የመለስ ስኬቶች ...የመለስ ስኬቶች ሲባሉ ..እነዚህን ለማየት ...
-በቅድሚያ የሃዜብ መስፍንን ኑሮና ከተቻለ :ካዝና ሁሉንም ነገር በርብሮ ማየት
-ሰመሃል መለስ በ4ሺ ብር ደሞዝ የት የት ትማር እንደነበረ ማየት
-አንድ የ6 ሺ ብር ደሞዝተኛ ጀነራል በ 60 ሚሊየን ወጪ ያስገነባውን ፎቅ ማየት
-የታናሽ ወንድሙን የ ኒቆድሞስ ዜናዊን ሃብት ማየት
-የአብዛኛው የትግራይ ተወላጆች: የደህንነት አባሎችን ካድሬዎች ኑሮ ማየት
-የአንድ ብሄር የበላይነት የሰፈነባት ሙላዋን ኢትዮጵያን ማየት
-አገሪትዋ በፊት ያላትን ወደብን ጨምሮ ዳር ድንበርዋን ሁሉ ማየት
-44% በመቶ ያሻቀበውን የኑሮ ውድነት ማየት
-ምርጫ ብሎ :ራሱ የምርጫ ቦርድ ሰይሞ ;ራሱ ተወዳድሮ ራሱ አሸነፍኩ ብሎ ሳያፍሩ መናገርን ማየት
-ባድመ እና በተለይም በሱማሊያ የውክልና ጦርነት ሲያደርጉ ያለቁትን ከ500 ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን ማየት
-አንድ ጣሳ ዉሃ ለማግኘት ከአንድ ኪሎ ሜትር በላይ በ እግሩ የሚግዋዘውን ኢትዮጵያዊ ህይወት ማየት
-ስራ ሲፈልግ ብሄር እና የካድሬ አባል ካልሆንክ ተብሎ የሚሰቃየውን ኢትዮጵያዊ ማየት
-የንጹህ ውሃ:መብራት: ኢንተርኔት :ስልክ አገልግሎቶችን በአገሪትዋ እንዳሉማየት
-በመካከለኛው ምስራቅ አፍሪቃ ጅቡቲን ጨምሮ :ያለውን ስደተኛ ኢትዮጵያውያን ኑሮ ማየት
-ኢትዮጵያ ውስጥ እየኖሩ ከመሞት ሽሽትን መርጦ በባህር ላይ ሰጥሞ የሚያልቀውን ህዝብ ማየት
-በበደኖ:አርባጉጉ: ሃውዜን ኦጋዴን እንዲሁም በጅማ እምነት እና ብሄር ላይ ያነጣጠሩ ጅምላ ጭፍጨፋዎችን ማየት
-በአዲስ አበባ ምርጫ 97 በየመንገዱ የፈሰሰውን የአዛውንቶች እና የህጻናት ደም ማየት
-በወጋዳርፋ እና አካባቢው አማራ ተብለው ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ኢትዮጵያውያንን ማየት
-በቂሊንጦ እና ቃሊቲ ያለወንጀላቸው ሽብርተኛ ተብለው የታጎሩ ንጹህ ኢትዮጵያውያንን ማየት
-ባንክ ቤት ዘረፍክ ተብሎ የተገደለውን የ9አመት እድሜ ሕጻን ነብዩን ማየት...
ይሀው ነው ;ሌላ ምታውቁት ካለ ጨምሩበት...
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen