Netsanet: በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የአንድነት መዋቅር ስራ አስፈጻሚ አባል ወጣት መልካሙ አምባቸው ተፈታ፡፡

Samstag, 14. Juni 2014

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የአንድነት መዋቅር ስራ አስፈጻሚ አባል ወጣት መልካሙ አምባቸው ተፈታ፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የአንድነት መዋቅር ስራ አስፈጻሚ አባል ወጣት መልካሙ አምባቸው ተፈታ፡፡

---------------------------------------------------
ሰኞ ግንቦት 18 ቀን 2006 ዓ.ም ማታ ራት ከበላ በኋላ ከዩኒቨርስቲ ግቢ ባልታወቁ ኃይሎች ታፍኖ የተወሰደው ወጣት መልካሙ አምባቸው ያለበት ሳይታወቅ ቀናቶች ማለፋቸው ያሳሰበው አንድነት ፓርቲ በየፖሊስ ጣቢያው ፍለጋውን ቢያጠናክርም ሊያገኘው ባለመቻሉ ግንቦት 29 ቀን 2006 ዓ.ም ለአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚደንት ጽ/ቤት 
በግልባጭ፡ - ለትምህርት ሚኒስቴር 
- ለአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚ ፋኩልቲ 
- ለአ/አ ዩኒቨርስቲ ጥበቃ ዋና ክፍል 
- ለፌዴራል ፖሊስ 
- ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን 
- ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን 
- ለሰብአዊ መብት ጉባኤ በደብዳቤ ተማሪ መልካሙ አምባቸው ያለበት ሁኔታ እንዳሳሰበውና ያለበትን ሁኔታ መረጃ እንዲሰጡ ጠይቋል፡፡ ነገር ግን ፍ/ቤት ይቀርባል ተብሎ የፓርቲው አመራሮች በተደጋጋሚ ፍ/ቤት ቢገኙም ታሳሪውን ሊያገኙ አልቻሉም፡፡ ረቡዕ ሰኔ 4 ቀን 2006 ዓ.ም በግምት 5፡00 ሰዓት አካባቢ ወደ ፓርቲው ጽ/ቤት ደውሎ 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ መታሰሩንና ፍ/ቤት ቀርቦ የ4000.00 (አራት ሺህ ብር) ዋስትና እንደተጠየቀ ከእስር ቤት በፖሊስ ታጅቦ ወጥቶ ስልክ ደውሎ እንዳስረዳ የፓርቲው አመራሮች ለፍኖተ ነፃነት ገልጸዋል፡፡ ወጣት መልካሙ አምባቸው የተከሰሰበት ክስ ግንቦት 20ን አስመልክቶ በዩኒቨርስቲ ውስጥ ሁከትና ብጥብጥ ለመፍጠር ወረቀት መበተን የሚል ክስ እንደሆነና ፍ/ቤት ቀርቦም እኔ የአንድነት ፓርቲ አባል በመሆኔና በጎንደር ድንበር ማካለል ዙሪያ በሰጠሁት መረጃ ምክንያት ክትትልን አፈና ለማድረግ በተደጋጋሚ ሙከራ ይደረግብኝ ነበር እንጂ እኔ በዩኒቨርስቲ ውስጥ ሁከትና ብጥብጥ አላነሳሳሁም፣ ወረቀትም አልበተንኩም በማለት በእስር ቤት የሚፈፀምበትን ድብደባም ለፍ/ቤቱ አስረድቷል፣ ፍ/ቤቱም ሰብአዊ መብቱ መከበር አለበት ድብደባ ሊፈጸምበት አይገባም በማለት ታሳሪው ላይ የሚደረገው ተጽዕኖ እንዲቆም በማሳሰብ በትላንትናው ዕለት ከ18 ቀን እሥር በኋላ ከቀኑ በአሥር ሰዓት ተኩል በ4000.00 ብር ዋስትና ከእስር ተለቋል፡፡


Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen