Netsanet: የዞን ዘጠኞች እና የጋዜጠኛው የፍርድ ቤት ቀጠሮ ዛሬም ረዘመ። የእናቶች እንባ ይቁም

Samstag, 14. Juni 2014

የዞን ዘጠኞች እና የጋዜጠኛው የፍርድ ቤት ቀጠሮ ዛሬም ረዘመ። የእናቶች እንባ ይቁም

የዞን ዘጠኞች እና የጋዜጠኛው የፍርድ ቤት ቀጠሮ ዛሬም ረዘመ። የእናቶች እንባ ይቁም!


ላለፉት 50 ቀናት ካለምንም ክስ በምርመራ ቀጠሮ እየተጉላሉ የሚገኙት የዞን ዘጠኝ አባላት እና ጋዜጠኞች ዛሬ ሶስቱ ወያኔ አራዳ ችሎት ላይ ቀርበው ነበር። የዞን 9 ጦማርያኖቹ ናትናኤል ፈለቀ፣ አጥናፍ ብርሃኔ ፣ ዘላለም ክብረት፣ ጋዜጠኛ ኤዶም ካሣዬ ጋዜጠኛ አስማማው ሃይለጌዪርጊስ እና ጋዜጠኛ ተስፋዓለም ወልደየስ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። ቢያንስ ቁጥሩ ወደ 300 የሚሆን ህብረተሰብ በፍርድ ቤቱ በመገኘት አጋርነቱን አሳይቷል።
ናቲና ኤዶም በፈገግታ የተሰበሰበውን ሰው ሰላም እያሉ ሲያልፉ አጥናፍ ግን ትንሽ ተከዝ ብሎ ነበር።ሰው ዛሬ በዛ ብሎ የታየ ሲሆን በእጅ ሰላምታ ሰጥቷቸዋል። እናቶችና የተወሰኑ ሴቶች ያለቅሱ ነበር! የእናቶች እንባ ይቁም!
ፍርድ ቤቱ በወያኔው የአራዳ ችሎት ካቀረባቸው በኋላ ወያኔያዊ ፖሊስ በጠየቀው መሰረት ሌላ 28 የቀጠሮ ቀን ተሰቶትል።

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen