Netsanet: ህወሃትና የትግራይ ህዝብ ሆድና ጀርባ!!!

Freitag, 6. Juni 2014

ህወሃትና የትግራይ ህዝብ ሆድና ጀርባ!!!

ህወሃትና የትግራይ ህዝብ ሆድና ጀርባ!!!
------------------------------------------------
ህወሃት ማሌሊትን ሲያከብር በተራበ ህዝብ ስም ከተለመነው የ100 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ እንዴት እንደባከነው ከዚህ በታች እንመልከት፡፡
ይህ ጉባኤ የተካሄደው የትግራይ ህዝብ በድርቅ እንደ ቅጠል እየረገፈ ባለበት ወቅት ነው፡፡የጉባኤው ወጭም ከዚሁ ህዝብ የጠነጠቀ ሀብት ነው፡፡ የሰው ልጅ እየረገፈ በየ መንገዱ ቀባሪ አጥቶ የጅብ ቀለብ በሆነበት ወቅት ነው ስብሰባው ለ15 ቀናት ተካሄደው፡፡ የጉባኤውን ቆይታ ወጭ ለትዝብት እንመልከት፡፡በማዕከላዊ ኮሚቴ የምግብ ዋና ሀላፊ ወ/ሮ ኤልሳ አስፍሃ የጻድቃን ገ/ጻዲቅ ሚስት ስትሆን በእሷ እዝ ስር በቅድመ ዝግጅቱ 300 ከብቶች ለእርድ ቀርበዋል፡፡ በየ ቀኑ ከ7-10 ከብቶችና ሁለት ፍየሎች ይታረዳሉ፡፡ ሁሉ ጉባኤተኛ የሚመገበው የነጭ ጤፍ እንጀራ ነው፡፡ በየ ቀኑ ጠዋት ቁርስ አንባሻና ስጋ ጥብስ፡ምሳ እና እራት ቀይ የስጋ ወጥ፡አልጫ የስጋ ወጥ፡ጥብስ ይቀርባል፡፡ በተጨማሪም የታሸጉ ፍራፍሬዎች እና አትክልት እንደ ልብ ነው፡፡መጠጥ ጠጅ፡ጉሽ ጠላ፡የጠራ ጠላ እንደ ውሃ ይንቆረቆራል፡፡ እንደዚሁም ውስኪና ቢራ በጅምላ ነው፡፡ የጉባኤው ተሳታፊዎች አብዛኞቹ የተገኙት ከነሚስቶቻቸው በመሆኑ ምርጥ ፍራሽ፤ብርድ ልብስና አንሶላ ከሱዳን ተገዝቶ እየተንፈላሰሱ ናቸው፡፡ በዚህ መሰረት በቀን የሚወጣው ወጭ እንኳንስ ሽምቅ ተዋጊ ቀርቶ የአንድ ሀብታም ሀገር መንግስትም ሊያወጣው አይችልም ነበር፡፡ …….ጉባኤው ያሰባሰበው የሰው ብዛት ጠቅላላ ድምር 7970 ሲሆን….በአጠቃላይ ሰላሳ ስድስት ሚሊዮን አምስት መቶ ሰላሳ ሁለት ሺህ ብር(36 532000)ወጭ በማድረግ የህወሃት መሪዎች ተሞሽረው ወጡ፡፡(ገብረ-መድህን፤ክፍል ሁለት ከገጽ 2-3) ዮናስ በላይ አበበ በመጽሃፉ ፉት ኖት ያስቀመጠው፡፡ 
እንግዲህ ይህ ማፈሪያ ድርጅት ነው የትግራይን ህዝብ እወክላለሁ ባሎ የሚያቅራራው፡፡ድምቄም መወከል፡፡ ለነገሩ አሽከሮቹ ብአዴንና ኦህዴድስ ወኪል ነን ይሉ አይደል!!! ‹‹ወይ ሰው ማጣት አለች አያቴ››፡፡
ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል!!

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen