሰብ ክፍል በተለይ ቀበሊ ነዋሪዎችን አንድ ለአምስት መርህ በኢህአዲግ
ቋንቋ(መጠርነፍ)መያዝ እና በህዝቡ ቁጥር ልክ የሚመስል የደህንነት ሃይል ማሰማራት
ይሄውም ተቀዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በህዝቡውስጥ ገብተው ምንም አይነት የፖለቲካ
እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ ማድረግ
6 ልማታዊ መንግስት በሚል መርህ በየመንደሩ በእርዳታ ድርጅቶች የተሰሩትን የውስጥ ለውስጥ
መንገዶች በኮብል እስቶን በመቀየርለዚሁም በአብዛኛው ሰራ የሌላቸውን ወጣቶችን በማሰማራት
አላማው ጥሩ ቢሆንም ከህብረተሰቡ የሚጠየቀው ገንዘብ ግን የተጋነነ ነው ኢህአዲግ ግን በዚህ
ሲስተም በአንድድንጋይ ሁለት ወፍ የሚለውን የአባቶች አባባል ተጠቅሞበታል ይሄውም
በልማት ሰበብ ለአባላቱ ጠቀም ያለ ገንዘብ ማስገኘት እና ሌላው አዳዲስ አባሎችን ማብዛትነው
እንግዲህ እነዚህን ከላይ የተጠቀሱትን የኢህአዲግ የ2002 የምርጫ ዝግጅት ማስቀየሻ
ስልቶች ሲሆኑ እንደእቅዱ ሲተገበር ያተረፈው ነገር እጅግ ብዙ ቁጥር ያለው ደጋፊ ማፍራት
ቢሆንም እውነታው ግን ኢህአዲግ ያፈራው እውነተኞቹን ደጋፊዎችን ሳይሆን በጥቅም
የታሰሩትን እና ለሆዳቸው የተገዙ ደጋፊዎችን ሲሆን የዚህም የመጨረሻ ውጤት የደጋፊው
ቁጥር በጨመረ ቁጥር የሁሉንም ጥቅም መጠበቅ አይቻልም ደጋፊዎችም ጥቅመኞች ስለሆኑ
ልማታዊ ሳይሆኖ በተቃራኒው ሙሰኞች እና ዘራፊዎች ናቸው እናም የኢህአዲግ ጠላቶች
የሚመነጩት ከራሱ ደጋፊዎች ሲሆን እነሱም እነዚህ በጥቅም የመጡቱ ጥቅማቸው በተቋረጠ
ጊዜ የኢህአዲግ የመጨረሻ ጠላቶች ናቸው
እንግዲህ ከላይ በጠቀስናቸው የማስቀየሻ ስልቶች ኢህአዲግ ምርጫ 2002ን ያለምንም
ተቀናቃኝ ምርጫውን 99ፐርሰንት አሸንፌአለሁ ለማለት አስችሎታል ለዚሁም በአሸነፈ ማግስት
የቀድሞው ጠ/ሚኒስት ሲናገሩ‹‹ ይህ ህዝብ ኢህአዲግ ካለፈው ስህተቱ የሚማር ፓርቲ
መሆኑን ተገንዝቦ ለ5አመት ኮንትራቱን ሰጥቶናል ይህ ለኛ ትልቅ ማስጠንቀቂያ ነው ቃላችንን
ካልጠበቅን በድምፁ የሰጠንን ካርድ መልሶ ይነጥቀናል›› ሲሉ አቶ መለስ የንቀት ንግግር
አድርገዋል በአንፃሩ ግን እንዴት እንዳሸነፉ እራሳቸውም ህዝቡም ያውቃል እናም የ2002
ምርጫ እንከን የለሽ ምርጫ በሚል ድራማ ተጠናቋል
በቀጣዩ መጣጥፍ በምርጫ 2007 ዘገባ ላይ ያተኮረ የዚህን መጣጥፍ ክፍል 2 ይዠ
እቀርባለው እስከዚያው ቸር ይግጠመን

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen