Netsanet: ስውሩ እጅ ኢሉሚናቲ ( Illuminati 666 )

Dienstag, 3. Juni 2014

ስውሩ እጅ ኢሉሚናቲ ( Illuminati 666 )

Jun 3/2014
say every thing that you like to say about this...
ስውሩ እጅ
ኢሉሚናቲ ( Illuminati 666 )
ኢትዮጵያ አዲስ የሚመሰረተው የአለም መንግስት ( NEW WORLD ORDER 666 ) አባል አገርና በምስራቅ አፍሪካ ተጽኖ ፈጣሪ አገር መሆኑዋን ያውቃሉ?አሁን ስላለንበት ስለ መጨረሻው ዘመን ምን ያህል ያውቃሉ? በመጽሐፍ ቅዱስ ስለ መጨረሻው ዘመን የሚያሳውቀውን የ666 ምልክት መቀበል መጀመሩን ምንያህል የውቃሉ? ስለ ኢሉምናቲ ስለተባለው የሰይጣን ማህበር ምን ያህል ያውቃሉ? በአለም ላይ እየተከሰቱ ያሉትን ችግሮች ምክንያታቸው ምን እንደሆነ ያውቃሉ ? ወደ ሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታ ስንመለስ ሙሉ በሙሉ ሊያጠፉን ከቀረቡት ምክንያቶች መካከል ፍቅር ማጣት : ዘረኝነት : ጎሰኝነት : ጥላቻ : ክፋት : ምቀኝነት : መለያየት : ሰላም ማጣት : አንድነት ማጣት : ድህነት : በሽታ : ስቆቃ : ስደት : እንግልት : ጭቆና : ፓለቲካዊ : ኢኮኖሚያዊ : ማህበራዊ ቀውሶች ምክንያታቸው ምን እንደሆና ያውቃሉ? …….. ሌሎችንም ተያያዥ የሆኑ ጥያቄዎች መልሶቻቸውን በተከታታይ በሚወጡት ጽሁፎች ለማየት ይቻላል:: የዚህ ጽሁፍ ዋና አላማ ህዝበ ክርስቲያኑ ከጠፋበት ህይወት ለመመለስ ሲሆን በጌታም ያላችሁ በጌታም የሌላችሁ ፈታኝ የሆነው የፈተና ግዜ ከመቸውም ግዜ በላይ ከፊታችን ተደቅኗል ያመነውን እምነት በተግባር የሚፈተንበት ግዜ ቀርቧል ይህ ማለት ምንድነው ክርስትና ፈተና ነው የዘላለምን ህይወት ለሞረስ ተጋድሎ ያስፈልጋል ተጋድሎውም ያስፈለገበት ዋናው ምክንያት ብዛት ሳይሆን ጥራት አምላካችን እግዚያብሔር ስለሚፈልግ ፈተናው የግድ ያስፈልጋል:: ይህንን ያልኩት እኔ ሳልሆን በመጽሀፍ ቅዱሳችን ውስጥ በብዙ ግዜ ተገልጦዋል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳ ምንድነው ያለው “እስከ መጨረሻ የጸና እሱ ይድናል” “በጠባባው በር ለመግባት ተጋደሉ” “መንግስተ ሰማያት ከመግባት ይልቅ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢያልፍ ይቀለዋል” ስለኖነም የእኛ ሰባኪዎች ሲሰብኩን እንደስብከታቸው የሚመስለን ሁሉም የዘላለምን ህይወት የሚያገኙ ይመስለናል ነገር ግን አይደለም የተመረጡ ብቻ:: ስለሆነም ፈተናውን ያዘጋጀው እግዚያብሔር ነው ትምህርቱን ያስተማረው ጌታ ኢየሱስ ነው ፈተናውን የሚፈትነው ዲያብሎስ ነው ፈተናው የሚያቶከረው በሁለት ነገር ላይ ነው እሱም የቃል እና የተግባር ነው የፈተናው ቦታ ባሉበት ይሆናል ወገኖቼ ፈተናውን ለማለፍ ፈታኙን ያፈታተን ጥበብ ለማወቅ እያንዳንዱን የፈታኙን እንቅስቃሴ በጥንቃቄ ማጥናት ያስፈለጋል ምክንያቱም ፈታኙም ዲያብሎስ ጥበበኛና ጨካኝ ነው:: በፈታኙ እንዳይሸወዱ እያሳሰብን የፈታኙን የፈተናውን እቅድ ከእዚህ ጽሁፍ ጀምሮ እንደጌታ ፈቃድ በሳምንት ሁለት ግዜ ይወጣል:: ማሳሰቢያ የዚህን ጽሁፍ ሀሳብ ባያምኑበትም ያንብቡት::! መልካም የእምነት ፈተና ይሁንልን ለሁላችንም ::
የእግዚያብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ በነገር ሁሉ ላይ ጌታ ነው:: !
የእግዚያብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ከነገር ሁሉ ያድናል:: !
ማራናታ !
አሜን ! ጌታ ሆይ ቶ ሎ ና !
በቢንያም መንገሻ May 30, 2014
መግቢያ
በመጀመሪያ ይህን ጽሁፍ ለመጻፍ እንዳውቅ : እንዳስብ : እንዳሰላስል : በመጨረሻ ደግሞ እንድጽፍ ለረዳኝ ለአምላኬ ለአባቴና ለጌታዬ ለሀያሉ እግዚያብሔር በልጁ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አመሰግነዋለሁ:: በማስቀጠልም ስለጨለማው መንግስት ድብቅ ረቂቅ ሴራ በማጋለጥ በቪዲዮ በአለም አቀፍ ሚዲያዎች ሁሉ ላይ የተሰሩትን እና የታቀዱትን የዚህ አለም የሰይጣን ድርጊቶችን በማጋለጥ የሰሩ በተለይ በምእራቡ አለም የሚገኙ ክርስትያን ወንድሞችና እህቶች በተጨማሪ በምእራቡ አገራት ያሉ የክርስትያን ቴሌቪዥን ፕሮግራሞችንና መጽሀፎችን እንዲሁም አንዳንድ ሀሳብ ከወሰድኩበት በአገራችን የሚገኝ ጦማርያን (Blogger) ግደይ ገብረኪዳን የተሸሸጉ ታሪኮች በሚል መጠሪያ ስለ ኢሊሚናቲ ( ስለሚስጢራዊው ማህበር ) የጻፈውን ጽሁፍ እንደ መነሻ ስለጠቀመኝ በጌታ በኢየሱስ ስም ለማመስገን እወዳለሁ እንዲሁም በፌስ ቡክ ለሚገኙ መላው ወዳጆቼ በጌታም ያልሆናችሁትን ጨምሮ ይህንን ሀሳብ ከመጀመሪያው ለማስተዋወቅ የተባበራችሁኝን እንዲሁም ያቀረብኩትን የመገለጥ ማእድ ስለተቋደሳችሁልኝ በጌታ ስም አመሰግናችዋለሁ::
ይህንን የህይወት መጣጥፍ እንድጽፍ ምክንያት የሆነኝ ሙያዬ ነው:: ሙያዬ ነው ለጠቅላላ ግንዛቤ ለአንባብያንና ለወገኖቼ ምን ለማለት ፈልጌ መሰላችሁ እንደሚከተለው ስለ ራሴና ስለሙያዬ ትንሽ አትታለው:: የእኔ ሙያ ጋዜጠኝነት ሲሆን ከሙያዬ ጋር በተገናኘ በዚህች በትንሽ ጌታ በሰጠኝና ባሳየኝ ህይወት ዘመን ከብዙ አይነት ሰዎች ጋር የመገናኘትና አብሮ የመስራት አጋጣሚዎች ነበሩ በህይወቴ እነዚህ ሰዎች ተራ ሰዎች አልነበሩም ማለቴ ስልጣንና ዝና የነበራቸው ሰዎች የነበሩ ሲሆን ምን አይነት ሰዎች ነበሩ ብላችሁ ለምታስቡ የመንግስት ትላልቅ ባለስልጣን : የውጭ ሀገር ዲፕሎማት : የሀይማኖት መሪዎች : የትላልቅ ዩኒቨርስቲ መምህሮች : ታላላቅ ባለሀብቶች : የታላላቅ ድርጅቶች ስራ አስኪያጆች : ታላላቅ የጦር ሹሞች በመዝናኛውም ያሉ አንቱ ከተባሉ ሰዎች ከብዙዎቹ ጋር በስራ አጋጣሚ እገናኝ ነበር ሌላው ቢቀር የውጭ አገር መሪዎችና ታዋቂ የአለማችን ግለሰቦች ለስራም ሆነ አሊያም ለሌላ ጉዳይ ሲመጡ የማግኘት አጋጣሚው ለኔ በጣም ቅርብ ነበረ ይህንን የማወራው እራሴን ልቆልል ሳይሆን ላዘጋጀሁት ማእድ እንደ ግብአት ስለሚሆን ነው:: በእውነቱ ጌታን ካገኘሁበት ይቅርታ ጌታ እሱ እራሱ ካገኘኝ የዛሬ 12 አመት ጀምሮ ላለፉት 10 አመት ያህል የክርስትና ህይወቴ ተራ የነበረ ሲሆን ጌታን ሳልሆን እከተለው የነበረው እራሴን ነበር “ክርስቲያን ሆኜ ሳይሆን ክርስቲያን ተብዬ” እኖር ነበር ምክንያቱም ህይወቴ በውጥረት የተሞላ ነበር ነገር ግን ብዙ ግዜ አይምሮዬ አያርፍም ነበረ በትንሿ የህይወት ዘመኔ ጌታ ለእኔ ብዙ ነገሮችን አሳይቶኛል (ክፉም በጎም) በስራዬ ምክንያት ከሚኒሊክ አስከሬን ቤት እስከ ታላቁ ቤተማንግስት እንዲሁም ከመርካቶ ጉርሻ ምግብ ቤት ( አንድ ጉርሻ 50 ሳንቲም ) እስከ ታላላቆች ሆቴል በተጨማሪ ሽንት ቤት የሽንት ቤት ቆሻሻ በላያቸው እየፈሰሰ ከሚኖሩ ወገኖቼ እስከ የተንጣለለ ታላቁ ቤተ መንግስትን የሚያስንቅ የግለሰብ መኖሪያ አይቻለሁ አይቻለሁ ስላችሁ በማት ደረጃ ሳይሆን ለረዥም ግዜ በመጠቀም ደረጃ ( በነጻ ግብዣ ቢሆንም ) አንዳንዶቹ እንደውም የክርስቲያን ወገኖቻችን መኖሪያ ቤቶች ናቸው:: ወደ ራሴ ስመለስ እንደነገርኳችሁ የስራዬ ጸባይ ሆኖ ብዙውን ግዜ ከትላላቆቹ የአገራችን ፓለቲከኞች ጋር በስራ አጋጣሚ እንገናኛለን ያው እንደምታውቁት ፖለቲካ የዚህች አለም ሞተር ነውና እነዚህ ፖለቲከኞች ያገራችንም ሆነ የውጮቹ እንዲሁም የመንግስትም ሆነ የግል ተቃዋሚ ፖለቲከኞች የሚያወሩልን ስለ ሰላም : ስለነጻነት : ስለ ህግ የባላይነት : ስለእኩልነት : ስለዲሞክራሲና ስለኢኮኖሚ ወዘተ ያወሩልንን ሁሉ በመስማት ያወሩልንን እና ተስፍ የሰጡንን ሁሉ ነገር እኛም በተራችን ነገሩን እውነት እናደርገውና እናቦካዋለን እኛም በተራችን ከተባልነው በላይ አጋነን እናጮኋለን ከዛም እውነቱ በሂደት ሲታይ ሁሉም ነገር ዜሮ ሆኖ እናየዋለን ይህንን ላነሳበት የቻልኩት ዋናው ነጥቤ ምርጫ 97 ሁላችንም የተሳተፍንበት ምርጫ ነበረ ላማለት ይቻላል:: ( ወደ ፓለቲካ ላስገባችሁ ፈልጌ አይደለም ወይም እናንተ እንደምታስቡት ምን ያገናኘዋል ብላችሁ እንደምጠይቁኝ እሙን ነው የዚህ ጽሁፍ ዋና አላማ የዲያብሎስ መንግስት ስውር እጅ በዲሞክራሲ : በሰላም : በእኩልነት : በነጻነት : በህግ የበላይነትና በኢኮኖሚ ስም የሚያካሂደውን መሰሪ አላማና እቅድ እኛንም ስለነካን ነው 97 ምርጫን መነሻ ያደረኩት) በኢትዮጵያ የምርጫ ታሪክ ትልቅ ክስተት እንደነበረ እስከአሁን ድረስ የሚወሳ ታሪክ እንደሆነ የሁላችንም የቅርብ ግዜ ታሪክ ነው:: የተደረገው ምንድነው በምእራባውያን ሀገሮች የገንዘብ ድጋፍ ዝግጅት ተደርጎበት ምርጫው ተደረገ በሚገርም ሁኔታ ከገጠር እስከ ከተማ ገዥው ፓርቲ (ኢህአዲግ) ተሸነፈ ከዛ ያ ሁሉ ሲደሰኮርለት እና በታላቅ ጉጉት ተስፍ ሲደረግ የነበረው ዲሞክራሲ : ነጻነት : ሰላም : እኩልነት : የህግ የበላይነትንና ኢኮነሚ የሚያስገኘው የህዝብ ድምጽ በአንዴ ውሀ በላው:: ከዛም ብዙ አሳዛኝ ክስተት ተፈጠረ የብዙ ንጹሀን ደም በከንቱ በግፍ ፈሰሰ ከህጻን እስከ አዋቂና ሽማግሌና አሮጊት ድረስ ከመንገድ ተለቃቅመው ለተወሰኑ ወራት በወህኒ ኖሩ ስደት መጣ አሸናፊ የፓለቲካ ፓርቲ አመራሮችና ደጋፊዎች ለእስር ተዳረጉ ጋዜጠኞችም ታሰሩ ተሰደዱ ባለንብረቶች ንግድ ቤታቸው ተዘጋ በገጠሩም ያለው አርሶ አደር ይህንኑ እጣ ደረሰው በዛ ሰሞን ብዙ ነገር ሳይታሰብ ተፈጠረ ያ ሁሉ ነገር ሲፈጠር ነገሩ ትክክል እንዳልሆነ በአፋቸው ሲቃወሙ የነበሩ ነገር ግን ውጤት የሌላቸው ጩኅቶች ከየቦታው በርካታ ነበሩ በተለይ ከምእራባውያን ዘንድ ምእራባውያን ያኔ እኔ እንደማውቀው ገዥው መንግስት በተሸነፈበት እንዲያሸንፍ ትልቅ አስተዋጽኦ አድርገዋል:: በተለይ አሜርካን እና እንግሊዝ በምርጫ 97 በተደረገው አላስፈላጊ የሰው ህይወት መጥፋት ከካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውጪ አንድም የሀይማኖት ተቋም ድርጊቱን የኮነኑበት ሁኔታ አልነበረም ካቶሊክም ልትቃወም የቻለችው ተጠሪነቷ ለሮማው ካቶሊክ ላቫቲካን ስለሆነ ብቻና የማስመሰል ተቃውሞ ጭምር እንደሆነ አሁን ላይ በደንብ ተረጋግጦዋል በምን ተረጋገጠ ብትሉኝ ሮማ ካቶሊክ በቀደምት በአለም ላይ በተደረጉ ጦርናቶችና ግጭቶች ጀርባ ሁሌም እንዳለችና አሁን ደግሞ የመጨረሻውን ዘመን አዲሱ የአለም መንግስት (666) እና የአለም አንድ ሀይማኖት መስራችና ዋና የክርስቶስ ተቃዋሚ እንደሆነች ይህንን ጽሁፍ እስከአዘጋጀሁበት ቀን እስከ ዛሬ ድረስ ትላላቆቹ የአለም መገናኛ አውታሮችና የክርስትና የእምነትት ተቋሞች በየግዜው የሚያስተላልፉት ሀቅ ነው:: የእኛዎቹ ቤተክርስቲያኖች ደግሞ ተጠሪነታቸው ለመንግስት እነደሆነ የገባኝ ከምርጫ 97 ጀምር ነው:: ይህ በእንዲህ እንዳለ እነደገና ምርጫ 2002 ደረሰ ገዥው ፓርቲ 99% ቢቻውን ተወዳድሮ አሸነፈ በጣም የደነቀኝ ከምርጫው ቡኅላ ሁሉንም የሀይማኖት መሪዎች ማእከል ያደረገ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያክ በአቡነ ፓውሎስ መሪነትና አዘጋጅነት የአቋም መግለጫ የወጣ ሲሆን የአቋም መግለጫውም ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተሰጣቸውን የህዝብ ድምጽ እንዲቀበሉ የሚያሳስብ የነበረ ሲሆን ምንም አይነት ተሳትፎ በሌለበት ምርጫ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የተሰጣቸውን የህዝብ ድምጽ እንዲቀበሉ መልእክት ሲያስተላልፉ አንድ በቦታው የነበረ የሙያ አጋራችን እንዲህ በማለት አቡነ ጳውሎስን ጠየቃቸው እናንተ በምርጫ 97 ያን ሁሉ ነገር ሲፈጸም ዝም ብላችሁ ምንም በሌለበት በእዚህኛው ምርጫ አሁን እንዲህ ስትሉ ትንሽ አይከብዳችሁም ወይ ብሎ ቢጠይቃቸኧው አቡነ ጳውሎስ ዛራቸው የተነሳ ያክል ተነሱ ተውረገረጉ “አረ ብንልስ ብንልስ ገና ብዙ እንለን ገና” አሉ በጣም ተናደው ያው የሳቸው አጃቢዎች ዋነኞቹ የእኛዎቹ ትላልቆቹና አንጋፋዎቹ እረኞች ነበሩ በዛን ግዜ አሁንም አሁንማ ብሰዋል ሁሉም አንድ ሆነዋል:: ከምርጫ 97 ቡሀላ ስለ ነጻናት : ዲሞክራሲ : እኩልነት : አንድነት : የህግ የበላይነትና ኢኮኖሚ ከላይ እንዳልኳችሁ ፕሮፓጋንዳ ብቻ ሆኖ ቀራ ብዙ ግዜ ለምንድነው ምእራብያኖች ለሚጨቁኑና ለሚበድሉ የአፍሪካ መሪዎች እገዛ የሚያደርጉት? ለምንስ ነው የስልጣን ዘመናቸውን የሚያራዝሙላቸው? ለምንስ ነው 90 % በላይ ህዝብ የመረጠውን 19 97 የምርጫ ውጤት እንዲቀለበስ ያደረጉት? ለምንስ ነው በተደረገው የሰብአዊ መብት ጥሰት አጸፋውን እርምጃ ያልወሰዱት? እና ሌሎችንም የእራሴን ጥያቄ ይዤ እኔም ከሀገር ወጣው:: ከአገር ከወጣው ቡሀላ እዚህ የምእራብያኖቹን አገር ህግ ማወቅ የግድ ስላለብኝ ህጎቹን ስማራቸውና ሳውቃቸው 100% በእግዚያብሔር ህግ ላይ የሚጻረሩ የአመጻ ህግ ተደንግገዋል:: በቤተክርስቲያን እንኳ ሳይቀር በዚህ ህግ ተጠቂዎች ሆነዋል ለምሳሌ የባልና የሚስት ህግ ስልጣን ለሴት ነው : ባል በአረገዘች ሚስቱ ጽንስ ላይ ስልጣን የለውም : በወላጆች በልጆች መሀከል ስልጣን ለልጆች ነው : ስለሰዶማውያን አጸያፊነት መስበክም ሆና ባደባባይ ማስተማርም አይቻልም : እኔ ባለሁበት አገር እንኳ የክርስቲያን ቤተክርስቲያን መሪዎች ጌይ እና ሌዚቢያንስ እንደሆኑና ትልልቅ የጌይና የሌዚቢያንስ ፕሮግራሞች ቤተክርስቲያን ውስጥ ፕሮግራም ይደረጋሉ : ልጆች ሴት ልጅ በ16 አመቷ ወንድ ልጅ 14 አመቱ በጾታዊ የግብረ ስጋ ግኑኝነት አንዱና ዋነኛው መዝናኛ እነደሆነ በማስተማር በተለያየ ዘዴ ይቀሰቀሳሉ ሌላ ለመዘረዘር የሚያስቸግር አስጸያፊ በእግዚያብሔር ህግ ላይ የአመጻ ህጎች አሉ:: ይበልጥ ህጋቸውን እያወቅኩ ስመጣ በጣም ያመኝ ጀመር ያው ከመነሻው እንዳልኳችሁ ከዛሬ 12 አመት በፊት ጌታን ባገኘውም ይቅርታ እሱ ነው ያገኘኝ የመገለጥ ብርሀን አልበራልኝም ነበር በደመ ነፍስ ነበር ስኖር የነበረው የመገለጡ ብርሀን ካገኘኝ ከአገር ከወጣው ቡኋላ ነበር ያገኘሁት ከአገር እንደወጣው አካባቢ መንግስትን በተለያየ ነገር ማለትም በሰብአዊ መብት : በነጻነት : በህግ የበላይነት : በእኩልነትና በኢኮኖሚ እቃወም ነበር ከዛም አልፎ ስልጣን መልቀቅ አለበት ብዬ እዚህ ከምራባውያን አገር ካሉ ተቃዋሚ ፓርዎች ጋር በማበር እንደመጣው እቃወም ነበር ታዲያ በእዚህ ሁኔታ ላይ እያለሁ ብዙ ግዜ አለም አቀፉ ታላላቆች መንግስት በኢትዮጵያ ስላለው መንግስት ምን ይላሉ ብዬ መረጃ ስሰበስብ ታላላቆቹ ሀያላን መንግስት ሁሉ እኛ ከምንገምተው በላይ አሁን ስልጣን ላይ ያለው መንግስት እንደሚደግፉት ከተለያየ አለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሀን በመረጃ ደረስኩበት ከእዛም ሁሉን ወደ ሚያውቀውና ወደሚችለው አምላክ ወደ እግዚያብሔር ቃል ዞርኩኝ የእግዚያብሔር መንፈስ ረድቶኝ ፊቴን ወደእግዚያብሔር ቃል ስለ መለስኩኝ በመጀመሪያ ወደ አይምሮዬ የመጣው የእውነት የጌታ ቃል “እኔ የምሰጣችሁ ሰላም አለም እንደሚሰጣችሁ አይደለም” የሚለው ሲሆን የዚህ ቃል የመገለጥ ፍቺ ሲበራልኝ በአለም ላይ ሁለት አይነት ሰላም አለ 1ኛው የእግዚያብሔር ዘላለማዊው ሰላም በጌታ ኢየሱስ በኩል የምናገኘውና 2ኛ የሰይጣን ጊዚያዊ ሰላም በአለም በኩል የምናገኘው እንደሆነ በራልኝ:: በጌታ ኢየሱስ የሚገኘው ዘላለማዊው ሰላም ምንም የማይከፈልበት ሲሆን በአለም የምናገኘው ጊዚያዊው ሰላም በብዙ ሚሊዮን የሰው ህይወት ና በብዙ ትሪሊያን ዶላር ከዛም በላይ ዋጋ ይከፈልበታል:: ይህ ሁሉ ውድ የሰውና የገንዘብ ክፍያ ተከፍሎበትም ብዙ ግዜ የሚፈለገው ሰላም አይመጣም መንፈስ ቅዱስ ይህንን አበራልኝ:: የበደል ጭቆና ስርአት ለውጥ የሚመጣው ወደ እግዚያብሔር ሲቀርብ ብቻ እነደሆነ ከእግዚያብሔር ቃልም ከተሞክሮም ካገኘዋቸውና ካጠናዋቸው መረጃዎች ለማወቅ ችያለሁ በተጨማሪ በአመጽና በጦርነት ሀይልን ማምጣት ይቻላል ነገር ግን የዚህ ሀይል ባለቤት ዲያብሎስ እንደሆነ መጽሀፍ ቅዱሳችን ይነግረናል:: “የዓመፅ ምሥጢር አሁን ይሠራልና፤ ብቻ ከመንገድ እስኪወገድ ድረስ አሁን የሚከለክል አለ። በዚያም ጊዜ ጌታ ኢየሱስ በአፉ መንፈስ የሚያጠፋው፥ ሲመጣም በመገለጡ የሚሽረው ዓመፀኛ ይገለጣል፤ ይድኑ ዘንድ የእውነትን ፍቅር ስላልተቀበሉ ለሚጠፉ፥ የእርሱ መምጣት በተአምራት ሁሉና በምልክቶች በሐሰተኞች ድንቆችም በዓመፅም መታለል ሁሉ እንደ ሰይጣን አሠራር ነው።” 2 ተሰሎንቄ 2:1-2
ወደ ዋናው ለእናንተ ወዳዘጋጀሁት ጽሁፍ ሀሳብ ስመለስ ይህ 2 ተሰሎንቄ 2:1-2 እና እራሱ ጌታ ኢየሱስን ለ 40 ቀን እና ሌሊት የፈተነው ዲያብሎስ ጌታችንን ያለው ምንድነው የአለምን ነገስታት ክብራቸውን አሳይቶት ወድቀህ ብትሰግድልኝ ይህንን ያሳየሁህን ስልጣን ለአንተ እሰጥሀለው :: ማቴ 4: 9 ይህ ማለት ምንድነው የንግስና ስልጣንና ሹመት በእዚህች ምድር ላይ ከዲያብሎስ እንደሆነ ከእዚህ ክፍል የምንማር ሲሆን የመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ ደግሞ በብዙ ቦታ የዚህ አለም ገዥ የሆነው ዲያብሎስ እንደሚያስተዳድር ይናግረናል:: የእዚህ አለም ገዥ እንዴት ነው አለምን እያስታዳደረና ወደ ዋናው ወዳዘጋጀው መንግስቱ የሚያስገባው ከተባለ የዚህ ጽሁፍ ዋነኛ አብይ ጉዳዩ እሱ ይሆናል :: እኔ የጽሁፌን አርእስት “ስውሩ እጅ” ቢዬዋለሁ የዲያብሎስ ልጆች ደግሞ NEW WORLD ORDER (አዲሱ የአለም መንግስት) NEW WORLD GOVERNANCE (አዲሱ የአለም አስተዳደር) ONE WORLD RELIGION ( አንድ የአለም ሀይማኖት) ILLMUINATI (ኢሊሚናቲ የቃሉ ፍቺ ላቲን ሲሆን ትርጉሙም የተሸሸገ እውቀት መግለጥ ማለት ነው ይህ ማለት ምንድነው ሄዋን ለመታለሏ ምክንያት የሆነ የዲያብሎስ ማሳሳቻ “ኢሉምናቲ” እባብም ለሴቲቱ አላት። ሞትን አትሞቱም፤ከእርስዋ በበላችሁ ቀን ዓይኖቻችሁ እንዲከፈቱ እንደ እግዚአብሔርም መልካምንና ክፉን የምታውቁ እንድትሆኑ እግዚአብሔር ስለሚያውቅ ነው እንጂ። ዘፍ 3:4_5)
የዚህ ጽሁፍ ዋና አላማ ሊመጣ ካለው የዚህ ዘመን መጨረሻ ፈተና ከሀሰተኛውና ከጨካኙ ከዲያብሎስ ፈተና እንድናመልጥና ወደ ክርስቶስ መንግስት ለመግባት ለመዘጋጀት እንዲረዳ የታሰበ ነው ምን ለማለት ፈልጌ ነው ያለንበት የመጨረሻው ዘመን እንደሆነና ሀሰተኛው ክርስቶስ መምጫው እንደ ደረሰ እንዲሁም የዲያብሎስን ረቂቅ አሰራር በማወቅ ሊደርስብን ከሚችለው መንፈሳዊ ውድቀት ለመዳንና ሊመጣ ያለውን ክፋትና ስቆቃ እንዴት እንደምናውቀውና ወደ እግዚብሔር መቅረቢያችን ሰአቱ እነደሆነ ለማስገንዘብና የጠላታችንን የዲያብሎስን እንቅስቃሴ ለማጥናት ይጠቅመናል:: በምእራቡ አለም ያሉ የእግዚያብሔር እረኞች የግዜው ትምህርት ይህ ነው እኛ ጋር ስንመጣ የእኛ አገሮቹ አቃቤ እረኞቻችን በማወቅም ይሁን በንቀት አሊያም ባለመገለጥ ሀሳቡን ሊያጣጥሉት ይችላሉ :: ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱሳችን ስለዚህ የዲያብሎስ መንግስት አስረግጦ ይነግረናል በጽሁፉ ማለቂያ ላይ የመጽሐፍ ቅዱስ እይታ በመጨረሻው ዘመን በሚመሰረተው የዲያብሎስ መንግስት የሚናገረንን የዚህ ጽሁፍ መጨረሻ ለአንባቢዮቼ እንዲረዱት ለመዳን አቀርባለሁ ሌላው የምናግራችሁ አሁን ባለንበት በመጨረሻው ዘመን አብዛኞቹ የእኛ አገር ሰባኪዎች በተሳሳተ ግንዛቤ ይሁን ምእመናው ከጉባኤ እንዳይጠፋባቸው አላውቅም በመጨረሻ ዘመን በህይወት ያለን እንነጠቃለን : ጌታ በትንሳኤ ያስነሳናልና ጌታ በመለአክ ያጅቦ መጥቶ ይወስደናል:: ይህ የሚሉት የታመነ እውነት ነው:: ነገር ግን ሁሉም አይደለም የሚነጠቀው : የትንሳኤ ህይወት የሚያገኘው : ከጌታ ጋር የዘላለምን ህይወት የሚያገኘው:: እዚህ ነገር ላይ እረኞቻችን ሊያጤኑበት የሚገባቸው ቦታ ነው የህይወት ጉዳይ ነው እንጂ የሐይማኖት ስርአት ጉዳይ ወይም የመልካም ምኞት መግለጫ አይደለም ጌታ እራሱ ምንድ ነው ያለው “በጠበበው በር ለመግባት ተጋደሉ” ተጋሎ ምንድ ነው ጦርነት ነው ይህ ጦርነት ከባድ ነው ምክንያቱም መንፈሳዊም ስጋዊም ውጊያ ስላለበት ስለዚህ ያለማመቻመች የእኛ እረኞች በግልጥ እንኳ ቢፈሩ በስውር እውነተኛውንና የሚዳንበትን ተጋድሎ ቢያስተምሩ ይሻላቸዋል ያለበለዚያ እኛን ሲያቃጥላን እነሱን ይለበልባቸዋልና:: ምክንያቱም ሌላው ቢቀር 666 ምልክቱን መቀብል በምድረ አሜርካን ሀገር ተጀምሮዋል እንደፕሬዚዳንት ኦባማ አባባል የአሜርካ ህዝብ እስከ 2017 ድረስ ምልክቱን ተቀብለው መጨረስ እንዳለባቸው አሳስበዋል ከዚያም በመቀጠል እሳቸው ያሉት ምንድ ነው 30 ቢሊዬን ማይክሮ ችፕስ በ IBM በኩል ተመርቶ በተባበሩት መንግስታት አማካኝነት ለአለም ይሰራጫል መቼ ከ 2017 ቡኋላ ሌላው ደግሞ በአለም ላይ የሮማ ካቶሊክ በአለም ላይ የምታደርገውን እንቅስቃሴ በዋናነት ሊጤን የሚጋባው ጉዳይ እንደሆነ ብዙዎች በውጭ ያሉ የእምነት ሰዎችና ቤተክርስቲያኖች እያሳሰቡት ያለ ጉዳይ ነው:: አሁንም በአንክሮ የማሳስበው ጉዳይ ይህ ጽሁፍ አላማው የጠላታችንን የዲያብሎስን መሰሪ አላማ : እቅድና ሴራ የምናውቅበትና ካወቅንም ቡሃላ ሐዋርያው ቅዱስ ፓውሎስ ያስተላለፈውን ትእዛዝ በመጽሐፍ ቅዱሳችን እንዲህ ይላል::
“የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ። መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ። ስለዚህ በክፉው ቀን ለመቃወም፥ ሁሉንም ፈጽማችሁ ለመቆም እንድትችሉ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ አንሡ። እንግዲህ ወገባችሁን በእውነት ታጥቃችሁ፥ የጽድቅንም ጥሩር ለብሳችሁ፥ በሰላም ወንጌልም በመዘጋጀት እግሮቻችሁ ተጫምተው ቁሙ፤በሁሉም ላይ ጨምራችሁ የሚንበለበሉትን የክፉውን ፍላጻዎች ሁሉ ልታጠፉ የምትችሉበትን የእምነትን ጋሻ አንሡ፤የመዳንንም ራስ ቁር የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው።በጸሎትና በልመናም ሁሉ ዘወትር በመንፈስ ጸልዩ፤ በዚህም አሳብ ስለ ቅዱሳን ሁሉ እየለመናችሁ በመጽናት ሁሉ ትጉ::”
ኤፌ 6:11-18
ይህ ጽሁፍ በጠቅላላ ወደ 35 ገጽ አካባቢ ይሆናል ነገርግን በሳምንት 2 ግዜ 6 ገጽ እያደረግኩ ለእናንተ ለውድ ወገኖቼ አቀርባለሁ ተከታታይ ጽሁፎችን ለማግኘት ፌስ ቡኬ ላይ ታግ አደርጋለሁኝ እናንተም ለወገኖች ሼር በማድረግና አስተያየት በመስጠት እንድትተባበሩኝ ስል በጌታ ስም እጠይቃችዋለሁ::
ማሳሰቢያ
ይህንን የመጨረሻውን የአለም መንግስት ምስረታ በማስመልከት የሚወጡትን አለም አቀፍ ዜናዎች : ድርጊቶችና ጥናታዊ መረጃዎች እስከ ዛሬ ድረስ ያለውን እናንተ አንባቢዮቼ እንዲረዳችሁ በማሰብ የዩቲዩብን ሊንክ አያይዤ አቅርቤያለሁ
New World Order Declared (666): Obama’s New America Will Implement Martial Law! Shocking, Stunning, Scary Video/ http://youtu.be/WahMK5NFpc8
ObamaCare: Mandatory Microchip Implant for all Americans!!!/http://youtu.be/ObA3OIo8_94
Obamanation : House hearing looks at the President's growing/http://youtu.be/DcPMMuTxva8
Is Barack Obama THE ANTICHRIST? 100% PROOF Is There!/http://youtu.be/rhnQ_ESpvuo
Hidden Messages in New $100 Dollar Bill?/ http://youtu.be/ut6tsUuajlo
Decoding the Past - Secrets of the Dollar Bill/ http://youtu.be/yUD4vTW5SS4
Illuminati 2014: Predictions!! We must reach mass awareness!/http://youtu.be/slanahLcIHY
Illuminati 2014 End of the World Conspiracy Predictions/http://youtu.be/39btKqMiqiQ
OBAMA'S ALIEN SECRET SERVICE spotted at 2012 AIPAC Conference/http://youtu.be/Tb8mU_g_f2w
His NAME and MARK Revealed ANTICHRIST 666 The Mark Of /http://youtu.be/OLR7x0l2BzE
The most dangerous Barack Obama video ever!!!/http://youtu.be/4Yro63c7B7A
Final Warning - %100 Proof Pope Francis I Antichrist 666 Obama/http://youtu.be/s_K-OsxiNqQ
POPE Francis New Controversy to ERUPT ----- BILLIONS to die./http://youtu.be/bP__nMYqyjo
What Will Happen To Israel In 2014? & 2015? THE 4 BLOOD/http://youtu.be/LClvrDFQWBw
WikiLeaks : LEAKED - U.N. Briefing On Alien God Arrival/http://youtu.be/OAlq0maKf2o
THE END OF AMERICA 2014-2016: "IT'S WORSE THAN YOU/http://youtu.be/Rc3QezVTQ20
Watch this and you will know we're in END TIMES!/http://youtu.be/t6WVZJ_CFHQ
GREY ALIENS CAUGHT ON TAPE (VERY SCARY!!)/http://youtu.be/_ECjO46EUp4
አዲሱ የአለም መንግስት (666)( New World Order or New World Govermant )
አዲሱ የአለም መንግስት ( New World Order ) ሲቋቋም ዋና አላማ ያደረገው ቤተክርስቲያኖችን በመቆጣጠርና በቁጥጥሩ ስር በማድረግ ከነበረው የእግዚያብሔር ተፈጥሮአዊ የህይወት ህግ መንገድ በተቃራኒው ማስጔዝ ሲሆን አላማውም ቤተክርስትያንን እና በእግዚያብሔር የሚያምነውን ህዝበ ክርስትያንን የከፋ ስቃይ በማድረስ ከአምላኩ ከእግዚያብሔር በመለየትና ወደ ራሱ መንግስት በማምጣት በእግዚያብሔር መንግስት ላይ አመጻ ማድረግ ሲሆን ይህንንም እኩይ ተግባር ጠንካራ እቅድ እና ፕላን ወጥቶለት በስራ ላይ ከዋለ ከፍጥረት ጅማሮ ከዘመነ አዳምና ሄዋን ጀምሮ አሁን ወደ መቋጫው ጫፍ ለመድረስ ጥቂት የሚባሉ ግዜያቶች ቀርተውታል :: ይህ አዲሱ መንግስት ሲቋቋም ሚስጥራዊ እና በረቀቀ ዘዴ የተቋቋመ ሲሆን የአመሰራረቱ ታሪክ በጣም ውስብስብ እና በጥቁር መጋረጃ ባሉ እርኩሳን መናፍስት በመታገዝ በአለም ላይ ባሉ ሀያላን ሰዎችና የአገር መንግስታቶች :ባለሐብቶች :ትላላቅ የሐይማኖት አባቶች :ትላላቅ ግዙፍ ተቋሞች :በአለም ላይ ያሉ ታዋቂ ሰዎች : በአለም ላይ ያሉ ታዋቂ መገናኛ ብዙሀኖችን (ሚዲያዎን) መሰረት ያደረገ መሆኑ ደግሞ በእዚህ ዘመን ያለን ክርስቲያኖች በንቃት እያንዳንዱን በእዚህች አለም ላይ የምትደረገዋን እንቅስቃሴዎች በጥንቃቄ መከታተል ይኖርብናል:: ምክንያቱም አዲሱ የአለም መንግስት የሚመሰረተው እኛን የኢየሱስ ክርስቶስን ተከታዮችን ለማጥፍትና የመጨረሻው ዘመን የክርስቶስ መንግስት ተቃዋሚና የዲያቢሎስ የጨለማው ሀይላት መንግስት መመስረት መሰረት ያደረገ ስለሆነ ነው::
አዲሱ የአለም መንግስት 666( New World Order ) አመሰራረት
አዲሱ የአለም መንግስት ( New World Order ) አመሰራረቱ በጨለማ ሀያላን መንፈስ ድብቅ ሴራና አጀንዳ የያዘ የአመጻ መንግስት ሲሆን የተመሰረተውም በወደቁ የእግዚያብሔር መልአክት ከሰው ልጆች ጋር በመዋለድ የእነሱ ዘሮች የሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ኒፍሌምስ የሚላቸው የወደቁ የእግዚያብሔር መልአክት ዘሮች ሲሆኑ እነዚህ የወደቁት መላክቶች ( ኒፍሌምስ ) ለመልአክት ብቻ የተሰጠውን ጥበብ እና እውቀት ለወለዱአቸው የሰው ልጆች እና የልጅ ልጆች በመስጠትና በማውረስ የዚህ አለም የሰው ልጆች መጥፊያ እና ማጕዋጉዊያ የሆነውን ከንቱ አለም ማስመለክ ዋና አላማ ያደረገው የዚህችን የዓለም ነገር ባለቤት:የጥፋት ፈጣሪ እና የጥበብና እውቀት ባለቤቶቹ እነዚሁ የወደቁ መላእክ ዘሮች እንደሆኑ ብዙዎች የመጸሐፍ ቅዱስ አጥኝዎችና የታሪክ ተመራማሪዎች በተለያዩ ግዚያቶች ባቀረቡዋቸው ጥናታዊ ጽሁፎች ለመረዳት ተችሏል:: እንዲሁም በተጨማሪ የእነዚህን የወደቁትን መላእክት ህይወት የሚያሳየው የመጸሀፍ ክፍል ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንዳይካተት ከተደረጉት አንደኛው የሆነው መጽሐፈ ሔኖክ ስለ እነዚህ ስለ ወደቁት መላእክት በደንብ ማብራሪያ ይሰጣል ይላሉ የመጽሐፍ ቅዱስ አጥኚዎች እነዚህ የወደቁ መላእክት ዘሮች ከ 18 ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ጀምሮ እራሳቸውን ከአለም በማግለል እራሳቸውን ኢሊሚናቲ (Illuminati) ሚስጥራዊ ተቋም (secret society) በማቋቋም አሁን በእዚህች አለም ላይ ሁለንተናዊ የሆነ ለውጥ በፖለቲካ : በባሀል : በሐይማኖት : በኢኮኖሚ በሁሉም አቅጣጫ አለምን ፊት ለፊት የያዙ ሲሆን ለእኛ ደግሞ ለክርስቶስ ተከታዮች እጅግ የፀና የፈተና ግዜ እንደሆነ እኛ ክርስትያኖች በደንብ አስተውለን ለመረዳት ግዜው አሁን እንደሆነ ከሚታየውና ከሚሰማው እንዲሁም በመጽሐፍ ቅዱስ ከተነገሩት የመጻኢ ትንቢቶችና የዘመኑ መጨረሻና የጌታ ኢየሱስ መምጫ ግዜ እንደሆነ ለመረዳት ይቻላል:: አሁን በእዚህ ዘመን የምናያቸውና የምንሰማቸው የቴክኖሎጂ ምጥቀት ሳይንሳዊ ፈጠራ ውጤት የእነዚህ የወደቁት መላእክት ዘሮች እንደሆኑ ብዙዎች የመጽሐፍ ቅዱስ አጥኝዎች ይናገራሉ::አብዛኞቹ የዚህች አለም ሳይንሲስቶች : ፈላስፋዎች : የአገር መሪዎች(የእኛን አገሮችን ይጨምራል) :ቤተክርስትያን : የሐይማኖት አባቶች(የኛዎቹም የሀይማኖት አባቶች ይጨምራል) : ባለሀብቶች : ታዋቂ ተቋሞች እና ታዋቂ የአለማችን ግለሰቦች የእዚህ ሚስጥራዊ ማህበር አባሎች ናቸው ይባላል:: እነዚህ ግለሰቦች መፈክራቸው ሁሌም ሳይንስ የሰው ልጅ ጭንቅላት የፈጠረው ጥበብ ነው:: እንጂ ከእግዚያብሔር አይደለም እግዚያብሔር ያሚባል አምላክ የለም በማለት ለዘመናት በክህደትና በሀሰት መንፈስ አማካኝነት በአለም ላይ ባሉ ህዝቦች ነብስ ላይ ሲጫወቱበትና ሲያሳስቱት ሲያወናብዱት እውነት የመሰለው የሰው ልጅ ለዘመናት ሳይንስን ተምሮና አውቆ እነሱን ለመከተልና እንደ እነሱ ለመሆን ያልቦዘነበት ግዜ አለ ለማለት አያስደፍርም እውነቱ ግን ሌላ ነው ዛሬ አለም የሚቋምጥለት ሳይንስ ጥበብ ባለቤትነቱ እግዚያብሔር ሲሆን ለክህደት እና ለክፉ ስራ ያዋሉት ደግሞ እነዚያ የወደቁ መላእክትና አሁን በምድር ላይ ያሉ የነሱ ዘሮች ናቸው ይሉናል በእዚህ ላይ ጥናት ያደረጉ ሰዎች::የወደቁ መልአክት ዘሮች እስከ አሁን ድረስ በምድር ላይ እንዳሉ ብዙዎች የመጽሐፍ ቅዱስ አጥኝዎች ይናገራሉ::የወደቁ መልአክት በአሁኑ ግዜ ዘሮቻቸው በኢራቅ በአውሮፓ:በእስካንዲቪያን:በጀርመን:በፈረንሳይ እና በታላቋ ብሪታንያ በእንግሊዝ እንዳሉ የሚገመት ሲሆን የእንግሊዝ የቀድሞ ስያሜዋንም (Engel - land)የመልአክት ምድር ያገኘችውም በእነዚህ በወደቁ መላእክት ነው ይሉናል አጥኚዎች:: እንግሊዝ የአሁኑዋን ስያሜ ኢንግላንድን መጠሪያ ስያሜም ያገኘችው ከቀድሞው ስያሜዋ በመነሳት ሲሆን ይህ ስያሜ ከየት መጣ ከተባለ የወደቁት መላእክቶች ከብዙ ዘመን በፊት በእስኮትላንድ ይኖሩ እንደነበረና እስከ አሁን ድረስ የእንግሊዝና በስውዲን:የንጉሳውያን ቤተሰብ እና ጀርመኖችም እንዲሁም በታላቋ አሜርካ በትላላቅ ተቋዋሟቶቿ ቁልፍ ቦታ የእነዚህ የወደቁ የመላእክ ዘሮች መሆናቸውንም ይናገራሉ አጥኝዎቹ::የወደቁ መልአክት ዘሮች እራሳቸውን እንደፈለጉ መለዋወጥ የሚችሉ ሲሆን ለአምልኮ ሲሰበበቡ እራሳቸውን በእባብ:በዘንዶ እና በድራጎን ይለውጡታል:: ለእዚህም በታላቋ ኢንግላንድ ዋና ከተማ በብዙ ቦታ የድራጎን እና የወደቁት መልአክት ሀውልት በብዛት ይታያል እነዚህ የድራጎን ሀውልቶች እንዲሁ በአሜርካን ሀገር በዋና ከተማዋ ዋሽንግተን ኮሎምቢያ ውስጥ ይገኛሉ:: ለእዚህ ነው ብዙውን ግዜ በአለም ጠቅላላ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ሁኔታ ላይ እነዚህ ሁለት ሀያላን አገሮች እንግሊዝ እና አሜርካን በአንድ ልብ ሆነው ተዋደው ሁለቱም አንድ አገር እስከሚመስሉ የጠለቀ አንድነት ያላቸው ታላቋ ብሪታንያ እንግሊዝ ሌላው መጠሪያ ቅጽል ስሟ (መፈክሯ ) በእንግሊዝ ምድር ላይ ፀሀይ አትጠልቅም ብላ እራሷን ያሳወቀች ሲሆን ይህ ማለት ምንድ ነው እራሱን በብርሀን የሚመስለው የሉሲፈር(ዲያቢሎስ)መፈክር መሆኑና እንግሊዝ የወደቁ መላእክት መኖሪያና መመለክያ ሀገር ነች ለማለት በእርግጥ ያስደፍራል::
ስለ ኒፍሌምስና ስለ መጻፈ ሔኖክ ታሪክ የሚያወሳውን ጥናታዊ ዶክመንተሪ ፊልምን ለማግኘት እነዚህን ሊንክ መጠቀም ይችላሉ ይችላሉ::
http://www.youtube.com/watch?v=BZGN6EKjvAo&list=PLde7MpiJoARushEWtiNILLHeM19TVR3IR&feature=share&index=3
http://youtu.be/atxGNYrBftI
http://www.youtube.com/watch?v=DU_u7qxYhlg&feature=share&list=PLde7MpiJoARushEWtiNILLHeM19TVR3IR
አዲሱ የአለም መንግስት ኢሊሚናቲ (Illuminati)
ኢሊሚናቲ (Illuminati) የቃሉ ትርጉም በላቲን ከእኛ የተሰወረ እውቀት ማለት ሲሆን::ይህ የተሰወረው እውቀት ምንድ ነው? ከተባለ እውቀት በሚመስል ማሳሳቻ ከአዲሱ የአለም መንግስት በስተጀርባ በጥቁር መጋረጃ ውስጥ ያለ ስውር ሴይጣናዊ እጅ ሲሆን የእዚህ ማህበር መስራች በ ግንቦት1/1776 ዓ.ም በአዳም ዉሻፕት የተመሰረተው ይህ ማህበር በመንፈሳዊና ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ የሚስጥር ማህበራት የነበረውን ልዮነት የደመሰሰ ነበር፡፡ የፍሪሜሶኖችንና የሮዚክሩሽያኖችን የባእድ የሰይጣናዊ ሳይንሶችን በመቀላቀል በሌላ እጅ በዝርዝር የተቀመጡ ሀይማኖታዊ እና ፖለቲካዊ ግቦችን ለማሳካት በማሴር ኢሉሚናቲ በዓለም መድረክ ዋና ተዋናይ ሆነ፡፡ በግዜው የነበሩ የሚስጥር ማህበሮች ከባእድ ሰይጣናዊ እውቀቶችና ሃብታም ሰዎች ዙርያ ሲያንዣብቡ የባቫርያ ኢሉሚናቲ ዓለምን ለመቀየርና ወደ አንድ መንግስት ለማምጣት በትጋት ይሰራ ነበር፡፡ የሚስጥር ማህበራት በታሪክ በተለያዩ ወቅቶች የተለያዩ ዓላማዎች ይዘው ተነስተዋል፡፡ የጥንታዊ ግብፅ የሚስጥራት ትምህርት ቤቶች የግብፅ አስተዳደራዊ ተቋም አካላት ነበሩ፤ ሌሎች ቡድኖች በአመፅ አላማቸውና ሴረኝነታቸው ሳቢያ ሚስጥራዊ ነበሩ፡፡ የመጀመርያው የመንፈሳዊ ገፅታ ሲሆን ሁለተኛው ፖለቲካዊ ገፅታውን የሚያሳይ ነው፡፡ የባቫርያ ኢሉሚናቲ በሁለቱም መስመሮች የሚንቀሳቀስ ነበር፡፡ “መንፈሳዊ ወንድማማችነት ቃል የሚገቡት ለጥበብና የሰው ልጆችን መጨረሻ ወደሌለው አካል ለማምራትና አዲስ የሆነ የአለም መንግስትን እንዲሁም የክርስቶስ ተቃዋሚን የሰይጣኒዝምን ሀይማኖትን ማምጣት ነው፤ ፖለቲካዊ ወንድማማችነትንና እውቀትን የሚያካትቱት የማታለያ አጀንዳቸውን በጭለማ ሀያላን ነፍሳት ስልጣን የሚጋርዱ የዲያብሎስ መሰሪ እቅድ ስብስብ ነው፡፡በፖለቲካዊና ሀይማኖታዊ የሚስጥር ማህበር ቡድኑ የሚወክላቸው ርእዮተ ዓለሞች ጋር ለሚስማሙ ቡድኖች ብቻ የሀይል ሚዛኑ ያጋደለ ነው፡፡ ከፖለቲካዊ አድማሱ የመጨረሻው አላማ መንፈሳዊ አብዮትን ማስነሳት ነው፡፡ እንዲህ አይነት ማህበር ራሱን ለማግዘፍ በጥንቃቄ : በጥበብ : በሀይል : በኢኮኖሚ ይጓዛል:: በስተመጨረሻ አንድ አለም አንድ ቋንቋ : አንድ ህዝብ : አንድ አዲስ መንግስት እና አንድ ሀይማኖት ኢሊሙናቲ 666 (Illuminati)፡፡

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen