Netsanet: በኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያዊነቴና እና ኢትዮጵያዊያን ላይ የሚመጣብኝ እንትፍ ብያለው ጠላቴ ነው!! ጠላቴ ነው!!!

Freitag, 6. Juni 2014

በኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያዊነቴና እና ኢትዮጵያዊያን ላይ የሚመጣብኝ እንትፍ ብያለው ጠላቴ ነው!! ጠላቴ ነው!!!

በኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያዊነቴና እና ኢትዮጵያዊያን ላይ የሚመጣብኝ እንትፍ ብያለው ጠላቴ ነው!! ጠላቴ ነው!!!

›>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>

ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያዊነትን እና ኢትዮጵያዊያንን ለማጥፋትና ለማስነሳት በሚሹ ሁሉ የተፈጠረች ስመ፣ ቅርፀ፣ ስዕለ፣ ምዕናበ፣ ታሪከ እና ምኞተ ብዙዋ ኢትዮጵያ…
#EthioMuslimPrisoners #EthioMuslimCommitteeTrial ##Ethiopia #UDJ #Blueparty #Medrek #Ginbot7 #Jiustice #Freedom #ethiopian politics #Eppf #minilik salsawi #አብቢ #ሳምቮድሶን

አለም ላይ በርካታ ኢትዮጵያዎች እንዳሉ ለመናገር ምንም አይነት መረጃ ማሳደደድ አያስፈልግም

1. ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኘው ነፃነት ናፋቂ ጭቁን ህዝብ የሚያውቃት እውነተኛዋ ኢትዮጵያ

2. ዲያስፖራው ነፃነት ናፋቂ የጭቁኑ ሎካል ህዝብ አካል የሆነው የተጨቋኝ መከታ ህዝብ ኢትዮጵያ

3. ኢህአዴግ የሚያውቃት ኢትዮጵያ

4. ሌላው ክ/ዓለም የሚያውቃት ኢትዮጵያ

5. ታሪክ ያጎሳቆላት ኢትዮጵያ

6. ተገንጣይና ገንጣዮች የሚያውቋት ኢትዮጵያ

7. ኢጣሊያና እንግሊዝ ፓኪስታንና ኤርትራዊያን የሚያውቋት ኢትዮጵያ

8. ግራ የተጋባው ሁሉ የሚያውቃት ኢትዮጵያ

9. ሆዳሙ ካድሬ የሳላትና የጨነቆራት የጎረጎራት ኢትዮጵያ

10. ታሪካዊ ሥዕተቶችና እውነቶች የሚገልጧት ኢትዮጵያ

11. ተጀምረው ያልተቋጩ እውነቶች እና ሳይጀመሩ የተቋጩ ታሪካዊ እውነታዎች የሚገልጧት ኢትዮጵያ

12. በልዩነቶች መካከል ያለች ነፍስ ውጭ ነፍስ ግቢ ውስጥ ያለች ኢትዮጵያ

13. በሚላክላቸው ቁልል መረጃ ላይ በመነሳት አንድም የሃገራችን ባለስልጣናት የሚያውቋ ት ኢትዮጵያና የውጭ ረጅ ድርጅቶች የሚያውቋት ኢትዮጵያ

14. "እኛ" የምናውቃት ኢትዮጵያ

15. የምንፈልጋት ኢትዮጵያ

16. ፖለቲካ ፓርቲዎች የሚለያዩባት ኢትዮጵያ /ፖለቲካ ፓርቲዎች በመካከላቸው ያለው ልዪነት የፈጠራት ኢትዮጵያ/

17. የአስተሳሰብ ስፋትና ጥበታችን የፈጠራት ኢትዮጵያ

18. ተማርኩ የሚለው ኢትዮጵያዊ ኢትዮጵያ የሚላት ኢትዮጵያ

19. ያልተማረውና በተለይም ያለፉት ስርዓቶች የተዋትን ሃገር
የሚያውቃት እና እንዲህ ናት የሚሏት ኢትዮጵያ

20. ቅኝ ገዥዎች የሚያውቋት ኢትዮጵያ

21. ስለፖለቲካ አይመለከተኝም የሚሉ አካላት የሚያውቋት ኢትዮጵያ

22. በኢትዮጵያዊያን መካከል ግጭት እንዲኖር የሚፈልጉ አካላት የሚያውቋት ኢትዮጵያ

23. መከላከያ ሰራዊቱና ፀጥታ ሃይሉ የሚያውቋት ኢትዮጵያ

24. ጎረቤት ሃገራት የሚያውቋት ኢትዮጵያ

25. የታሪክ ምሁራን የሚያውቋት ኢትዮጵያ

26. ያለመረጃ ኢትዮጵያ እንዲህ ናት ኢትጵያ ይች ናት ብሎ የሚያውቃት ኢትዮጵያ

27. የኣለም ሚዲያዎች በየራሳቸው አመለካከትና ባላቸው መረጃ የሚያውቋት ኢትዮጵያ

28. ኢቲቪ የሚላት ኢትዮጵያ

29. ሃይማኖቶች የሚሏት ኢትዮጵያ

30. ኢንቨስተሩና ባለሃብቱ የሚያውቃት ኢትዮጵያ

31. ዘረኛ አመለካከት ያላቸው አካላት የሚያውቋት ኢትዮጵያ

32. ዶ/ር መራራና መሰሎቹ የሚያውቋት ኢትዮጵያ፣ እህህህህ አጼ ዮሃን፣ አጼ ሚኒሊክ እንዲሁም ሌሎች አጼዎቻችን እና አጼ
ቴወድሮስ የሚያውቋት እንዲሁም የሞቱላት ኢትዮጵያ እስካሁን ቁጭተን አዝሎ

33. ጠላትና ወዳጆቿ የሚያውቋት ኢትዮጵያ

34. ኢትዮጵያዊነት የሚያንገበግባቸው አካላት የሚያውቋት ኢትዮጵያ

35. ኢትዮጵያዊያን የሚያውቋት ኢትዮጵያ

36. አማጺ ቡድኖች ካሉበት ሆነው የሚያውቋትና ተገድደውም ሆነ ለስትራቴጅ የሚያውቋትና የሚቀበሏት ኢትዮጵያ

37. ኤርትራዊያን፣ ሱዳናዊያን፣ ሶማሊያዊያን፣ ጅቡቲያዊያን እንዲሁም ኬንያዊያን የሚያውቋት ኢትዮጵያ እንዲያውም ግብፅ፣ ምዕራባዊያን እና የአረቡ ባህረሰላጤ የሚመኛትና የሚያውቃት ኢትዮጵያ

38. ባለሃብቱ ቨርሰስ ድሃው ብለቶ የሚያድረው ያጣ የሚያውቋት ኢትዮጵያ

39. ብሄሮች ተብለው የኢህአዴግ ፌደራሊዝም /ፌዝራሊዝም/ የፈጠራቸው /ያስፈነጠራቸው/ ልጆቹ የሚያውቋት ኢትዮጵያ

40. ግለሰቦች፣ ድርጅቶች፣ ባለስልጣናት፣ ሃይማኖት ተቋማት፣ ታሪካዊ አባቶችና እናቶች፣ ዕድሜ ባለፀጎች ገለመሌ የሚያውቋት ኢትዮጵያ ከራሳቸው ደካማ አስተሳሰብ ከራሳቸው እውነተኛ መረጃ ከራሳቸው ጥቅም ከራሳቸው አቅም በመነሳት የሚመኗትና የሚያውቋት ኢትዮጵያ

41. የማናውቃት ኢትዮጵያ…

42. ኢትዮጵያ የምትባል ሃገር ስለመኖሯ የማያውቅ ህዝብ የሚስላት አፈታሪካዊ እና መፅሃፍ ቅዱሳዊ ምናባዊ ኢትዮጵያ


43. ደራሲውና ታሪክ ፀሃፊው ጦማሪውና ጋዜጠኞች እንዲሁም ሌላው የሚያውቃት ኢትዮጵያ ወዘተ…

ለማንኛውም ኢትዮጵያዊያን እና ዓለም የሚያውቃት ኢትዮጵያ በትንሹ ይህን ትመስላለች፡፡ እስቲ በናታችሁ ተፈጥሯዊ ልዩነቶቻችን ለምሳሌ የቋንቋ፣ ዘር፣ ቀለም፣ የትውልድ ቦታ፣ ቢሎንጊንግነስ፣ ወዘተ…

ፍጹም ተፈጥሯዊ ልዩነቶቻችን ጠብቀን እና ተንከባክበን ከተፈጥሯዊ ልዩነቶቻችን ውጭ ያሉትን "መጤ ሰው ፈጥሮሽ" ልዩነቶቻችን ለምሳሌ ታሪክ ያበላሻቸውና ድጋሚ ሊደገሙ የማይገባቸውን ልዩነቶቻችንን፣ ተፈጥሯዊ ልዩነቶቻችንን መርጠን ፈልገን ቢሎንግ እንዳደረግንበት በመቁጠር በተሳሳተ መልክ የሚፈጠሩ ዘረኛ አመለካከቶችን፣ በስዎች ፍላጎት ላይ የተመሰረቱ ልዩነቶቻችንን፣ ስልጣን ላይ ባለው አካል እና በስልጣን ጥመኞች የተፈጠሩና የሚቆሰቆሱ ልዩነቶቻችንን፣ ኢትዮጵያ ተበታትና እንደ ደሃ ቁምጣ ሽርጥ መስላ ማየት የሚፈልጉ አካላት የፈጥሯቸው ልዩነቶቻችንን፣ በአጠቃላይ በመቻቻልና በመፋቀር በመተሳሰብና በአንድነት የምናውቃት ኢትዮጵያን ለመፍጠር የበኩላችን እናበርክት፡፡

እኔ አብቢንም እስካሁንም ሳደርግ እንደነበረው ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያዊነትን እና ኢትዮጵያዊያንን እኔንም ጭምር የምችለውን ያህል የሚከፈለውን መስዋዕትነት ከፍየ ለማዳን በማደርገው ትግል ትንሽ እጣቴን ከትንሽ እጣቴ በማቆላለፍ ቃል ገብቻለው፡፡
ትግሉ የትኛውንም ያህል መስዋዕትነት ሊጠይቅ ቢችልም ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያዊነትን እና ኢትዮጵያዊያንን ከአንድነታቸውና ከፍቅራቸው ሊበታትናቸው የሚፈልግን ሁሉ ድራሹን እስከማጥፋት ድረስ ለመሄድ ዝግጁ ነኝ፡፡

ይህንን የሚቃወሙ መብታቸው ነው ብየ ማለፍ አልሻም ምክንያቱም ሰው የሚፈልገውን መግለፅ መብቱ ቢሆንም ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያዊነትን እና ኢትዮጵያዊያንን አንድ አድርጎ ጠንካራዋን ማለትም በአንድነቷ በኩል የማይደራደሩ አባቶቻችን ያስረከቡንን ኢትዮጵያን ለመፍጠር የሚደረግን ግብ ግብ በተፃራሪው የሚቆምና ፀረ-ኢትዮጵያን፣ ፀረ-ኢትዮጵያዊነትን እና ፀረ-ኢትዮጵያዊያን ላይ የሚዘባበት ዝተት አልሻም፡፡

አሁን ኢትዮጵያዊያን ራሳቸውን የሚመረምሩበትና ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያዊነትን እና ኢትዮጵያዊያንን የሚያድኑበት ብቸኛ ጊዜ ነው፡፡

ከዚህ ጊዜ ትንሽ ብንዘገይ ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያዊነት እና ኢትዮጵያዊያን የለንም፡፡ አትጠራጠሩ የለንም፡፡ ምክንያቱም ጠላት እየቀደመን ነው፡፡ ዳቧችን ሳይበላ እንጅ ከተበላ በኋላማ የኛ ማደንፈቅ የኛ መወራጨት ምን ጥቅም አለው ከመላላጥኛ ከመጋጋጥ ራስን ከመጉዳት ውጭ፡፡ ይህ ነው ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያዊነትን እና ኢትዮጵያዊያንን ማዳኛ ትክክለኛ ጊዜው፡፡

ይህን ጊዜ ተገንጣይ አስገኝጣዮች ዘረኛ እና በጥቅም ልክፍት የታመሙ ሁሉ መቃብራችንን እየማሱ ይላፉናል፡፡ የሚምሱት መቃብር ለራሳቸው ብለው ሳይሖን የሚያቅዱት ለኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያዊነት እና ኢትዮጵያዊያን ነው!!! ነገር ግን ከቀድምናቸው ራሳቸው ሳንገፋቸው ከማሱት ጉድጓድ ውስጥ ይገባሉ ፡፡

ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያዊነትን እና ኢትዮጵያዊያንን ህልም ያላደረገ ወደ መቃብር ይገባል!!!!

እኔ አብቢን ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያዊነትን እና ኢትዮጵያዊያንን መቃብር ውስጥ ለማስገባት ጉድጓድ የሚምሱትን በየትኛውም የትግል አቅጣጫ ታግሎ ለማታገል ዝግጁ ነኝ፡፡

ይህ ፅሁፍ ለማንም ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያዊነትን እና ኢትዮጵያዊያንን ለሚሻ ሁሉ ነው፡፡ ይህንን ሃሳብ የሚነቅፍ ያለምክንያት የሚዘበዝብ ሁሉ ግን ጠላቴ ነው!! እርም ብያለው ጠላቴ ነው፡፡
በኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያዊነቴና እና ኢትዮጵያዊያን ላይ የሚመጣብኝ እንትፍ ብያለው ጠላቴ ነው!!! ጠላቴ ነው!!!
#አብቢን ንኝ

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen