Netsanet: ሁሉ ነገር ከመጋረጃው በስተጀርባ የሚወሰንባት አገር

Dienstag, 10. Juni 2014

ሁሉ ነገር ከመጋረጃው በስተጀርባ የሚወሰንባት አገር

በእውነት ባለስልጣኖቻችን አሳዘኑኝ
በ1997 ምርጫውን ተከትሎ የደረሰውን ዘግናኝ ጭፍጨፋ እንዲያጣሩ የአጣሪ ኮሚሽኑ ሰብሳቢ ሆነው ተመርጠው የነበሩት የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንት ፍሬሕይወት ሳሙኤል የኮሚሽኑ ሰብሳቢ ተደርገው መሾማቸውን ከጓደኛቸው መስማታቸውን ለኢሳቱ ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ሲናገሩ አደመጥኩ፡፡
ፍሬሕይወት በእኔ መሾሜን አለማወቅ ብቻ አትደነቁ በማለትም አሰፋ ከሲቶ የፍትህ ሚኒስትር ተደርገው እንደሚሾሙ ያወቁት ሹመቱ ከመጽደቁ አንድ ቀን በፊት መሆኑን ተናግረዋል፡፡በቃ ሰዎቹ ስለሚሾሙበት ቦታ ፍላጎት ይኑራቸው አይኑራቸው ሳይጠየቁ ስለራሳቸው መረጃ ተነፍገው ከመጋረጃ ጀርባ ባለው ሃይል ይመደባሉ፡፡ምደባውን መቀበል ደግሞ ግዴታ ብቻ ይሆናል፡፡
ፍሬህይወት አሁን ጠቅላይ ሚኒስትር የሆኑት ኃይለማርያም ደሳለኝ በተንቀሳቃሽ ስልካቸው ደውለውላቸው ‹‹አሁን ከአዲስ አበባ ይደወልልሃል የሚሉህን ዝም ብለህ ተቀበል››እንዳሏቸው በማስታወስ እንዴት ዝም ብዬ እቀበላለሁ ነገሩን ሰምቼ አስቤበት መልስ እሰጣለሁ ››ሲሏቸው ስልኩ እንደተዘጋ ነግረውናል፡፡
እንዴት ነው ነገሩ ታዲያ ባለስልጣኖቻችን ፈልገውትና ተመኝተውት ያገኙት ስልጣን የትኛው ይሆን?ሌላው አስገራሚ ነገር ተቀበል የተባሉትን ስልጣን እስከ መቃብር ይዘው ለመውረድ አንዳንዶቹ ቁርጠኝነት ማሳየታቸው ነው፡፡ሰው እንዴት ሌላው ሁን ባለው ለመሆን እየተፍጨረጨረ ራሱን ሳይፈልግ ይህችን የራሱን ዓለም ይሰናበታል?

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen