Netsanet: “ፀሎታችን በቤታችን”

Freitag, 20. Juni 2014

“ፀሎታችን በቤታችን”

June 19, 2014 

የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች የፀሎትና መቃብር ስፍራ ጥያቄ በሳውዲ አረቢያ
comnity jedd

በተለያዩ ግዜያት ህጋዊ እና ህገወጥ በሆነ መንገድ ተሰደው ወደ ሳውዲ አረቢያ ከሚገቡ ኢትዮጵያውያን መሃከል ጥቂት የማይባሉ  የኦርቶዶክ እምነት ተከታይ ወገኖቻችን የህዝብ ሙስሊሙን ሃይማኖታዊ ደንብ እና ስረአት  አክበረው እንደሚኖሩ ይታወቃል። እነዚህ በሃገሪቱ ግዛቶች ሪያድ፣ ጅዳ፣ ደማም እና ጅዛን በሚባል ክፍለ ግዛቶች ውስጥ በተለያዩ ስራዎች ላይ ተሰማርተው እንደሚኖሩ የሚነገረው የእምነቱ ተከታዮች በደስታም ሆነ በሃዘን ግዜ ሃይማኖታቸው የሚያዘውን የፀሎት ስረአት ሃይማኖታዊ ወግ እና ስረአት ጠብቀው ለፈጣሪያቸው ጸሎት ማድረስ እንደማይቸሉ የሚገልጹ ምንጮች ሳውዲ አረቢያ በእስላማዊ ህግ የምትመራ እንደመሆኗ መጠን ሌሎች ሃይማኖቶችን ማራመድ በጥብቅ የተከለከለ በመሆኑ በመንግስት ዘንድ በይፋ ከሚታውቀው ሃይማኖት ውጭ ምንም አይነት አማራጭ የጸሎት ስፍራዎች ባለመኖራቸው  በኢትዮጵያውያኑ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ወገኖቻችን ላይ ከፍተኛ መንፈሳዊ ተጸዕኖ እንዳሳደረባቸው ይነገራል።
እንደ ኢትዮጵያውያኑ በሳውዲ አረቢያ የሌላ እምነት ተከታይ ወገኖች እንዳሉ የሚጠቅሱ ምንጮች እንደ ፊሊፒንስ፣ ኔፓል፣ ህንድ፣ ወዘተ የክርስትና እምነት ተከታይ እና ሌሎች መንፈሳዊ እምናተ ተከታይ  የውጭ ሃገር ዜጎች በኤምባሲያዎቻቸው በኩል በሚደረግላቸው ሁለንተናዊ ትብብር እና ድጋፍ ህይወቱ ያለፈች ዜጋን አስክሬን ተባብረው ለሃሀገሩ አፈር ሲያበቁ ከፈጣሪው ተማጽኖ የራቀውንፈሪሃ እግዚአብሄር  በየሃገሮቻቸው ኮሚኒቲ ተቋማት ሰር ተሰባስቦ በሳምንት አንዴ «ከፈጣሪው ጋር ተገናኝቶ» ፀሎት የሚያደርስበት ስፍራ እንደተዘጋጀለት የሚገልጹ እንዚህ ወገኖች  በሪያድ እና በጅዳ የሚገኙ የመንግስት ተወካዮቻችን  ለዜጎቻቸው ደህነት የሚጨነቁ ከሆነ  በጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት በጂዛን የኮሚኒቲ ግቢ እና በሪያድ የኢትዮጵያ የኮሚኒት ካፍቴሪያ አዳራሾች ለዚህ የተቀደሰ ተግባር የሚውል ቤቶቻቸው የማይለየው ግቢ ውስጥ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የፀሎት ቦታ ሊፈቀድላቸው እንደሚገባ  ይናገራሉ።
በየአመቱ በኢትዮጵያውያን የኦርቶዶክስ ምዕመናን ዘንድ የሚከበሩ በአላትን ከሳውዲ አረቢያ ህግ አንጻር አንድ ቦታ ተሰባስቦ ማክበር እንኳን እንደማይችሉ የሚናገሩ እነዚህ ወገኖች ኤምባሲውን በበላይነት የሚቆጣጠሩት ዲፕሎማቶች አብዛኛዎቹ የእልምና ሃይማኖት ተከታዮች በመሆናቸው ዲፕሎማቱ ለኢትዮጵያውያኑ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ትኩረት እንደማይሰጡዋቸው ይገልጻሉ። ይህ በዚህ እንዳለ ሳውዲ አረቢያ ውስጥ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች መካነ መቃበር ባለመኖሩ በተለያየ ምክንያት ህይወታቸ የሚያጡ የዕምነቱ ተከታዮች እስከሬኖቻቸውን ወደ ሃገር ለመላክ አቅም ስለማይፈቀድ በዲፕሎማቱ ፊርማ እና ሃላፊነት ሆስፒታል «ተላጃ» ገብቷል እየተባለ ሃይማኖታዊ ስረአትን ባልጠበቀ ምንገድ በአቦጀዴ እይተጠቀለለ ወደ አልታውቀ ስፍራ እንደሚወሰድ ምንጮች አክለው ይገልጻሉ።
ቀደም ሲል አንዲት በቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ ትሰራ የነበረች የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ኢትዮጵያዊት በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ግቢ በሚገኝ ግዜያዊ መጠለያ ውስጥ ታማ ያለህክምና እርዳታ ስትሰቃይ ከርማ  ህይወቷ በማለፉ በዲፕሎማቱ ት ዕዛዝ በሳውዲ ማዘጋጃ ቤት ሰራተኞች አስከሬኗ የት እንደደርሰ እንደማይታወቅ የሚናገሩ የልጅቷ የቀርብ ቤተሰቦች  እናት  የልጃቸውን ሞት ሳይረዱ ሳውዲ አረቢያ ለስራ የሄደቸው ልጄ ከዕለታት አንድቀን ጥሪት ቋጥራ ትመጣልኛለች በሚል ተስፋ የልጃቸው ሬሳ በወግ በመአረግ ለአፈር መብቃቱን ሳይረዱ መቅረታቸውን በሃዘን የሚገልጹ ምንጮች በተመሳሳይ መልኩ ህይወታቸው አልፎ መርዶ ነጋሪ ያጡ ኢትዮጵያውያን ወላጆች ብዛት ቤት ይቁጠረው ብለዋል።
“ፀሎታችን በቤታችን” በሚል መሪ ቃል ከእንግዲህ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከጎናችን ሊቆም ይገባል የሚሉ በሳውዲ አረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች እስካሁን ሳውዲ አረቢያ ምድር ላይ ህይወታቸው አልፎ የቀብር ስረአታቸው በወጉ ሳይፈፀም የቀሩ ወገኖችን ሰም ዝርዝር ዲፕሎማቱ ለቤተሰቦቻቸው በውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መ/ቤት በኩል ይፋ ማድረግ እንደሚገባቸው ገልጸው ወድፊት እንደዚህ አይነቱ አሳዛኝ ታሪክ በዜጎቻችን ላይ እንዳይደገም ኤምባሲው ከማህበረሰቡ ጋር በመተባበር የጋራ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ በአሰቸኳይ እንዲቋቋም ጠይቀዋል።
ይህ በዚህ እንዳለ ቀደም ሲል ጅዳ ከተማ አንድ የግል መኖሪያ ቤት ውስጥ ተሰባስበው በጋራ ፀሎት ሲያደርሱ በነበሩ የኦርቶዶክ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ላይ የሳውዲ ፀጥታ ሃይሎች በወሰዱት እርምጃ ከ39 በላይ ኢትዮጵያውያን ለእስር መዳረጋቸው አይዘነጋም። ይህንን እርምጃ የሚያስታወሱ በሳውዲ አረቢያ የሚገኙ የእምነቱ ተከታዮች የኢትዮጵያ መንግስት ዲፕሎማቶች በአመታዊ በአላትም ሆነ በሳምንት አንዴም ዕመናኑ ተስባስበው በጋር መንፈሳዊ ፀሎታቸውን ያለምንም ስጋት የምናደርሱበትንም ሆነ የእምነቱን ተከታዮች  ሃይማኖታዊ ግንዛቤ እንዲዳበር የሚያስተምሩበት  መንፈሳዊ ማዕከል በኤምባሲው ስር ከሚገኙ ተቋማት ውስጥ ጅዳ፤ ሪያድ፤ እና ጂዛን ከተሞች እንዲፈቀድላቸው ተማጽነዋል።
ለህዝበ ክርስቲያኑ ምዕመናን ጥያቄ መስካት በሳውዲ አረቢያ የሚኖሩ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ከጎናቸው እንደሚቆሙ ከኢትዮጵያን ሃገሬ ምንጮች ማረጋገጥ ተችሏል። ይህን ጉዳይ በተመለከተ  በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ የሁኑትን አቶ ሸሪፍ ኬሬ +96626653444 እና ተቀማጭነታቸው ሪያድ የሆኑትን የኢትዮጵያ አምባሳደር ዶ/ር መሃመድ ሃሰን በዚህ ዙሪያ ለመነጋገር ያደርኩት ሙከራ በተለያዩ ምክንያቶች እስካሁን አልተሳካም ።
Ethiopian Hagere ጀዳ በዋዲ ለጎልጉል የላኩት

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen